በኦነግ የሚመራ መከላከያ አይደለም ህዝብን ነፃ ሊያወጣ ተደራጅተህ እንዳትከላከል ተበትነዋል ዱቄት ሁነዋል እያለ እያዘናጋህ እንደነበረ እንዴት እረሳህ

የቀድሞ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ኢትዮጵያን በልባቸው፣ ነፍጣቸውን ደግሞ በክንዳቸው አንግበው ጠላትን ሊፋለሙ እየገሰገሱ ነው፡፡
ደብረ ማርቆስ፡ ሕዳር 11/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በምስራቅ ጎጃም ዞን ከተለያዩ ወረዳዎች የተውጣጡ የቀድሞ የመከላከያ ሠራዊት አባላት የቀደመ ወታደራዊ ልምዳቸውን በመጠቀም ጠላትን ለመደምሰስ፤ የኢትዮጵያን የጀግንነት ታሪክ በክንዳቸው ለማረጋገጥ፤ የጀግኖች አባቶቻቸውን የጀግንነት ታሪክ በጠላት መቃብር ላይ በደማቅ ለመፃፍ ዘመቻውን ተቀላቅለዋል::
ጀግኖቹ ጠላት ወደ አለበት ሄደን እንቀጣዋለን እንጅ ጠላት ቤታችን እስኪመጣ አንጠብቅም፤ ነፃነት በትግል እንጅ በምኞት አይገኝምና ነፃነታችን በክንዳችን ልናረጋግጥ ትግሉን ተቀላቅለናል ብለዋል፡፡
የእናት ሀገር ጥሪን ተቀብለው ትግሉን በመቀላቀላቸውም ክብር እና ኩራት እንደሚሰማቸው ነው የተናገሩት።
ሀገር በችግር ውስጥ ሆና ጥሪዋን የማይቀበል ለባርነት እራሱን ያዘጋጀ ነው ያሉት ጀግኖቹ የቀድሞ የመከላከያ ሠራዊት አባላት በፌስቡክ ጀግንነት፣ በወሬም አሸናፊነት አይገኝም፤ ስለዚህ ሀገሩን የሚወድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ዘመቻውን ይቀላቀል ነፃነትና ክብሩን በትግሉ ያረጋግጥ ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
የቀድሞ የመከላከያ ሠራዊት አባል ወታደር አስረበብ ታረቀኝ የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪ ስትሆን ቀደም ሲል የሀገሯ ዳር ድንበር እንዲከበር ረሃቡን እና ቁሩን ተቋቁማ ዳገት ቁልቁለቱን ወጥታ ወርዳ ሀገሯን በውትድርና አገልግላለች፡፡ ዛሬም እንደ ትላንቱ ሁሉ ሀገሯን የደፈረውንና ክብሯን ለማዋረድ የመጣውን አሸባሪ የትግራይ ወራሪ ኀይል በመደምሰስ የሀገሯን ሉዓላዊነት ለማስከበር ኢትዮጵያን በልቧ ይዛ፣ ነፍጥ አንግባ ጠላትን ለመፋለም ወደ ግንባር አቅንታለች፡፡
ወታደር አስረበብ ከአሚኮ ጋር በነበራት ቆይታ ሀገርን ያዋረደ አሸባሪ ኀይል እናትና እህቷን የደፈረውን፣ ኩሩ ወገኗን እጁን ለእርዳታ እንዲዘረጋ ያደረገውን፣ ሃብቱን የዘረፈ እና ያወደመውን ጠላት ተፋልሞ በመቅበር ነፃነትን ከማረጋገጥ ውጭ ሌላ ምርጫ የለም ብላለች፡፡
ዘማቾቹን የሽኙት የደብረ ማርቆስ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ይትባረክ አወቀ ወጣቶች የጀግኖች አባቶቻቸውን ቆራጥ ወኔ እና ድል በመድገም ጠላትን ባለበት እንደሚፋለሙና እንደሚደመስሱ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡
ዘጋቢ፡-ዘላለም አስፋው-ከደብረ ማርቆስ

አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

SHENEህዝቤ ሆይ መከላከያን አትውቀስ
~~~~~~~~~~~~~`~~~
በማን እንደሚመራ ለምን እንደሚሸሽ
ለምን እንሸሻለን ያሉትን የወሰዱባቸውን እርምጃ መርምር፡፡
በኦነግ የሚመራ መከላከያ አይደለም ህዝብን ነፃ ሊያወጣ ተደራጅተህ እንዳትከላከል ተበትነዋል ዱቄት ሁነዋል እያለ እያዘናጋህ እንደነበረ እንዴት እረሳህ ፡፡ሀገር ለማዳን የሚዋደቁ ምርጥ ልጆች አሉ ገንዘብ ተቀብለው ለመፈርጠጥ ብቻ ሳይሆን ስነ ልቦና የሚሸረሸሩ እልፋ ናቸው፡፡
ለማሸነፋ ከብአዴንና ከብልፅግና የፀዳ አማራዊ ሀይል ሀገር ለማዳን ወሳኝ ነው፡፡
258803663 1537501079954061 3333205256434455565 n
258757964 1366080847168740 7979880623965945854 n

 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.