ፈንጂ ረግጦ ወደ ጠላት ምሽግ በመግባት ጀብዱ የፈጸመው ወጣት

258125448 6518655191543238 2881304957274316014 n ፈንጂ ረግጦ ወደ ጠላት ምሽግ በመግባት ጀብዱ የፈጸመው ወጣትየጀግንነትና የነጻነት ተምሳሌት አገር ኢትዮጵያ! በየጊዜው ዓለምን የሚያስደምም ጀብዱ የሚፈጽሙ ጀግኖችን መፍጠር መታወቂያዋ ነው። ልጆቿ ለሀገራቸው ህልውና መስዋዕት መክፈልን እንደጽድቅ ይቆጥሩታል። በጠላት መረገጥን አምርረው ይጠየፋሉ። በጠላት ከመገዛት ሕይወታቸውን ቢያጡ ይሻሉ። ይህ በታሪክ ቅብብሎሽ የታየ ሃቅ ነው።
ዛሬም አሸባሪው ትህነግ ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር በማበር በአማራና አፋር ክልሎች መጠነ ሰፊ ወረራዎችን መፈጸሙ ያንገበገባቸው በርካቶች ናቸው። ይህንን ወረራ ለመመከት በየጦር ግንባሮቹ የገቡ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ድንቅ ጀብዱ እየፈጸሙ ይገኛል።
በጋሸና ግንባር የተሰለፈው ጀግናው ወጣት ታድሶ ኃይሌ ልሳነወርቅ ጀብድ ከፈጸሙ ወጣቶች መካከል አንዱ ነው። እድሜው በ20ዎቹ መጀመሪያ የሚገኘው ጀግና በመቂት ወረዳ የገረገራ ከተማ ነዋሪ ነው። የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትም ወጣቱ ስለሰራው ጀብዱ ጠየቀው። ጀግናው በቁጥብ አንደበቱ ስለተፈጠረው ሁኔታ አጫወተን።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጠላትን ከደብረ ዘቢጥ እስከ ኮኪት እና ፍላቂት ሲያባርረው እግሬ አውጭኝ ያለው የሽብር ቡድኑ በጋሸና ግንባር አርቢት ላይ አደገኛ ምሽግ በመሥራት ተቀመጠ። ምሽግ ሰርቶ ዙሪያውን በፈንጅ አጠረ። ወጣት ታድሶና የሰፈር ጓደኞቹ ከመከላከያ ጎን በመሰለፍ መስዋዕትነት ለመክፈል ስምምነት ማድረጋቸውን አይዘነጋውም።
አካባቢህን ጠብቅ
ወደ ግንባር ዝመት
ሠራዊቱን ደግፍ
EBC

5 Comments

  1. የአብይ አህመድና የሺመልስ አብዲሳ – 45 ዙር የሰለጠነዉ ልዩ ሃይል ኢትዮጵያ በጭንቅ ተወጥራ ባለችበት ጊዜ ካልደረሰላት ለመቼ ሊሆን ነው። ወይስ ከህዉሀት ጋር የተለየ ዉል አለው ? እነዚህ ደካማ ገዢዎች መልስ መስጠት ቢችሉ መልካም ነበር። የሸፍጥ ፖለቲካ ለሁላችንም አይበጅም።

    • የሸፍጥ ፖለቲካ ብሎ ቁጭብሎ ወይም እንደ ጣቃ እየተቀረደዱ ወሬ ማናፋት አገር ትፍረስ ብሎ ከሚአፈርሰው ሃይል እና ገና ከጅምሩ አገር ገንጥሎ አስገንጥሎ የሚመራት አገር ወደብ አያስፈልጋትም ብሎ የሚዘምር ቅዘና የእንግዴልጅ ጁንታ ቡድን ለይተንአናይህም ምን አይነት የተረገመች እናት ናት እንደዚህ የዘቀጠ ትውልድ የምትወለደው ወይስ ሳትፈልግ ስለወለዳችሁ እና አስተዳደጋችሁም እንደዚሁ በሜዳ ስለሆነ ነው እንደ ሰው የማታስቡት ።

      • ሳሙኤል ከጽሁፍህ ብዙ ተምረናል በርትተህ ተሳደብ ለትውልድ ኩራት ነህ ልጆችህም ጎበዝ ተሳዳቢ አባት አለን ብለው ይኮሩብሀል።

  2. Heros are born in trying times. I wonder why ABiy AHmed and Shimles ABdissa are hoarding the 45 round trained special forces of ORomia when EThiopia is in such a difficult times. OR have they striked a deal with the devilish TPLF forces? I wish they come out in the open and expalin what th ORomia special forces are for once Addis Ababa falls to TPLF.

  3. ጎበዝ እንደዚህ አይነት ህጻናትን ማጀገን መልካም አይመስልም ይህ ህጻን ናጅ አካለ ጎደሎ የእድሜ ልክ ሸክም ሊሆን ይችላል በዚህ ተነሳስተው ትምህርት ቤት ሊሆኑ የሚገባቸው ህጻናት ብአዴንን ለማቆየት ፈንጅ ረግጠው ማምከኛ መሆን የለባቸውም ቦታቸው ትምህርት ቤት ነው።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.