ለማ መገርሳና አብይ አህመድ በእኔ እይታ – ሰርፀ ደስታ

Lema and Abiyከጥቂቶች በቀር ይህ ዛሬ እየሆነ ያለውን ይሆናል ብሎ የገመተ ያለ አይመስለኝም፡፡ ሆኖም ለውጥ ተብሎ ከተጀምረባት ቀን አንድ ጀምሮ ኢትዮጵያ ከወያኔ በከፋ አደገኛ ቡድን እጅ እንደገባች ግልጽ ምልክቶች ነበሩ፡፡ ችግሩ በግርግር በወያኔ እየተሳበበና የሃያ ሰባት ዓመት የትግሬ ወያኔ ከአዲስ አበባ መቀሌ መግባት ከምንምና ምንም በላይ እንደ ልዩ ለውጥ ተደርጎ መታሰቡ አደገኛውን የዛሬውን ቡድን ዘንግተንዋል፡፡ ያለማስተዋላችን ልከ ማለፍ የሚለካው ከወያኔ ጋርከ1983 ጀምሮ አብረው ሲገድሉና ሲያስገድሉ የነበሩ ለውጡን እንመራለን ሲሉን ቢያንስ በጥንቃቄ ማየት አለመቻላችን ነው፡፡ በእኔ እምነትና አተያይ በለውጡ ጊዜ ትልቅ ድርሻ የነበረውና በእርግጥም ከልቡ አደጋዎችን ሁሉ ሳይቀር የተጋፈጠ ቢኖር ለማ መገርሳ ብቻ ነበር፡፡ ለማ በእርግጥም ለውጡን ለሕዝብ ማድረስ ችሎ ነበር፡፡ አሁንም አሁንም በእኔ እይታና ግምገማ ነው ለማ በግልጽ ነገሮችን ይፋ በማውጣት በተለይ ኦሮሞ ምን ሲሴርበት እንደነበርና እንዴት ለወያኔ አገልጋይ እንዲሆን እንደተሰራበት በድፍረት እየተናገረ ሕዝቡ ወደራሱ እንዲያስብ አስችሎት ነበር፡፡ ገና ከጅምሩ የኦሮሞን ወጣት ቄሮ በሚል እነ ጀዋር ለአደገኛ ሴራቸው ሊጠቀሙበት ሲያዘጋጁት ለማ ነበር ቀምቶአቸው ወደ ኢትዮጵያዊነት እንዲያቀና አድርጎት የነበረው፡፡ በዛ አጭር በሆነ የትግል ወቅት በእርግጥም የኢትዮጵያዊነት አንድነት በይፋ መጥቶ ነበር፡፡ ሀያ ሰባት ዓመት ሕዝብን ከሕዝብ ለማባላት ከተሰራበት በላይ ኢትዮጵያዊነት በእነዛ የትግል የመጨረሻ ዓመታት በግልፅ መጥቶ ነበር፡፡

በዚህ ሁኔታ ነበር ከየሀገሩ ተቃዋሚ በማስገባት ሥም ከውስጥ ያሉ በወያኔ የጥላቻና ዘረኝነት ጥምቀት የተጠመቁ አጋጣሚውን ከጌቶቻቸው ወያኔዎች በወረሱት ሥልት ሌላ የሁለተኛ ወያኔ ምዕራፍ በአዲስ መልክ ያስቀጠሉት፡፡ በዚህ ሂደት በአንደበቱ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያለ ብዙዎችን እንዳያስቡ ያደነዘዛቸው ዛሬ ጠ/ሚኒስቴር የሚባለው ዋና የሴራው መሪ ነበር አሁንም ቀጥሏል፡፡ አጋጣሚውን በፍጥነት ከትግሬ ወያኔ ወደ ኦሮሞ ኦነጋውያን ለመቀየር ሙሉ በሙሉ ተጠቀመበት፡፡ አሁንም የእኔ አተያይ ነው፡፡ የራሰ መሰለኝ ምናምን ሳይሆን የሁኔታዎች መዘና (ሲቹዌሽን አናሊሲስ) መሠረት ለማ ይሄን አካሄድ ከተቃወሙትና ወያኔ የሄደችበት አካሄድ ላለመድገም ከሴረኞቹ ጋር አልተግባባም፡፡ ለማ በወቅቱ በኦሮሞ ዘንድ በጣም ተደማጭነት ስላለው ይሄን ጉዳይ ወደ ውጭ ቢያወጣው ብዙ ኦሮሞ ሁኔታዎች በማስተዋል በእርግጥም የወያኔ ዘመን በሌላ መልኩ እንዳይደገም ሊቃወም ስለሚችል ለማን በቶሎ ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዘዳንትነት ማንሳት ግድ ነበር፡፡ በምትኩ ያው የሰማንውን የኮንቪንስና ቾነፉውዝ ዘፋኙ ተተካ፡፡ አዲስ አበባን በፍጥነት በኦሮሞ ኦነጋውያን እንድትወረር ተደረገ፡፡ አብይ አህመድ ከፊት ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያለው ከሥር ከወያነ 27 ዓመት በተማረው ስልት ከወያኔም በከፋ ዛሬ ያለውን በጥላቻና ዘረኝነት የቀወሱ ስግብግብ ኦነጋውያን ተካ፡፡ ዛሬም ድረስ ይሄ ለብዙ ኢትዮጵያውያን ግልጽ አልሆነለትም፡፡ ለማ ከኦሮሚያ ወደ መከላከያ ሚኒስቴርነት ከዛ ከእነጭርሱ ከመዋቅሩ ሳይቀር እንዲወጣ መደረግ ብቻ ሳይሆን ጭራሽ አብይ ለኢትዮጵያ የሚሰራ ለማ ግን የኦነግን ሴራ እያሴረ እንደሆነ በገንዘብ በገዛቸው ዮቲውበሮች፣ ጋዜጠኞችና ሚዲያውች አብይ አስወራ፡፡ በሬ ካራጁ ይውላል ይሄ ነው፡፡

እንደ እውነቱ ለእኔ የለማ የአብይም ማንነት አያሻማኝም፡፡ ለማን ለመጀመሪያ ጊዜ የኦሮሚያ ፕሬዘደንት ሆኖ ከአን ፍጹም ጋር በኢንቨስትምነት ጉዳይ በአንድ ወቅት ኢንቨስተሮችን ሰብስቦ ሲናገር የሰውዬው ማንነትና ቅንነት የገባኝ፡፡ ያ ንግግሩ ከኦሮሚያ ፕሬዘደንት ከተባለ ሰው ሆኖ ስሰማ ትልቅ ራዕይ ያለው ሰው እንደሆነ ነበር የታዘብኩት፡፡ ዛሬ በአሜሪካ አምባሳድር የሆነው ፍጹም ይሄን ክስተት ያስታውሰው ይሆናል፡፡ ይበልጠውንም በአካል ስለሚተዋወቁ መቼም ይገባዋል፡፡ በተቃራኒው አብይ አህመድ የሚባለው ሰው በየተገኘበት ቦታ በሚያወራቸው ንግግሮቹ አዋቂነቱን ለማሳያት የሚያደርገውን መጋጋጥ በግልፅ አይ ነበር፡፡ ጠ/ሚኒስቴር ተብሎ እስከተሸመበትና ስለኢትዮጵያ በአስመሳይነቱ ያቀረበውን ንግግር እስከሚናገር እኔ ለዚህ ሰው ያለኝ ግምት ሥህተት አልነበረም ብዬ አምናለሁ፡፡ በወቅቱ እኔ ለማ ጠ/ሚኒስቴር እንዲሆን አልፈለግኩም፡፡ ምክነያቴ ከጠ/ሚኒስቴርነቱ ቦታ ይለቅ የኦሮሚያው ፕሬዘዳንትነት ቦታ ቁልፍ እንደሆነ ስለማስብ ነበር፡፡ ለማ ከኦሮሚያ ፕሬዘዳንትነት ቦታ ከተነሳ ነገሮች ሊበላሹ እንደሚችሉ ብዙ የማያቸው ምልክቶች ስለነበሩ፡፡ የጠ/ሚኒስቴርነቱ ቦታ በወቅቱ የዛን ያህል ወሳኝ አልነበረም፡፡ ሆኖም አብይ ቦታውን ስለሚፈልገው ጭምር ሆነ፡፡ ከሆነ በኋላ ያው በፊት ጀምሮ የሚናገረው አይነት አስመሳይነቱ ቢያሳስበኝም መጀመሪያ በግርግርና የበለጠ ለማስመሰል የሄደባቸው ጥረቶች በእርግጥም እኔንም እንድቀበለው አድርጎኝ ነበር፡፡ በወቅቱ እስኪ ሁኔታዎችን እኔም እንደሰው ላስብ በሚል የራሴን የውስጥ ስሜት ትቼ መደገፍ እግረ መንገዴንም ወሳኝ ብዬ የማስባቸውን መጠቆም ቀጠልኩ፡፡ ነገሮች ግን እየቆዩ አደባባይ መውጣት ጀመሩ፡፡ በተለይ አብይ አህመድ አሜሪካ ደርሶ ከእነጀዋር ጋር ተነጋግሮ ከተመለሰ በኋላ በፊትም እሰጋው የነበሬ ሴራ ፊንጭ ታየኝ፡፡

ለማ የዲሞግራፊ ለውጥ እያደረግን ነው ብሏል የሚል ቪዲዮ ብቅ አለ፡፡ ያ ቪዲዮ ከተናጋሪው ለማ ይልቅ ሌሎች ሆን ብለው ከኋላ እንድ ሴራ እያሴሩ እንደነበር ባስብም ምን አልባት ለለማ ያለኝ እምነት ከመጠን በላይ ይሆል በሚል በወቅቱ ከየትኛውም ወገን ሳልሆን አስተያየቴን ሰጥቼ ነበር፡፡ ጉዳዩ ግን በጥላቻና ዘረኝነት ያበዱ ስግብግብ ወያኔ የአስተሳሰብ ባሪያ ያደረገቻቸው ኦሮሞ ኦነጋውያን ባሉበት ስብሰባ ላይ የኦሮሚያ ፕሬዘደንት የሆነው ለማ ተጠይቆ የመለሰው መልስ እንደሆነ ግልጽ ነበር፡፡ በኦሮሞ ኦነጋውያን ፊት ኢትዮጵያዊም ኦሮሞም ሆኖ መገኘት እጅግ ፈታኝ ነው፡፡ ለማን የገጠመው ይሄ ነበር፡፡ በሕይወቱ የመጡበት ወያኔዎች ኦሮሞ ከሆኑት ኦነጎች ለለማ የተሸለ የመናገርና በራሱ የመወሰን እድል ሰጥተውታል፡፡ የኦሮሞን በጥላቻ ቂም፣ የበታችነትና ዘረኝነት የተመረዘ ፖለቲካ ለብዙዎች አይገባቸውም፡፡ ለማ በዛን ወቅት የገጠመው ይሄ እንደነበር እረዳለሁ፡፡ የጀመረውን ኦሮሞን ወደ አባቶቹ ልዕልና የመመለስ ሕልሙን ሁሉ እንደሚያበላሹበት ገብቶት ነበር፡፡ በመጨረሻም ለማ ከዛ ቦታ ካልተወገደ ችግር ሊሆን እሚችል ስለተረዱ ለማን ከኦሮሚያ ፕሬዘዳንትነት ወደ ማዕከላዊ መከላከያ ሚኒስቴርነት ከዛም ከእነጭርሱ ከእነሱ መዋቅር አወጡት፡፡

በዚህ መልኩ ነው ለማ ወደ ኢትዮጵያዊነትና ወደ ቀድሞ አባቶቹ እየመለሰው የነበረው ኦሮሞ በፍጥነት 27 ዓመት ወያኔ ባጠመቀችው የጥላቻ፣ ዘረኝነትና የበታችነት ብዙውን ኦሮሞ ወደለየለት የጥላቻ፣ ዘረኝነት፣ ስግብግብነት እብደት ያሸጋገሩት፡፡ ከቀን አንድ ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ከወያኔ ዘመን በከፋ አረመኔነቶችን ማየት ጀመርን፡፡ ከጌዲዎን፣ ባሌ አርሲ፣ ሲዳማ ……. ስንቱ ተቆጥሮ ይዘለቃል፡፡ ኦሮሞ ኦነጋውያን የወያኔ ሁኔኛ ፈረስ እንደሆኑት ኦሮሞ ኦነጋውያኑም በአቅማቸው ሲዳማን እንደፈረስ መጠቀም ጀመሩ፡፡ እንግዲህ እንዲህ በአለ እውነት ነው ስንት ተስፋ ተደርጎ የነበረው ለውጥ የተባለው ዛሬ ያለንበት ያደረሰን፡፡

አብይ አህመድ ሰው እያረደና እያሳረደ በመናፈሻ ፎቶ ሕዝቡን አደነዘዘው፡፡ ምሁር ነኝ የሚለው ሁሉ የእዙ መንጋ ሆነ፡፡ ወያኔ ትግሬዎቹ አነሰም በዛም የመንግስት መዋቅር አስራርን ይጠቀሙ ነበር፡፡ ኦሮሞ ኦነጋውያኑ ከወያኔ የተማሩት ነገር ቢኖር ዘረኝነትና አረመኔነቷን ብቻ ስለሆነ ስግብግብነታቸውን እንኳን በመጠኑም ቢሆን የሚደብቁበት ሥርዓት ብሎ ነገር የላቸውም፡፡ ለዛም ነው አዲስ አበባን የሚያህል ከተማ ውስጥ ከፍት ባገኘህው ቦታ ሀሉ ግባ መብትህ ነው እያሉ ሲያውጁ የነበሩት፡፡ ይህን እንግዲህ የተናገረው ይሄው ዛሬ ጠ/ሚኒስቴር የሚሉት ነው፡፡ በተቃራንው ከቀን አንድ ጀምረው ኦሮሞ ያልሆነን ከአዲስ አበባ ዙሪያ ከተሞች ማጽዳት ጀመሩ፡፡

ይሄን ሁሉ ዛሬ ያዩት ምዕራባውያን ኢትዮጵያ በለየላቸው ወሮበሎች እንደተያዘች ሲያስቡ ብዙዎች ከወዳጅነት ወደ ንቀት ሄዱ፡፡ የዛሬው የአሜሪካ የአመራር ቡድን ከወያኔ ጋር ያለውን ትስስር ሊጠቀምበት ካስቻሉት ጉዳዮች አንዱ ይሄው መረን የለቀቀ የኦነጋውያንን ስግብግብና በጥላቻ የተጠመቀ ማንነታቸው በመረዳታቸው ነው፡፡ የኢትዮጵያውያንን ለአገራቸው ስላላቸው ፍቅር የውስጥ ጉዳያቸውን ምን ያህል እንደሚታገሱ አለመረዳታቸው ነው እንጂ አሁን ለወያኔ ዳግም እድል ለመስጠት የኦነጋውያን የለየለት ተውረኝነት ጥሩ አጋጣሚ እንደሆነ ገብቷቸዋል፡፡

ይሄ ዛሬ እሆነ ያለው እንዳይሆንና ኢትዮጵያን የወያኔን ሰንኮፎች ሁሉ ነቅሎ ለኢትዮጵያውን በማስረከብ ትልቅ የልዕልና ማማ ላይ የሚያስወጣችሁ የታሪክ አጋጣሚ ነውና ተጠቀሙበት ብልን ክልብ ብንመክርም በወያኔ የተጫነ ዘረኝነት፣ ጥላቻ የበታችነት አጋጣሚውን በስግብግብነት አበላሹት፡፡ ያሳዝናል፡፡ ዛሬም ድረስ ለወያኔ ዋና ጉልበትና ፈረሷ ይሄው በደህና ቀን የአስተሳሰብ ባሪያ የአደረገቸው የኦነጋውያን ስሪት ነው፡፡ ያሳዝናል፡፡

ይህ በአጭሩ በእኔ እይታ በአብይና ለማ መካከል ያለው መሠረታዊ ልዩነት ነበር፡፡ ለማ ክልቡ የኦሮሞን ሕዝብ ወደ አባቶቹ ልዕልና መመለስ ከምንም በላይ ክብር እንደሆነ ቢያምንም አብይና ቡድኑ ግን ከወያኔ የወረሱት በወያኔ ያዮት ስግብግብነት ሊፋታቸው አልቻለምና ኢትዮጵያን እንደ ሀገር አዋረዷት፡፡ ኢትዮጵያ ተነሳለች እነሱ ግን የሚነሱ አይመስለኝም፡፡ እየሆነ ያለው ሁሉ የእነሱ ሴራ ይገለጥ ዘንድ ነው፡፡

ኢትዮጵያውያን ሁሉ ማንም አያስታችሁ፡፡ ለትግሬው ትግሬ ወያኔ አልጠቀመውም፡፡ 27 ዓመት በሴፍቲ ኔት አኑሮት ይሄው በስተመጨረሻ ጭራሽ ዘሩ የሚጠፋበት ጦርነት ውስጥ ከተተው እንጅ፡፡ ለኦሮሞው ኦነግ አልጠቀመውም፡፡ 27 ዓመት ያን ሀሉ ግፍ ያደረገበት ሳያንስ ዛሬም ድረስ በወያኔ የአስተሳሰብ ባርነት እንዲኖር በይፋ እያየው ነው፡፡ ሁሉም ቢሆን የሆነ የእሱ ዘር ሥልጣን ስለያዘ አይጠቅመውም፡፡ ሲጀምር ከህሊና ያልሆነ ጥቀም ምን ሊሆን፡፡ ሞት ለእነደዚህ ያሉት ቅርብ ነች፡፡ ሳይበሉት የሚሞቱት ብዙዎች ናቸው፡፡ ሕሊና ንጹኅ ከሆነ ምንም ባይኖር ሰላም አለ፡፡ የገዛ ጎረቤቱን ጠላት አድርጎ ጦርነት ወደቤቱ እየጋበዘ ሠላም የለም፡፡ እኛ እንደሕዝብ ማሰብ እንጀምር፡፡ ከ60ዎቹ ጀምሮ የመጣብን አውሬ ትውልድ እየበላንና እያባላን እድል ሌላ እድል አንስጠው፡፡ አሁን ለእነሱ እድል የለም፡፡ ለኢትዮጵያውያን ግን አሁንም እድል አለ፡፡ ማስተዋል ግን የስፈልጋል፡፡

ኢትዮጵያዊ ለሆናችሁ ዛሬ ጦርነቱን እየመራችሁ ላላችሁ በአጭር ጊዜ ጦርነቱን ማጠናቀቅ ግድ ይላል፡፡ የመንግስቱን መዋቅር የያዙት ጦርነቱ በቶሎ እንዲያልቅ አይፈልጉም፡፡ ለጊዜው እነሱ ያሉበት አዲስ አበባ ደህና ነች፡፡ ወያኔ የትኛውንም ሴራ ልትጠቀም እንደምትችለ አስተውሉ፡፡ ሰሞኑን ሚሌን ይዘናል ብዙ አስወርተዋል፡፡ ይሄ ስልታቸው ከላይ ከአላማጣ ጀምሮ ነበር፡፡ በምርኮኛም ይሁን በስደተኛ መልክ ያሉትን በደንብ ሊታሰብበት ይገባል፡፡ ሚሌም ሆነ ሌላ ቦታ የሚዋጋን ወራሪ መጠበቅ ሞኝነት ነው፡፡ ሚሌ ላይ መሣሪያና ሌላ ትጥቅ አዘጋጅቶ የሚጠብቀው የቀመጣል እሱ እንደ ማንኛውም ሰው አፋር መስሎ ሚሌ ይገባል፡፡ አሁን ላይ ያለው ተስፋ እንደዛ ባያስኬድም ከመጀመሪያው ጀምሮ ያየንው የወያኔ ታክቲክ የሄ ነው፡፡ ምርኮኛ የሚባሉት በሙሉ በልዩ ሥፍራ እንዲቆዩ ማድረግ ግድ ይላል፡፡ እስካሁን የምናየው ወደኋላ ተመለሰ ነው፡፡ እስከመቼ ነው መከላከል፡፡ ተከላክሎ የሚያሸንፍ ሰራዊት የለም፡፡ ጊዜውን ማሳጠር ግድ ይላል፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! አሜን

 

3 Comments

  1. Well, because we have or may have differences in why and how we perceive and understand and interpret things , it is not difficult to take the way the writer of the above piece of comment tried to see the differences between the two politicians of OPDO as normal and healthy argument .
    But as a matter of the very political agenda of ending the deadly politics of ethno-centrism led by TPLF and replacing it with the much more hegemony of Oromuma and Oromization by distorting and destroying the political history of northern Ethiopia just like what they are doing right , there was no and still there is no difference at all ! It was Lemma who went to extent of deceiving or fooling the people by declaring a very hypocritical or cynical rhetoric such as Ethiopiawinet sus ( to be an Ethiopian is just intrinsic addiction) . If he was and is really a man of truth, he could stay with the people who are suffering untold suffering and help them to make themselves free from the very tragic and deadly political practice he grew . To my understanding the comparison and contrast between the two in a way the writer tried to is misleading .

  2. የለማና የአብይ ጉዳይ አበው እንደሚሉት “ከዝንጀሮ ቆንጆ ምን ይመራርጡ” ነው:: ኢትዮጵያን በሚመለከት ከዚህ በፊትም ሆነ አሁን በግልፅም ይሁን በድብቅ የሰሩትና እየሰሩ ያለው (ምንም እንኳን ለማ በይፋ ከመድረክ ቢገለልም) ያገሬ ስው እንደሚለው ” ለእኔ እናት ማን በጃት አንዱ አፈር አለበሳት አንዱ ድንጋይ ጫነባት” ነው:: አቶ ሰርፀ ደስታ ይሄ አባባል እንደሚገባዎት ተስፋ አደርጋለሁ!!

    ተስፋሁ

  3. Serste:

    For me, the issue is “ke zengero konjo min yemerartu” meaning all monkeys-OLF fascists-are the same with regard to their hate towards Amharas..

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.