የሕወሓት ቅጥረኛው ማርቲን ፕላውት የሀሰት ዜናን ስለመፍጠር ሲያሰለጥን የሚያሳይ ምስል ወጣ

ኢትዮጵያ ላይ የውጭ ጫናን ለማበርታት የአሸባሪው ሕወሓት አፈቀላጤ ሆኖ እየሰራ የሚገኘው ማርቲን ፕላውት የሃሰት ዜና እንዴት መፍጠር እንደሚቻል ሲያሰለጥን በድብቅ የተቀረፀው ተንቀሳቃሽ ምስል ወጣ።
የአፍሪካ ቀንድን ፖለቲካ ለዓመታት ያጠናውና የ”አንደርስታንዲንግ ኤርትራ” መጽሐፍ ደራሲው አሁን ላይ የለየለት የሽብር ቡድኑ ሕወሓት የውጭ አገር አፈቀላጤ ሆኖ እየሰራ ነው።
በዚህም በየደቂቃዎች ልዩነት በኢትዮጵያ ላይ የሀሰት ዜና በማሰራጨት የተጠመደው ማርቲን ፕላውት እንዴት የሀሰት ዜና እንደሚሰራ አገር ለማፍረስ አጋርነት ለፈጠሩት የጥፋት መልዕክተኞች ሥልጠና ሲሰጥ የሚየሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ወጥቷል፡፡
“ለቪኦኤና ለቢቢሲ ትግርኛ ለዜና የሚሆን መረጃ ልንሰጣቸው እንችላለን በእርግጥ መገናኛ ብዙኃኑ የዜና ረሃብ ያለባቸው በመሆናቸው ያለንበትን እውነታ ከግምት ውስጥ ለማስገባት ማሰብ አይጠበቅብንም” ሲል ተደምጧል፡፡
“ጋዜጠኞች አንድ ህዋስ ያላቸው ቀላል ፍጡራን ናቸው፤ ነገሮችን ይፈልጋሉ፤ ጎግልን ይፈትሻሉ ነገር ግን አያጤኑትም ያገኙትን ያወጣሉ” ሲል እነሱ ስለሚዘውሯቸውና በጋዜጠኝነት ካባ መገናኛ ብዙኃን ውስጥ ስለገቡ አካላት ይገልፃል።
“የሀሰት ዜናውን መስራት አስፈላጊ ነው፤ መስራቱ ያን ያክል ከባድ ላይሆን ይችላል ብሏል” በድብቅ ተቀርፆ በተለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምስል፡፡
ዜናው ሲፈበረክ ስለሚሰራበት አቅጣጫ ማስተዋል እንደሚያስፈልግም ለቅጥረኛ ሰልጣኞቹ ይመክራል፡፡
ኅዳር 7/2014 (ዋልታ)
ተጨማሪ ያንብቡ:  ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ስልጣናቸውን ማስረከብ አለባቸው!! የዘ-ሐበሻ ድረ ገጽ የአቋም መግለጫ

3 Comments

  1. ይህን ግለሰብና የመሳሰሉትን በኢትዮጵያ ላይ የዘመቱ ቅጥር ነፍሰ ገዳዮች ዜናቸውን ብቻ አንብቦ ማለፉ ተገቢ አይደለም።የድርሻችንን ልንወጣ ግድ ይላል።ኢትዮጵያን በአገራችን ጉዳይ ሁላችንም ያገባናል።እነ ማርቲን ፕላው በየቀኑ በሚፈነጩበት በተለይ የቲዊተር(twitter) ገጽ ልናሳጣቸው እንችላለን።እውነት ከኛ በኩል ስላለ ልናጋልጣቸው ግድ ይላል።በተለይ ከወይኔዎች ጋር በአማሪኛ ከመሰዳደብ በተቻለ አቅም እነ ማርቲንን ሥራዬ ብለን በዓለም ሕዝብ ፊት እናሳጣቸው።አንድም፣ አሥርም፣ ሃያም ሆነን፣ሥራዬ ብለን፣ ማርቲንን የመሰልሉትን ብቻ ቀን በቀን አስተያቶቻቸው ማርከስ ግዴታችን ይሁን።
    ኢትዮጵያ አገራችን በአደጋ ላይ ባለችበት በአሁኑ ሰዓት ግማሹ ጦርነት በመገናኛዎች የሚደረገው ውጊያ ነው።ይህ ጦርነት ከሽምቅ ውጊያው ባላነሰ መልኩ የሰውን ሕሊና መማረኩ አንዱ ግቡ ነው።ጠላቶችን አናውቃቸዋለን።እነ ማርቲን በጠራ ፀሐይ የቃላት ናዳ አያወረዱብ ነው።ከኛ ተሽለው፣አገራችንን ከኛ በበለጠ አውቀዋት ሳይሆን የእኛ ዓይነተኛ ችግር “የት ይደርሳሉ፣ምን ያመጣሉ” በሚል ትዕቢት ተውጠን ለጠላት ፋታ እየሰጠን ነው።ማርቲንን የመሰሉ ግለሰቦችን ብቻ ሳንሰለች ሁለትና ሦስት ወራት እየተከታተልን መልስ እንስጥ።አቅማቸው ሲዳከም ውጤቱን የምናውቀው ሙግታቸው እያነሰ ደብዛቸው እየጠፋ ይመጣል።በማነፃጸር ዴቭነሰን(Davison) የሚያቀርበው ትርኪ ምርኪ እያነሰ መምጣቱ ጫናው እንደከበደው ማስረጃ ነው።በተቻለ ማርቲንና መሰሎቹን በነገር ሁካታ እንክበብ።እንረባረብ።ጊዜያችንን በስደብ በጊዜው ባናደደን ግለስብ ላይ አናጥፋ።የድርሻችንን እናዋጣ። ድሉ የኛ ነው።ኢትዮጵያ ዘላዓለም ትኖራለች።

  2. ታሪክ ምስክሩ መልካም ብለሀል ክአል ማርያም በቀር ደፍሮ በፈረንጅ አፍ የሚጽፍ ጠፋ

  3. He is old in age but spent his life time in making fake news, the worst thing he is doing, the evil esprit of his mind.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share