የግል መገናኛ ብዙሃን ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ሊሰሩ ይገባል

Yonatan
የግል መገናኛ ብዙሃን ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ሊሰሩ እንደሚገባ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን አሳሰበ።
ለንግድ አገልግሎት የተቋቋሙ አንዳንድ የሚዲያ ተቋማት አገሪቷ አሁን ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ ሳያገናዝቡ እየሰሩ መሆኑን ባለስልጣኑ ጠቅሷል።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዮናታን ተስፋዬ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ ብዙዎቹ የግል መገናኛ ብዙኃን ኢትዮጵያ ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ ተገንዝበው ለዚህም የሚመጥን ሥራ እየሰሩ አይደለም፡፡
መገናኛ ብዙኃኑ ከዚህ በፊት ከተለመደው አሰራር እና የአዘጋገብ ስልት ወጥተው ኢትዮጵያና ዜጎቿን ከገጠሙት ወቅታዊ ችግሮች ሊያሻግሩ በሚችሉ ዘገባዎች ላይ ሊያተኩሩ ይገባል ብለዋል።
የህዝብ ሚዲያዎች በአንፃራዊነት በአገራዊ ህልውናው የተሻሉ ስራዎችን እያከናወኑ መሆኑን ጠቅሰው የግል መገናኛ ብዙሃንም ለአገራቸውና ህዝባቸው ወግነው እንዲሰሩ ጠይቀዋል።
በመዝናኛው ዘርፍ የተሰማሩ ሚዲያዎችም ቢሆኑ አገራዊ አንድነትና አብሮነትን የሚያጠናክሩ የኪነ-ጥበብ ሥራዎችን በማቅረብ ዜጎች ለአገራቸው እንዲነሳሱ አስተዋጽኦ ማድረግ የሚችሉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት አገር አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ስትገባ ወቅቱን የሚመጥን ሥራ በማከናወን ረገድ ድርብ ኃላፊነት እንዳለባቸውም ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አስገንዝበዋል።
ለውጭ ሚዲያዎች ወኪል በመሆን በአገር ውስጥ የሚገኙ የሚዲያ ባለሙያዎችም ያገኙትን ዕድል ተጠቅመው የአገራቸውን እውነታ ለዓለም ማሳወቅ ይኖርባቸዋልም ብለዋል፡፡
እነዚህ ባለሙያዎች አገራቸውን በተመለከተ የሚነዙ የውሸት ፕሮፓጋንዳዎችን መቃወም እንዳለባቸው ጠቅሰው፤ይህን በመሥራትም ለኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች መሆን እንዳለባቸው ተናግረዋል።
ለውጭ ሚዲያዎች ወኪል ሆነው የሚሰሩ ጋዜጠኞች አገር ከምንም በላይ መሆኗን በቅጡ ተረድተው የህዝቡን ስነ-ልቦና፣ ማንነትና ታሪክ ጠብቀው የኢትጵያን ብሄራዊ ጥቅም በሚጎዳ ሥራ ላይ ባለመሳተፍ አገራዊ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ አስገንዝበዋል፡፡
ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ እንድትወጣ ከመንግሥትና ከህዝብ ጎን በመሆን የተጀመረውን ጥረት መደገፍ የሁላችንም ግዴታ መሆኑን ተናግረዋል።
******************
(ኢ ፕ ድ)

1 Comment

  1. Well, it sounds good; but you desperately need to go with your political stupidity of making lie after lie and after lie that has nothing to do with the very horrible reality in the ground !

    Yes, media needs to be as truthful and balanced as possible . But you seriously need to get out of the vey criminal political system you carried out for a quarter of a century as speaking tools of TPLF , and the very unprecedented political crime you either directly committed or indirectly committed !
    It is then and only then you can talk about what others did and are doing . It must be clear that a politically motivated crimes cannot be challenged by politicians were and are chronically ill ! Never, never and never !!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.