ለራሷ ያላወቀች ለቅዱስ ገብርኤል መድኃኒት ጠየቀች !

ኦባሳንጆ በካርተር ዘመን ለአሜሪካ የስለላ ድርጅት እንዲሰራ የታጨ ናይጄሪያዊ ነው። አሁንም ያው የአሜሪካንን ሚና ለመወጣት በአፍሪካ ሽፋን በየላኩት ቦታ ይጓዛል። የአፍሪካ ሕብረትን በጀት ምዕራባውያን ስለሚሸፍኑ ሕብረቱ በታዘዘው መሰረት የነአሜሪካ አስፈጻሚ አካል ነው። የቦኮሃራምን ችግር ያልፈታ ሰውዬ ለኢትዮጵያ መድኃኒት ሆኖ ሲመጣ እጅ በአፍ ያስጭናል።
በመንግሥት በኩል የሚደበቅ ምንም ነገር የለም ….. ኦባሳንጆ እውነትን እንዲያፈላልጉና መረጃ እንዲሰበስቡ የመቀሌውን ጉዞ አመቻችተናል ! ብሏል የኢትዮጵያ መንግስት፤ ኦባሳንጆ ከመቀሌ ተመልሷል ፤ ዛሬ አማራና አፋር ክልል ያሉ ባለስልጣናትን ሊያናግር ይበራል። አዲስ አበባ ያሉትን ማናገሩን ነግሮናል። መንግስት የኦባሳንጆን የመፍትሔ ሀሳብ በጉጉት እንደሚጠብቅም ነግሮናል። በሁለቱም ወገን በኩል የእሳቸው የማደራደር ጥረት ተቀባይነት አግኝቷል።
ለማሸማገል እየሞከሩ ካሉት የፌደራል መንግሥት ወይም የህወሓት አመራሮች ዘንድ ሸምግልናውን አልቀበልም ያለ ወገን አለ? ተብለው የተጠየቁት ኦባሳንጆ፤ “የአፍሪካ ሕብረት ሰላም ለማምጣት፣ ንግግርን ለማስጀመር እና ደኅንነትን ለማስጠበቅ ልዩ መልዕክተኛ መሰየሙን ሁሉም ወገን በበጎ ነው የተቀበሉት” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
ድርድር ጥሩ ነው፤ ተደራድሮ መስማማትም ይበል የሚያሰኝ ነው። ድርድርን በተመለከተ የሕወሓት የኃላ ታሪክ ስናጤነው ግን ድርድር ከሕወሓት ጋር ለመጪው ጊዜ አደጋ ከመፍጠር ውጪ ምንም ፋይዳ የለውም። መንግስት መደራደሩን ስንደግፍ ከሕወሓት ጋር ያለው የድርድር ሂደት ኝ ውጤቱ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ይገባል። ደግሜ ለማስታወስ ያሕል ሕወሓት የድርድር ታሪኩ በራሱ ተንኮል የቆሸሸ ነው።
አሜሪካኖቹም ቢሆኑ እያየነው ያለነው ነገር ለሕወሓት እያደሉ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫና እየፈጠሩ ነው። ኦባሳንጆም ሌላኛው የነሱ ታዛዥና ተላላኪ ነው፤ በዚህ ጦርነት ዙሪያ እንደተሾመ የመጀመሪያውን ንግግርና ኝኙነት ያደረገው ከአሜሪካ ባለስልታናት ከሳማንታ ፖወር ና ፌልትማን ጋር ነበር፤ እነሱ ጋር ያለውን ሂደት ጨርሶ ነው ፊቱን ወደ ኢትዮጵያ ያዞረው። ሕወሓትን ኦባሳንጆን አልቀበልም ካለ በኃላ ከኦባሳንጆ ውጪ ወደ ውጪ ያለው በአሜሪካ ትዕዛዝ መሆኑ እሙን ነው። እና ይህ ድርድር ምን ያህል አዋጪና የሚሳካ ነው ብሎ መጠየቁ ግድ ነው። ድርድሩ ባይከፋም መጠንቀቁ ግን አይከፋም። የሚሰማ ካለ !

(ምንሊክ ሳልሳዊ)

ተጨማሪ ያንብቡ:  የባህርዳሩ ሰላማዊ ሰልፍ፣ በግርማ የሺጥላን የተኩት ሰው፣ ፕ/ት ኢሳያስ ፈረሙ፣ “አዲስ የጉዞ ክልከላ ደርሶኛል” ጄ/ል ተፈራ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share