ዛሬ በአሜሪካ የተቋቋመው ፓርቲ: ጋሼ እንደነገሩኝ

252824375 10158927607069915 1707681250213576483 n

ጋሼ እና ባለ ወደቧ ጎንደር

(እውነተኛ ታሪክ)

ከጥቂት አመታት በፊት እኔ እና የተወሰኑ ሀገር ወዳድ ወዳጆቼ ሆነን ኢትዮጵያዊነትን የሚያቀነቅን ፓርቲ ለማቋቋም ተነሳን፡፡

በኛ ብርታት ሳይሆን ኢትዮጵያብለን ስለተነሳን ብቻ ብዙ ድጋፍ አገኘን፡፡ ከሰሜን እስከደቡብ ከምስራቅ እስከ ምእራብ ተዘዋውረን ደጋፊ አሰባሰብን፡፡ ኋላ ላይ ትንሽ የተደራጀን ሲመስለን አዲአበባ ካሉ ኢትዮጵያከሚሉ ፓርቲዎች ጋር ህብረት እንፍጠር አልንና በኔ ግምት አንድ ቀን የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብሰባ ላይ ወ/ት ብርቱካንን በነገር ሲሸነቁጡ አይቼ ቆፍጣናብዬ ካሰብኳቸው አንድ የፓርቲ አመራር ጋር ከአብሮ መስራት አስከ ውህደት ድረስ ለመነጋገር ቀጠሮ ያዝን፡፡

ለመጀመሪያ ቀን የአንድ ለአንድ ግኑኝነት እኔ ኢብንን እንድወክል ተመረጥኩና ወደ እሳቸው ፓርቲ ቢሮ አመራሁ፡፡

ስማቸውን መጥቀስ ስለማልፈለግ ከዚህ በኋላ ጋሼብለን እንጥራቸው፡፡

ጋሼ እንደነገሩኝ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ከ80ዎቹ ጀምረው ጥርሳቸውን ነቅለዋል፡፡(በርግጥ በስኳር ይመስለኛል የታችኛው ጥርሳቸውም ሁለቱ ተነቅሏል)

ገና እንደደረስኩ ጋሼ ስሜንና ፓርቲዬን እንኳን በደንብ ሳይጠይቁኝ ያለ ምንም መንደርደርያ የፖለቲካ ገድላቸውን መተረክ ጀመሩ፡፡

በወያኔ ግዜ ከሚጠቅስላቸው ትላልቅ ገድሎች መካከል ዋናው በአንድ የግል ጋዜጣ የፊት ፔጅ ላይ በ1990ዎቹ መጀመሪያ ፎቶዋቸው መውጣቱ ብቻ ነበር፡፡(ጋዜጣውንም አጋጣሚ በሚመስል ሁኔታ ጠረጴዛቸው ላይ ጣል አድርገውታል)፡፡

ስለ አይዶሎጂ እና መሰል ነገሮች ያወራነውን ምናልባትህይወቴና ፋታ ያልሰጠኝ የፖለቲካ እርምጃዬበሚለው መጽሃፌ ሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ፡፡ ሎል

ከንግግራችን እንደገባኝ ጋሼ ፌዴራሊዝምየሚል ቃል መስማት እንኳን ያማቸዋል፡፡ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ራሱ የእግር ኳስ አሃዳዊ ጽ/ቤትቢባል ደስ ሳይላቸው ይቀራል!?)፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ወልቃይት: ለዶ/ር ዓብይ አህመድ የተሰጠ መልስ - ቻላቸው አባይ እና ብርሃኑ ጥሩ ይናገራሉ

ግን ደግሞ ጋሼ እንደነገሩኝ አስተዋይ እና አርቆ አሳቢ ስለሆኑ ምናልባት ፌዴራሊዝም ለኢትዮጵያ ግዴታ ከሆነ በሚል አማራጭ የራሳቸውን መጠባበቂያ መፍትሄ አዘጋጅተዋል፡፡

ጂኦግራፊያዊ ፌዴራሊዝም ስራ ላይ የሚውል ከሆነ በታሪክና በፖለቲካ ሊቃውንት ተጠንቶ የተዘጋጀው የኢትዮጵያ ካርታየሚል አንድ በላስቲክ የተጠቀለለ ዶክመንት ከመሳቢያቸው አወጡና ጠረጴዛው ላይ ዘረጉት፡፡

በእውነቱ አስቀድመው የኢትዮጵያባይሉኝ ኖሮ ካርታው የሀገሬ ይሁን የሩስያ ማወቅ አልችልም ነበር፡፡

በካርታው ሰሜናዊ ክፍል ጋሼ ጎንደርብለው የሰየሙት በሰሜን ቀይ ባህር የሚያዋስነው ታላቅ ክፍለሀገር አለ፡፡በታች በኩል መጀመሪያ ጅቡቲ የመሰለችኝ ትንሽ ክ/ሀገር ኋላ ላይ በደንብ ጠጋ ብዬ ሳያት ኤርትራየተሰኘች ነቁጥ ክልል ትታያለች፡፡

አሁን ላይ ሳቄ በጣም እያፈነኝ ነው፡፡

..”ጋሼ ግን ይህ ካርታ ትንሽ ከጎረቤትም ከተቀረው አለምስ አያጣላንም?!” አልኳቸው…ፈራ ተባ እያልኩ፡፡

አይ የዛሬ ልጆች ምንም የምታውቁት ነገር ሳይኖር እኮ ነው ዘላችሁ ፖለቲካ ውስጥ የምትገቡትአሉና …ተቆጡ፡፡

ረዘም ያለ ጊዜ ወስደው ለምን ይህን አይነት አካሄድ መከተል እንዳለብን የኢትዮጵያን ታሪክ ከስሩ ጀምረው እያጣቀሱ አስረዱኝ፡፡ብቻ አሁን ትዝ እንደሚለኝ የቅርብ ጊዜ የኢትዮጵያ መሪ የጠቀሱት አጼ ካሌብን ነው መሰለኝ፡፡

ጋሼ ሲያወሩ እየሰማሁ እያስመሰልኩ ካርታው ላይ ያደኩባትን አርሲ ለማግኘት በአይኔ ሳማትር ቆየሁ፡፡አርሲ ድሮም ትንሽ ናት በሳቸው ካርታ ያለ አጉሊ መነጽር እርዳታ አትታሰብም፡፡

ኋላ ላይ አንድ ሀሳብ ብልጭ አለልኝ፡፡

“….ለምን የፓርቲያችንን የሥራ አስፈጻሚ አባላት አላዝናናቸውምየሚል …

ተጨማሪ ያንብቡ:  የዓረና መሪዎች በእንደርታ ኲሓ ከተማ በፖሊስ ታሰሩ

ሀሳባቸውን ገታ ሲያደርጉ ጠበኩና ጋሼ ጥሩ ነገር ያነሱት! በቀጣይ ታዲያ ለምን በስራ አስፈጻሚ ደረጃ ሰብሰብ ብለን አንወያይም? ..ሰባት ሰባት ሰው እንምረጥና ሁለተኛውን ስብሰባ እናድርግ ..በዛውም እርስዎም በእኛ ቢሮ ያሁኑን ግሩም ሃሳብ ፕረዘንት አያደርጉልንም?!” አልኳቸው.፡፡

ደነገጡ!

ለመጀመሪያ ጊዜ ኮንፊደንሳቸው ከፊታቸው ላይ ብን ብሎ ሲጠፋ አየሁ፡፡

ከዛ ጋሼ የሞት ሞታቸውን ምን ቢሉ ጥሩ ነው..

ወንድሜ በዛሬ ጊዜ የሚታመን ሰባት ሰው ከየት ይመጣል ብለህ ነው?!”

**

ዛሬ በአሜሪካ የተቋቋመውን የኡአነግ (የኡበር አሽከርካሪዎች ነጻ አውጪ ግንባር ) ፎቶ ሳይ ነው ጋሼ ትዝ ያሉኝ፡፡

እንደውነቱ ከሆነ ለነኚህ ወራዶች በኢትዮጵያ መንግስት ደረጃ መልስ መሰጠቱ አናዶኛል፡፡

ባይሆን እኚህን እንደ ጋሼ እስቲ ለፎቶ የሚሆን ሰባት ሰባት አባላቶቻችሁን ይዛችሁ ኑማለት ብቻ ይበቃ ነበር፡፡

ኢትዮጵያ ታሸንፋለች

መልካም ቀን

Andualem Buketo Geda

https://amharic.zehabesha.com/tplf-terrorist-gropup-other-groups-form-alliance-against-ethiopias-leader/

1 Comment

  1. I enjoyed your article. መቆየት ብዙ ያሠማል።ቅጠሎቹ ዋርካ ለመሆን መመኘታቸው አንጀቴን አልበላው አለ።
    ሐገራችን ታሸንፋለች!!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.