Hiber Radio: ኦጋዴን ውስጥ የ17 አመቷ ልጃገረድ በአገዛዙ ታጣቂዎች 13 ጊዜ መደፈሯን ገለጸች

/

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
የህብር ሬዲዮ ዕሁድ መጋቢት 15 ቀን 2005 ፕሮግራም
<<..ጦርነቱን አሸንፈዋል ወይም ተሸንፈናል ብሎ በቀላሉ መናገር አይቻልም። ሊታዩ የሚገባቸው ብዙ መሰረታዊ ጉዳዮች አሉ። 17 ዓመት ሙሉ በረሃ ውስጥ የነበረው ወታደር ሞራል መውደቅና የሶሻሊስቱ ካምፕ መፍረስ ናቸው ኢትዮጵያን ሰራዊት ራሱን በራሱ ያሸነፉት።አሸናፊዎች ከሆኑ ሻዕቢያም 30 ዓመት ወያኔም 17 ከውስን አካባቢ ሳይወጡ ለምን ቆዩ? ... ቀድሞ ከፍተኛ ወታደራዊ ሹመት ለማግኘት ብሄር የሚባል ነገር ሳይሆን ብቃት ነበር የሚታየው ጄኔራሎቹም ሆኑ የበታች መኮንኖች የተማሩ ነበሩ።ወታደራዊ ሹመት ብሄር እየታየ አይሰጥም...>> ብ/ጄኔራል ውበቱ ጸጋዬ በቅርቡ ያሳተሙትን <<ሁሉም ነገር ወደ ሰሜን ጦር ግንባር >> የተሰኘውን ዕውነተኛ ታሪካዊ መጽሐፋቸውን በተመለከተ ካደረግንላቸው ሁለተኛ ክፍል ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡ)
ትንታኔ የኢትዮጵያ ጦር ከሱማሊያ ዕውነት ይወጣል ወይስ ተጨማሪ ዓለም አቀፍ ድጋፍ ለማግኘት ማስፈራሪ ነው?
የአልሸባብ የተለቀቁ ቦታዎችን መቆጣጠር ይቀጥላል? (በትንታኔው ተካቷል)
የካቶሊኩ አዲሱ ጳጳስና የተከታዮቻቸው አቀባበል
ተጨማሪ ቃለ ምልልስ አለን
ዜናዎቻችን
– እስክንድር ነጋ ያለ ማስረጃ በመታሰሩ በነጻ ሊለቀቅ ይገባል ሲል የጠቅላይ ፍ/ቤት ዳኛ ከዐቃቤ ህግ ጋር መጋጨቱን ተመስገን ደሳለኝ ይፋ አደረገ
– የእስክንድር ይግባኝ ለመጨረሻ ጊዜ ረቡዕ ይታያል ተብሎ ተቀጥሯል
– ኦጋዴን ውስጥ የ17 አመቷ ልጃገረድ በአገዛዙ ታጣቂዎች 13 ጊዜ መደፈሯን ገለጸች
– ሁለት የኦነግ ክፍተኛ ባለስልጣናት እራሳቸውን ከድርጅቱ አገለሉ
– ከመቀሌ የህወሀትን ጉባዔ ምስጢር ያጋለጠው ዘጋቢ አሸባሪነ ተብሎ ማስፈራሪያ እንደደረሰው ገለጸ
ቬጋስን ጨምሮ ከአሜሪካ ለህወሃት ጉባዔ ተወክለው የሄዱ አሉ
– ለኢትዮጵያ ሰራዊት የሰልላሉ የተባሉ የ80 አመት አዛውንት አንገታቸውን ተቀሉ
– የቬጋስ የታክሲ አሽከርካሪዎች የስራ ማቆም አድማ አራተኛ ሳምንቱን ያዘ

ተጨማሪ ያንብቡ:  ብርቱ ምስጢር: የድሮን ጥቃትን ለመከላከል ባለፈው ጊዜ በፍኖተሰላም የደረሰ የድሮን ጥቃት - ተግባር ቁጥር ፩
Share