አሸባሪው ኦነግ ሸኔና የዘር ማጥፋት ተባባሪዎቹ በጓህ ጽዮን ወረዳ ሁለት አማራዎችን በጥይት በመግደል ከ500 በላይ ቤቶችን አቃጥለዋል

ከእነ ሙሉ ንብረት አቃጠሉ፤ ከአምስት ሽህ በላይ አማራዎችን አፈናቅለዋል።
አማራ ሚዲያ ማዕከል
ጥቅምት 23 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ ሸዋ
አሸባሪው ኦነግ ሸኔና የዘር ማጥፋት ተባባሪዎቹ በጓህ ጽዮን ወረዳ ቢስቲኖ ጤና ቀበሌ ልዩ ስሙ ሙግደጤራ በተባለ አካባቢ ሁለት አማራዎችን በጥይት በመግደል ከ500 በላይ ቤቶችን ከእነ ሙሉ ንብረታቸው አቃጥለዋል።
ከጥቃቱ የተረፉ ተጎጅዎች እንዳሉት ከአምስት ሽህ በላይ አማራዎችንም ቤት አልባ አድርገው አፈናቅለዋል።
በሽህ የሚቆጠሩ ተፈናቃዮችም ወደ አካባቢው በርሃ እና ወደ ደራ መጓዛቸው ተሰምቷል።
እስካሁን አንድም የሰብአዊ እርዳታ ያደረሰ የመንግስት አካል የለም ተብሏል።
የኦሮሚያ ክልል የመንግስት አካላትም ከአሁን ቀደምም በንጹሃን ላይም ሆነ በአማራ ሚሊሾች ላይ የሚፈጸመውን ተደጋጋሚ ጥቃት ለማስቆም አለመተባበራቸው ተነግሯል።
ጥቅምት 17 ቀን 2014 ከጠዋቱ 1 ሰዓት ጀምሮ እስከ 5 ሰዓት ድረስ
ሁለት ንጹሃንን በመግደል አምስት መቶ ቤት ካወደሙ በኋላ ነው የጸጥታ አካላት የደረሱት ብለዋል ተጎጅዎቹ፤ ብዙ ሳይቆዩም መመለሳቸውን ለአሚማ ምንጮች ተናግረዋል።
የተገደሉትም:_
1) ኩራዝ ጤናው
የ35 ዓመት ጎልማሳ እና
2) ወ/ሮ ቦጋሉ መንግስቱ
የ65 ዓመት አቅመ ደካማ እናት ሁለቱም በጥይት ተገድለዋል።
የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን በጓህ ጽዮን ወረዳ ጨለንቆ እና ከራቲ የተባሉ አካባቢዎችን እንደ ምሽግ በመጠቀም
በአማራ ላይ የለየለት ማንነት ተኮር ጥቃት መፈጸሙን ቀጥሏል።
የመንግስት አካላትም እነዚህ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች ወደ ጨለንቆና ከራቲ መግባታቸውን እያወቀ አንድም እርምጃ ለመውሰድ አልደፈረም ሲሉ ወቅሰዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ:  Hiber Radio: ከመተከል የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ዳግም ከባህር ዳር ሊፈናቀሉ መሆኑን ተቃወሙ፣ዶ/ር አብይ የጠ/ሚኒስትር ስልጣን ገደብ ይኑረው ማለታቸው በኢህአዲግ ጎራ መደናገጥ ፈጠረ፣የኦሮሞ ሕዝብ ተቃውሞ ያቀረበበት የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን በአዲሱ መከላከያ ሚኒስትር ተጨማሪ አስር ዓመት ተፈቀደለት፣ሀይለማርያም ደሳለኝ የደ/ሱዳን መሪዎች ስልጣን ይልቀቁ ማለታቸው ለመስቀለኛጥያቄ ዳረጋቸው፣የሶማሌ ሕዝብ ተቃውሞ፣ኢትዮጵያዊው የሁበር አሽከርካሪ መቀጣት ሌሎችም ዜናዎችም አሉን

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.