የሚኒስትሮች ምክር ቤት በመላ ሀገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ

አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተከለከሉ ተግባራትና ግዴታዎች..

ሁሉም ሰው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ በአዋጁ መሰረት የሚያወጣቸውን መመሪያዎችና የሚሰጣቸውን ትዕዛዞች የመቀበል ግዴታ አለበት፤የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዙን እንቅስቃሴና የአዋጁን ዓላማ የሚቃረን፣ የሚቃወምና ለሽብር ቡድኖች ዓላማ መሳካት አስተዋፅዖ የሚያደርግ፣ የሽብር ቡድኖችን የሚያበረታታ፣ ሰላማዊ ዜጎችን የሚያሸብር ንግግር በማንኛውም መንገድ ማድረግ ወይም ማሰራጨት የተከለከለ ነው፤

  • በየትኛውም መንገድ፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለሽብር ቡድኖች የገንዘብ፣ የመረጃ፣ የቁስም ሆነ የሞራል ድጋፍ ማድረግ የተከለከለ ነው፤
  • የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዙ በተዋረድ ውክልና ከሰጣቸው አካላት ፈቃድ ውጭ ማንኛውንም የአደባባይ ስብሰባ ወይም ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ የተከለከለ ነው፤
  • ከመከላከያ፣ ከፌዴራል ፖሊስ ወይም ሌሎች ፈቃድ ከሚሰጣቸው የፀጥታ አካላት ወይም ከእነዚህ አካላት እውቅናና ፈቃድ ውጭ ማናቸውንም የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፤
  • በከተሞች አካባቢ የነዋሪ መታወቂያ፣ የመንጃ ፈቃድ፣ የሰራተኛ መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይም ከነዚህ ተመጣጣኝ የሆነ መታወቂያ ሳይዙ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፤
  • ማንኛውም ወሳኝ በሆነ የአገልግሎት ዘርፍም ሆነ በምርት ሂደት ላይ የስራ ማስተጓጎል ወይም የኢኮኖሚ አሻጥር መፈፀም የተከለከለ ነው፤
  • የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈፃፀም ሰበብ በማድረግ የግል ጥቅም ለማግኘት ስልጣንን አላግባብ መጠቀም፣ ምክንያታዊ የሆነ ጥርጣሬ ሳይኖር ሆን ብሎ ዜጎችን ማሰር ወይም መሰል እርምጃ መውሰድ የተከለከለ ነው፤
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከዛሬ ጀምሮ የሚተገበር ሲሆን ለቀጣዮቹ ስድስት ወራት እንደሚቆይ በተሰጠው መግለጫ ላይ ተብራርቷል።
252343379 2127044260780244 3572233096419458492 n251809082 2127044320780238 3091729197102172678 n251825332 2127044370780233 7016640738093975035 n251163004 2127044404113563 3848447585929352658 n252712721 2127044454113558 4342780251360003256 n252106335 2127044487446888 5295591317610891760 n
= = = = =

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.