ነገር እንደ እንጀራ እየራበን አስከ መች ? – ማላጂ

ሠሞኑን ባዕዳን ቅጥረኛ ወታደሮች በወሎ ግንባር መታየታቸዉ አንደ አዲስ እየተነገረ እሰማን ነዉ ፡፡

ይሁንና ይህ የአገር ዉስጥ ጠላት ከዉጭ ጠላት ጋር ህብረት ፈጥሮ አገርን እና ህዝብን የማዳካም የሴራ ወጥመድ ስራ ላይ ካዋለ የ፶ ዓመት ዘመን የጥፋት እና ሞት ጌኛ ነዉ ፡፡

በሁሉም ኢትዮጵያ የነጻነት ትግል የዉስጥ እና የዉጭ ጠላቶች ቅንጅት እንደነበር ከኢጣሊ ወረራ አስከ ካራ ማራ ከደደቢት አስከ አፋቤት የተደረጉ ጦርነቶች ዋቢ ምልክቶች ናቸዉ ፡፡

በሰማሊያ ጦርነት የኢትዮጵያ መታወቂያ ይዘዉ ለዚያዳባሪ የታላቋ ሶማሊያ መስፋፋት የዕናታቸዉን ጡት ነካሽ የነበሩት እና የሆኑነት የዛሬወች “የትግሬ ወራሪዎች ” እና የዉጭ ፤የዉስጥ ግብረ አበሮች እንደነበሩ ይታወቃል፡፡

በየትኛዉም የአገሪቷ ክፍል ለዓመታት የአገሪቷን አንድነት ፤የህዝቡን ደህንነት ለማናጋት የሚሰሩት በቀለም እና በስም ካልሆነ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ያልሆኑ ማለት ከንቱ መዘናጋት ነዉ ፡፡

የባዕድ ወረራ በጠላት እና የባዕድ ተላላኪ ወዳጂ መሳይ አስመሳይ ለባዕድ ያደሩ የጠላት ወዳጂ ባዕዳን አምላኪዎች እና ቅጥረኞች ወዳጂ ወይም ወገን ሊሰኙ የሚችሉበት የየትኛዉም ዘመን አጋጣሚ የለም ፡፡

አንድን አገር እንደጠላት ፤አንድን አገር እንደባዕድ (ሌላ) ለሚፈርጂ እና ኢትዮጵያዊነትን አጥብቆ ለማፍረስ ለምዕተ ዓመት ለሚሰራ በዕድነት እና ጠላትነት ከዚህ በላይ ማሳያዉ ምን ይሆናል፡፡

ሁለት እና ሶስት የዜግነት ወረቀት ይዞ ኢትዮጵያን ለመሸጥ የሚያስማማ ….ኢትዮጵያዊ ነዉ እያሉ መድከም የ፳፯ ዓመት የኋላ ጨለማ ዘመን ብርሀን እና ፍስኃ አድርጎ ለማሳየት መዛከር ነዉ ፡፡

ድርም ሆነ ዛሬ አገራችን የምትጎሳቆለዉ በስም እንጂ በተግባር ሠባዊነትም ሆነ ኢትዮጵያዊነት ስሜት በሌላቸዉ የአገር ዉስጥ እንክርዳዶች እንጅ በዉጭ ዜጎች /ጠላቶች አይደለም ፤አይሆንም ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኒኪሌር ጣቢያው ጥቃት ሥጋትና የኢዜማ ድንገተኛ ቁጣ ወዴት? | Hiber Radio Special Program |

እናም ሠዉ ሆይ ጊዜ አናጥፋ ፤በከንቱ አንልፋ …… አናቀላፋ ጠላት እና ወዳጂ በቀለም እና ስም አይለይም ፡፡

በአገር እና ህዝብ መከራ የሚደሰት ፣የሚሳለቅ እና የሚኩራራ ምንም ይሁን ምን ወዳጂ እና ወገን ግን አይሆንም እና ከዕባብ ዕንቁላል ዕርግብ ጠብቁ ለምትሉን ዕባካችሁ ዕዉነት ባትናገሩ ሀሰት በሉ ፡፡

“ጠላትም ምንጊዜም ጠላት ነዉ……አስቀድሞ ማለት ……” ብለዉ ነበር ያን ጊዜ በጊዜዉ ጊዜ ….

 

ማላጂ

“አንድነት ኃይል ነዉ”

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share