አሁንም ደሴና አካባቢዋ በፀጥታ ሃይላችን ስር ነው ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡

አሁንም ከፍተኛ መረጋጋት ያስፈልጋል። የህወሀትን የጥፋት ግስጋሴ ለመግታት ከጦርነቱ ጥንካሬ በላይ ሊኖረን የሚገባው መረጋጋት ነው። በጦርነቱማ ህወሀት እየታሸ ነው። እውነት ለመናገር ሁኔታው ለወሬም አይመችም። የሚቀጠቀጡት፣ እንደቅጥል የሚረግፉት እነሱ ሆነው መረጋጋት እያቃተን፣ በወሬ ተረብሸን ለጥፋት ግስጋሴአቸው መንገዱን የምንጠርግላቸው እኛው መሆናችን ነው። የጦርነቱን ድላችንን በሽብር ወሬና በነጭ ፕሮፖጋንዳ እያበላሸን ዋጋ እየከፈልን እስከመቼ እንደምንዘልቅ አላውቅም።

ነገሮች በየግማሽ ሰዓቱ በሚቀያየርበት የደሴው ጦርነት የጠላትን የውሸት የድል ዜና አብረን የምናዳምቅበትና የምናጯጯህበት ሁኔታ ለህወሀት ከውጊያ በላይ እየጠቀመው መሆኑ እስከአሁን ያልተገለጠልን ቁጥራችን የትየለሌ ነው። የደሴው የሰሞኑ ክስተት ከትላንት ስህተታችን አለመማራችን፣ በቀጣይም በስህተት ላይ ስህተት እየደረብን ሀገራችንን በስጋት ውስጥ እንድትሰነብት የምናደርጋት እንደሚሆን ይታየኛል። ህወሀት በጦርነቱ ተሸንፏል። በፕሮፖጋንዳው ግን አሸንፏል። ጦር ከፈታው ወሬ የረታው ስለሚበልጥ ህወሀት እየሞተም በምላሱ እድሜው ለጊዜውም ቢሆን እንዲረዝምለት አድርጎታል።
ደሴን ህወሀት ተቆጣጥሯል የሚለው ወሬ ከ15ቀናት በፊትም ነበር። ሰሞኑን በየዕለቱ ይኸው ዜና በሰበር መልክ ተመላልሶ እየተነገረን ነው። ደብረጺዮንም ጦርነቱ አልቋል ብሎ ፊሽካ ከነፋ ሶስት ቀናት ተቆጥረዋል። የእነሱን የውሸት ዜናቸዎች እየተቀባበሉ ከዓለም ጫፍ እስከጫፍ የሚያስተጋቡላቸው ግዙፍ ሚዲያዎች ሰሞኑንም ስራቸውን አልዘነጉትም። በእርግጥም ደሴ በማን እጅ ናት? በህወሀት ቁጥጥር ስር ብትሆንስ ምን መደረግ አለበት? የደሴ መያዝ የዓለም መጨረሻ ነውን?
ጦርነት ተለዋዋጭ ባህሪ ስላለው በየሰዓቱ ነገሮች መቀያየራቸው አይቀርም። ዛሬ ብቻ ደሴ ላይ የተከሰቱት ነገሮች ለሶስት ጊዜያት ተቀያይረዋል። አሁን ያለበት ሁኔታም ዘላቂ ላይሆን ይችላል። ህወሀቶች የፕሮፖጋንዳ ታክቲኩ ላይ የተካኑ በመሆናቸው ብልጭ ብለው ለቅጽበት በታዩባቸው ቦታዎች ላይ ሳይቀር የድል ብስራት እያወጁ ደጋፊዎቻቸውን የሚያስፈነጥዙበትና ዓለምን የሚያደናግሩበት ሁኔታዎችን በተደጋጋሚ ታዝበናል። ደሴን ተቆጣጥረናል የሚል በፎቶግራፍ የታጀበ ሰበር ዜና ስንሰማ መቆየታችን ስናስብ እነሱ በፕሮፖጋንዳው ላይ የቱን ያህል ጥግ እንደሚሄዱ እንረዳለን።
እኔ ባለኝ መረጃ ደሴ በኢትዮጵያ ሃይሎች ቁጥጥር ስር ናት። ከቀትር በኋላ ህወሀት በተወሰነ የሰው ሃይል በሶስት የከተማዋ መግቢያ አከባቢዎች ሰብሮ ገብቶ ነበር። ወደመሃል ሳይዘልቅ በከተማዋ ዳርቻ ለሁለት ሰዓታት አድፍጦ የቆየው ይህ ሃይል ደሴን ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር ተልዕኮ ለተሰጠውና ከፍተኛ ቁጥር ላለው የህወሀትን ሰራዊት መንገድ የማመቻቸት ስራ እንዲያስፈጽም የተላከ ነበር። ይሁንና ዋናው የህወሀት ሃይል ወደደሴ ሲገሰግስ መሃል ላይ በኢትዮጵያ አየር ሃይል ተመቶ ከታሰበለት ቦታ ሳይደርስ ቀርቷል። ደሴን የመቆጣጠር ተልዕኮ ያነገበው ዋናው ሃይል መንገድ ላይ ቀልጦ መቅረቱ እንደተሰማ በአስተኛ ቁጥር በሶስት የደሴ መግቢያ መንደሮች የገባው ሃይል ወደ ኋላ በማፈግፈግ ከደሴ ዳርቻ አከባበቢዎች ለቆ ወጥቷል። ይህ ክስተት በተጠና መንገድ የህወሀት ሰራዊት ደሴን እንደተቆጣጠረ ተደርጎ ተራገበ። ሁኔታውን ያዩ የአከባቢው ነዋሪዎችም ደሴ በህወሀት እጅ ወድቃለች ብለው ሸሹ፣ ወሬውንም ሌላው ህዝብ ዘንድ እንዲደርስ አደረጉ። ከሶስት ሰዓት ያነሰ ቆይታ ያደረገው የህወሀት ሃይል አሁን በቦታው የለም።
ይህ ክስተት ሊቀየር ይችላል። በየትኛውም ሰዓት ሌላ ነገር እንደሚሆን መጠበቁ ስህተት አይደለም። በኢትዮጵያ ሃይሎች እጅ ያለችውን ደሴን ለመቆጣጠር ህወሀት ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ሃይሉን በደሴ ዙሪያ አስገብቷል። ውጊያው በብርቱ ሁኔታ ቀጥሏል። ለአሁን ያለው መረጃ ይህንን ይመስላል። በመንግስት በኩል የተሰጠው መግለጪያም ደሴ በኢትዮጵያ ሃይሎች እጅ እንደምትገኝ የሚያረጋግጥ ነው። ምናልባት ሌሊቱን ነገሮች ይለዋወጡና ተቃራኒ ሁኔታዎች ይከሰቱ ይሆናል። ወይም ህወሀት እየቀመሰ ያለው ዱላ ከሚችለው በላይ ሆኖበት ሊያፈገፍግ ይችላል ብሎ ተስፋ ማድረጉም አይከፋም።
ደሴን ህወሀት ቢቆጣጠራትስ? የዓለም ፍጻሜ ነውን? በእርግጥ ደሴ ወሳኝና ቁልፍ ከተማ ናት። ህወሀቶች እጅ መውደቋ ከፍተኛ የሆነ ፖለቲካዊም ሆነ ስነልቦናዊ ኪሳራ የሚያደርስ ነው። ግን የዓለም መጨረሻ አይሆንም። ደሴን እነዚያ ክፉዎች እንዳይቆጣጠሯት የሚያስፈልገው መስዋእትነት ሁሉ መከፈል ይገባል። ካልተሳካም ክፍተትን ደፍኖ፣ ስህተትን አርሞ፣ ሀገር የማዳን የህልውና ትግሉን በአዲስ መንፈስና ሀገራዊ ተልዕኮ ማፋፋም ይኖርብናል። ምርጫ የለንም። ኢትዮጵያን ማጣት ለምርጫ የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም። ከኢትዮጵያ ሌላ የእኛ ነው ብለን የምንሄድበት ሀገር፣ የምንሞትለት ማንነት የለንም። አኩርፈን የምንቆዝምበት፣ ተስፋ ቆርጠን የምንቆምበት ጉዳይ አይደለም። ደሴ ይቅርና አዲስ አበባ ቢደርሱ እንኳን እጅ የምንሰጥበት ሊሆን አይገባም። ሀገር እኮ ናት?! ኢትዮጵያ!! ቸር ወሬ ያሰማን።

Mesay Mekonnen

———————–

ተጨማሪ ያንብቡ:  የ ዶ/ር አቢይ ኢትዮጵያ ወይም ሞት ጥሪ ክፍል ፪ (ከአባዊርቱ)

250589718 4977072482312140 2605705694691873147 nበሃገር መከላከያ ሰራዊት እየተመራ ወራሪውን የሽብር ቡድንና ያሰለፈውን መንጋ እየመከተ የሚገኘው መላው የፀጥታ ሃይላችን በፀረ ማጥቃት እርምጃው ቀጥሏል። በተለይ ደሴን ለመያዝ አሰፍስፎ የመጣውን ወራሪ ሃይል በመመከት አኩሪ ገድልን እየፈፀመ ይገኛ

ሌሊቱን ሙሉ ከተለያዩ ግንባሮች ጠጋግኖ በማሰባሰብ ደሴን ለመያዝ በኩታበር; ቦሩ ስላሴና በሃይቅ መስመር የመጣውን ወራሪ መንጋ የፀጥታ ሃይላችን በታላቅ ጀብዱ መክቶታል። አሁንም ደሴና አካባቢዋ በፀጥታ ሃይላችን ስር ነው። ቀደም ብለውም ስደተኛ በመምሰልና የመከላከያ ሃይላችንን ወታደራዊ አልባሳት ለብሰው ሊዘርፉ የሞከሩ ቡድኖችና በከተማዋ የሚኖሩ ለጥፋት ሃይሉ የሚሰሩ ባንዳዎች ከትናንት ጀምሮ የጁንታውን አላማ ለማስፈፀም ከግንባር ውጊያው ባልተናነሰ ሲሰሩ ውለዋል።
የደሴ ወጣቶችና መላው የፀጥታ ሃላችንም ይህንን ሃይል በተደራጀ መንገድ እየመከቱት ይገኛሉ። የከተማዋ ወጣቶችም በጀመሩት መንገድ ከተማቸውን ከባንዳ የመጠበቅ ተግባራቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል።
ያለውን ሃይል ሁሉ አሰባስቦ በዚሁ ግንባር ያመጣው የሽብር ቡድኑ በጦር ግንባር ያቃተውን በወሬ ለማግኘት አሁንም መፍጨርጨሩን ቀጥሏል።
አንዳንድ የውጪ መገናኛ ብዙሃንም የሽብር ቡድኑን የሃሰት ፕሮፖጋንዳ እያስተጋቡ ይገኛሉ። በወሬ የሚያዝ ከተማ የለም ሊኖርም አይችልም ብሎ መላው ህዝብ በደሴ ከተማ ዙሪያ ለሚነሳው አሉባልታ ጆሮ ሳይሰጥ አሁንም የሃገሩን ህልውና ለማስከበር የሚያደርገውን ተጋድሎ ቀጥሏል። በዚሁ አጋጣሚ በተለይ ያልተጣራ መረጃን በመያዝ ህዝብን ለማሸበር እየተንቀሳቀሱ የሚገኙና የሽብር ቡድኑ መጠቀሚያ የሆኑ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ መንግስት ያሳስባል።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
——————————————————
ደሴ አልተያዘም አልተያዘም አራት ነጥብ። ነገርግን እስከዚች ቅፅበት በሦስት ግምባር ውጊያ እየተደረገ ነው። ኔትወርክ የጠፋው በመንግስት ትእዛዝ ለልዩ ኦፕሬሽን ነው አለቀ። ማመን ያለማመን የራስህ ጉዳይ ነው። የወያኔን የመግለጫ ጋጋታ አራጋቢ መሆን፣ ፊት ተሰልፈው እየተዋደቁ ያሉትን ጀግኖች ዋጋ ማሳጣት ነው።
የሆነውን በአጭሩ ላስረዳ፦ ዛሬ ቀትር ላይ የተወሰነ የጁንታው ኃይል በ3 የከተማዋ መግቢያ አካባቢ ሰብረው ገብተው ነበር። ወደ መሐል ከተማው ሳይገቡ በከተማዋ ዳርቻ አድፍጠው ቆዩ። ዋና ዓላማቸው ከኋላ እየተገተለተለ ለሚመጣው ኃይል ማመቻቸት ነበር። ነገርግን ዋናው ኃይል ወደ ደሴ ሲመጣ በጄት ተመትቶ ተበታተነ።
መጀመሪያ ወደ ደሴ ተልዕኮ ይዘው አድፍጠው የነበሩት ከኋላ ያለው ደጀናቸው እንደተመታ ሲሰሙ ወደኋላ አፈግፍገዋል። ይህ ሁኔታ ለሕወሓት ፕሮፓጋንዳ የተመቸ ብቻ ሳይሆን፣ ሁኔታውን ያዩ የደሴ ከተማ ኗሪዎች ደሴ በህወሓት እጅ ወድቃለች በማለት ሸሹ፣ ሌላው ስልክ እየደወሉ አይተናቸዋል እየገቡ ናቸው እያሉ ለወዳጅ ዘመድ ተናገሩ፣ ወሬው ወደ ህዝብ ተሠራጨ። ውዥንብሩ የተፈጠረው በዚህ ምክንያት ነው። ነገርግን የጁንታው ሃይሎች ቆይታቸው ከ3 ሰአት አይበልጥም ነበር።
አሁንም በሦስት ግምባር ውጊያው ቀጥሏል፤ ሌሊት የሚፈጠረው አይታወቅም የምነግራችሁ አሁናዊ መረጃ ነው። ይልቅስ የውሸት ፕሮፖጋንዳ በማመከን፣ ህዝብ በማረጋጋት፣ እየተዋደቁ ላሉት ደጀን በመሆን የምንችለውን እናግዝ። ያለነው ጦርነት ላይ ነው። ከማሸነፍ ውጪ ምርጫ የለንም።

Seyoum Argaw

————————————————————–

ተጨማሪ ያንብቡ:  የዛሬው የሊቃነ ጳጳሳት ምልዓተ ጉባዔ ውሎ - ነገሰ ተፋረደኝ
በሃገር መከላከያ ሰራዊት እየተመራ ወራሪውን የሽብር ቡድንና ያሰለፈውን መንጋ እየመከተ የሚገኘው መላው የፀጥታ ሃይላችን በፀረ ማጥቃት እርምጃው መቀጠሉንም አስታውቋል።
በተለይ ደሴን ለመያዝ አሰፍስፎ የመጣውን ወራሪ ሃይል በመመከት አኩሪ ገድልን እየፈፀመ ይገኛል ሲልም አክሏል።
እንደ አገልግሎቱ መግለጫ ሌሊቱን ሙሉ ከተለያዩ ግንባሮች ጠጋግኖ በማሰባሰብ ደሴን ለመያዝ በኩታበር, ቦሩ ስላሴና በሃይቅ መስመር የመጣውን ወራሪ መንጋ የፀጥታ ሃይላችን በታላቅ ጀብዱ መክቶታል።
አሁንም ደሴና አካባቢዋ በፀጥታ ሃይላችን ስር ነው ያለው የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ቀደም ብለውም ስደተኛ በመምሰልና የመከላከያ ሃይላችንን ወታደራዊ አልባሳት ለብሰው ሊዘርፉ የሞከሩ ቡድኖችና በከተማዋ የሚኖሩ ለጥፋት ሃይሉ የሚሰሩ ባንዳዎች ከትናንት ጀምሮ የጁንታውን አላማ ለማስፈፀም ከግንባር ውጊያው ባልተናነሰ ሲሰሩ ውለዋል ብሏል።
ያለውን ሃይል ሁሉ አሰባስቦ በዚሁ ግንባር ያመጣው የሽብር ቡድኑ በጦር ግንባር ያቃተውን በወሬ ለማግኘት አሁንም መፍጨርጨሩን እንደቀጠለም ገልፀዋል።
አንዳንድ የውጪ መገናኛ ብዙሃንም የሽብር ቡድኑን የሃሰት ፕሮፖጋንዳ እያስተጋቡ ይገኛሉ ሲልም አክሏል።
እንደ መንግስት መግለጫ በወሬ የሚያዝ ከተማ የለም ሊኖርም አይችልም ብሎ መላው ህዝብ በደሴ ከተማ ዙሪያ ለሚነሳው አሉባልታ ጆሮ ሳይሰጥ አሁንም የሃገሩን ህልውና ለማስከበር የሚያደርገውን ተጋድሎ እንደቀጠለ ነው።
በዚሁ አጋጣሚ በተለይ ያልተጣራ መረጃን በመያዝ ህዝብን ለማሸበር እየተንቀሳቀሱ የሚገኙና የሽብር ቡድኑ መጠቀሚያ የሆኑ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ መንግስት አሳስቧል።

—————————

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.