ቴድሮስ አድኃኖም ለቀጣይ ዙር ብቸኛ ተወዳዳሪ ብቸኛ እጩ የዓለም ጤና ድርጅት በመግለጫው ዐስታውቋል

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ኃላፊው ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም ለቀጣይ ዙር ብቸኛ ተወዳዳሪ መሆናቸውን ዛሬ ዐስታወቀ። ዶ/ር ቴድሮስ በማመልከቻ ጽሑፋቸው ኮቪድ-19 ወረርሺኝ፦ «ዓለምን ማንኮታኮቱን» ገልጠው በሁለተኛ ዙር የሥልጣን ዘመናቸው ዓለማችንን ለመሰል ወረርሺኝ «የምር ዝግጁ» መሆኗን ማረጋገጥ ፍላጎታቸው መሆኑን ጠቁመዋል ሲል የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት (AFP) ዘግቧል። ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም የዓለም የጤን ድርጅት ዋና ኃላፊ ሆነው የተመረጡት በጎርጎሪዮሱ 2017 ነበር። የአምስት ዓመት የሥልጣን ዘመናቸውም ባለፈው ነሐሴ ወር ውስጥ ነው የተገባደደው። «መስከረም 13 ቀን፣ 2014 ዓም በነበረው ቀነ-ገደብ በአባል ሃገራት የቀረበው እጩ አንድ ብቻ ነበር፤ ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም ገብረእየሱስ» ሲል የዓለም ጤና ድርጅት በመግለጫው ዐስታውቋል፤ በ28 ሃገራት እጩ ሆነው መቅረባቸውንም ዓለም አቀፉ ድርጅት ይፋ አድርጓል።

ከሰሜኑ የኢትዮጵያ ጦርነት ጋር በተያያዘ በርካታ ኢትዮጵያውያን ዶ/ር ቴድሮስ እጃቸው አለበት ሲሉ ይከሳሉ። በቅርቡ ይፋ በሆነ የድምፅ ቅጂ ውስጥ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ኃላፊ የነበሩ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኃላፊዎች፦ የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም ከሌሎች ባለሥልጣናት ጋር በመሆን በኢትዮጵያ የተመድ ኃላፊ እንዲነሱ ግፊት እያደረጉ ነው ሲሉም በቃለ ምልልሱ ተደምጧል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ በኢትዮጵያ የዓለም የፍልሰተኞች ጉዳይ ድርጅት (IOM) ዋና ኃላፊ ማውሪን አቺንግ ከሌላ የተመድ ባለሥልጣን ጋር በመሆን ስለ ኢትዮጵያ በስፋት በመዘገብ ከሚታወቀው ካናዳዊው ደራሲና ጸሐፊ ጄፍ ፒርስ ጋር ያደረጉት ረዘም ያለ ቃለ ምልልስ በማኅበራዊ የመገናኛ አውታሮች ሰሞኑን ሲንሸራሸር ቆይቷል።

ዶ/ር ቴድሮስ ኮቪድ-19 ወረርሺኝ ዓለምን ባዳረሰበት ወቅት ይበልጥ ታውቀዋል። የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ኃላፊው ለቻይና ያደላሉ የወረርሺኙን መነሻ በማድበስበስም «የቤጂንግ አሻንጉሊት ናቸው» በሚል ሀገራቸው ከዓለም አቀፉ ድርጅት እንድትወጣ አዘው ነበር። የኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ውስጥ የኤቦላ ተሐዋሲን እንዲዋጉ የላኳቸው ሠራተኞቻቸው አስገድዶ መድፈር እና የወሲብ ጥቃት ፈጽመዋል የሚል ዘገባ መውጣቱም ለብርቱ ሒስ ዳርጓቸዋል። እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር ከ2018 እስከ 2020 ድረስ ባሉት ጊዜያት 21 የዓለም ጤና ድርጅት ሠራተኞች የአስገድዶ መድፈር እና የወሲብ ጥቃት መፈጸማቸው እንደተገለጠ የፈረንሳይ የዜና አገልግሎት (AFP) ዘግቧል። ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖምን የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ዋና ኃላፊ ሆነው ዳግም እንዲመረጡ የእጩነት ድጋፍ ከሰጡ ሃገራት መካከል 38 የአውሮጳ ሃገራት ይገኙበታል። ከአፍሪቃ ኬንያ እና ሩዋንዳ ድጋፋቸውን ሠጥተዋቸዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና አንዳርጋቸው ጽጌ የፊታችን እሁድ በቨርጂኒያ የሕዝብን ጥያቄ ይመልሳሉ

DW

1 Comment

  1. ምን አይነት ነገር ነው ይህ ሰው እድሜ ልኩን ሲገዘግዘን ፈረንጂን እያታለለ ኢትዮጵያ ላይ ሲያዘምት የኖረ ባንዳ መቼ ነው በቃህ የሚባለው ይሄ ዶክተር ፕሮፌሰር ብላችሁ ካልጠራችሁኘ ሙቼ እገኛለሁ የሚለው አንድን ቀጣፊ ማስቆመ አቃተው? አማርኛ ተጠይቆ ሲመልስ ቋንቋ እንደጠፋዉ ሁሉ ካልደባለቀ የማያወራው ወይ ሰብስብ ብሎ ወይ በተናጥል አንድን ነብሰ ገዳይ ለፍርድ ማቆም ቢሳነው ዳግም አሁን ያለበት ቦታ ሁኖ አገርን ጤና እንዳይነሳ ማቆም ያስቻለ ምሁር ምሁር አልለውም ትግሬ ቴድሮስ አዳኖምን ምሁርና ጀግና ብሎ መጥራት ይችላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share