የኢትዮጵያ አየር ኃይል ማይጠብሪ የሚገኘውን የአሸባሪውን ሕወሓት ማዕከል መታ

247730959 4324872084276274 8587896513367045640 n

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ዛሬ እሁድ በትግራይ ክልል «ማይጠምሪ» እና « አድዋ » አካባቢ የሚገኙ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ግንባር (ሕወሓት) ወታደራዊ ይዞታዎችን በአየር ማጥቃቱን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች አገልግሎት ዐስታወቀ። የጦር ኃይሉ ዛሬ ረፋዱን «በማይጠምሪ የሚገኝ የወታደራዊ ማሰልጠኛ እና የሰው ኃይል ማደራጃ ይዞታዎች በአየር ተመቷል» ብሏል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቀጥሎ ባወጣው መግለጫው ደግሞ «ዐድዋ አካባቢ የሚገኘው፣ የጠላት ወታደራዊ ትጥቅ እና ወታደራዊ አልባሳትን አመሳስሎ የሚያመርትበት ማዕከል በአየር ድብደባ ከጥቅም ውጭ ሆኗል።» ብሏል።በማይጠምሪ በሚገኘው የወታደራዊ ማሰልጠኛ እና የከባድ ጦር መሣርያዎች ማከማቻ ላይ የተሳካ የአየር ጥቃት መወሰዱን ላረጋጋጥላችሁ እችላለሁ ።» ሲሉ የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚንስትሩ ለገሰ ቱሉ ለሮይተርስ የዜና ወኪል ተናግረዋል።
የህወሃት ቃል አቃባይ ጌታቸው ረዳ የጥቃቱን መፈጸም ለሮይተርስ አረጋግጠዋል። «ጥቃቱ በአንድ የገጠር ሆስፒታል አቅራቢያ ተፈጽሟል።» ብለዋል። በዐድዋ በተፈጸመው ጥቃት «ቀደም ሲል በኢትዮጵያ እና የኤርትራ ወታደሮች ውድመት ደርሶበት የነበረው እና ጥቂት ተርፎ የነበረው የአልሜዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ መመታቱን » በቲውተር ባሰፈሩት መልዕክት አረጋግጠዋል።
በሺዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያን ስደተኞች የሚገኙባቸው የማይ አኒ እና አዲ ሃሩሽ የመጠለያ ጣብያዎች በማይጠምሪ አቅራቢያ ይገኛሉ። እንደ ኮሚኒኬሽን ሚንስትሩ ለገሰ ቱሉ የመጠለያ ጣብያዎቹ ለአየር ጥቃቱ ተጋላጭ እንዳልነበሩ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ አስተዳደር እና የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ ኮሚሽነር የመጠለያ ጣብያዎቹን ደህንነት በተመለከተ ላቀረበላቸው ጥያቄ ወዲያውኑ ምላሽ እንዳልሰጡ ሮይተርስ የዜና ምንጩ ጠቅሷል።
DW

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.