የሱዳን ምክር-ቤት ፕሬዝዳንት ሌ/ ጀኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን ሰባት የህግ መንግስት አንቀጾች መታገዳቸውን አስታወቁ

248689409 2120374148113922 1028204322470136669 n

የሱዳን የሽግግር ምክር-ቤት ፕሬዝዳንት ሌ/ ጀኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን ዛሬ በሰጡት መግለጫ በህገመንግስቱ ውስጥ የሚገኙ 7 አንቀጾች መታገዳቸውንና የተለያዩ ውሳኔዎችን ማስተላለፋቸውን አስታውቀዋል።

የታገዱት የህገ መንግስቱ አንቀጾችም ከዚህ በታች ያሉት ናቸው፤
1. አንቀፅ 11፦ የሉዓላዊ ምክር ቤት መቋቋም እና ሲቪሎችና ወታደሮች ስልጣኑ በጋራ እንደሚጋሩየሚገልጸው፤
2. አንቀፅ 12፦ የሉዓላዊ ምክር ቤት ተግባር እና ሀላፊነት፣ እዚሁ አንቀፅ ላይ አስቸኳይ ጊዜ ማወጅ የጠቅላይ ሚንስትሩ ስልጣን መሆኑን የሚገልጸው፤
3. አንቀፅ 15፦ የሚንስትሮች ምክር ቤት በዲሞክራሲያዊ ለውጥ አብዮት በኩል እንደሚሰየሙ የሚጠቅሰው፤
4. አንቀፅ 16 የሚንስትሮች ምክር ቤት ተግባር እና ሀላፊነትን የሚደነግገው፤
5. አንቀፅ 24/3፦ 67 በመቶ የሚሆነው የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ከለውጡ ሀይል እንደሚሰየም የሚደነግገው፤
6. አንቀፅ 71፦ ህገመንግስቱ የበላይ ህጎች መሆኑን የሚደነግገው አንቀጽ፤
እና
7. አንቀፅ 72፦ ወታደራዊ ካውንስሉ በሉዓላዊ ምክር ቤቱ ውሳኔ እንድሚበተን የሚደነግገው አንቀጽ መሆኑን አስታውቀዋል።
በተጨማሪም የሱዳን የሽግግር ምክር-ቤት ፕሬዝዳንት ጀኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን ሱዳን ያለችበት ሁኔታ አስቸጋሪ በመሆኑና ሀገሪቱ በደህንነት ስጋት ውስጥ የገባች ስለሆነ በሚል የተለያዩ ውሳኔዎችነ አስተላልፈዋል።
መከላከያ ሰራዊቱ ሀገር እና ህዝብ የመጠበቅ ሀላፊነት የተጣለበት መሆኑን በመግለፅ የሚከተሉትን ውሳኔዎች ማስተላለፋቸውም ተገልጿል።
1. በመላው ሱዳን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ፣
2. በህገመንግስቱ እና በጁባ የሰላም ስምምነት ሰነዶች መስረት ስራዎች እንደሚፈጸሙ፣
3. በህገመንግስቱ መሰረት ዓለም አቀፍ ስምምነት የተደረሰባቸው ጉዳዮች እንደሚቀጥሉ፣
4. ሉዓላዊ የሽግግር ምክር-ቤት መበተኑና የተሰጡት ሀላፊነቶች በሙሉ መሰረዛቸው፣
5. የሚንስትሮች ምክር-ቤት መበተኑ፣
6. የክልል አስተዳዳሪዎች በሙሉ ከስልጣናቸው መነሳታቸው፣
7. ሚንስትሮች እና ሚንስትር ዴታዎች ከሃላፊነት መነሳታቸው፣
8. በክልል እና በሚንስቴር መስሪያ ቤቶች በዳይሬክተር ደረጃ የሚገኙ ሀላፊዎች ስራዎችን እንዲያከናውኑ መወከላቸው፣
9. የሀብት አስመላሽ ኮሚቴ ስራ ታግዷል የሚሉት ናቸው
(ኢ ፕ ድ)

248306853 3073233506336738 6589789644667253863 n

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.