የአማራ ክልላዊ መንግስት አሳዛኝና አሳፋሪ ተግባር

Amhara 7
አስር አለቃ ሁሴን

አስር አለቃ ሁሴን አሸባሪውን በመደምሰሱ ትግል ከፊት በመሆን ለአማራ ህዝብ ብሎም ለኢትዮጵያ የተዋደቀ እየተዋደቀ የነበረ የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው

ነገር ግን ከስህተቱ ፍፁም የማይማረው የአማራ ክልላዊ መንግስት ባለፈው በአላይ እንደፈፀመው አግባብ ያልሆነ እስር ሁሉ አሁንም ወሎ በጠላት ተወራ ባለበት በዚህ ሰአት አስር አለቃ ሁሴንን እስከጓደኞቹ ትጥቅ በማስፈታት የቁም እስረኛ አድርጓታል
241445900 4225218024265680 1015490426313811989 n
አርቲስት ጌትነት አለማየሁ
የክልሉ መንግስት በዚህ ሰአት እንደ አስር አለቃ ሁሴን ያሉ የወሎን ምድራዊ ጆግራፊያዊ አቀማመጥ ጠንቅቀው የሚያቁ ልምድ ያላቸው ተዋጊዎችን ከፊት እንደማሰለፍ ትጥቅ ፈተው እንዲቀመጡ ማድረግ ከጠላት ተለይቶ የማይታይ እጅግ አሳፋሪ ድርጊት ነው
ለአማራ ህዝብ ነብሱን ለመስጠት በርሀ ለበርሀ እየተዋደቀን ያለ ጀግና ትጥቅ አስፈትቶ የቁም እስረኛ ማድረግ የባንዳ ስራ እንጂ የወገን ስራ በፍፁም ሊሆን አይችልም
አሁንም አልረፈደም። ጥፋት ካለ ይህ አስቸጋሪ የህልውና ፈተና ሲጠናቀቅ መጠያየቅ ይቻላል
ምንም አይነት ችግር ቢኖር ከገጠመን ከተጋረጠብን የህልውና ጥያቄ አይበልጥም
እውነት የክልሉ መንግስት እስትንፋስ ካላችሁ ይህንን ጀግና የቁርጥ ቀን ልጅ ትጥቁን መልሳችሁ ወደ ትግሉ መልሱ

ጎንደር Tube

1 Comment

  1. ብአዴን ከስህተት ይጠራል ብለህ አታስብ አመራር የሚሰጠው በረከት ስምኦን ካዘጋጁለት ቤተመንግስት ነው።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.