ፓሊስ በግድ መስክርበት ብሎኝ ነው…..ገለታው ዘለቀ

ደርግ ለምን እከሌን አሰርክ? ሲባል የአብዮቱ አደናቃፊ ነው ይልሃል።
Eskinderኢህአዴግ ሲመጣ ደግሞ የፓለቲካ ስዎችን ሲያስር ሲደበድብና ሲገድል የሚሰጠው ምላሽ መቃወም መብታቸው ነው የሚል ይሆንና ነገር ግን ዘር አጥፊዎች ወይም አሸባሪዎች ናቸው ይላል። ፍርድ ቤት አቅርቦ ፍርድ ቤቱን መሳሪያ አድርጎ ተቃዋሚን ያሰቃያል። አሁን ያለው መንግስት ደግሞ ተቃዋሚዎችን ለምን ታስራለህ፣ ትደበድባለህ፣ ትገድላለህ? ሲባል ምላሹ የኢህአዴግ ምላሽ ሆኖ ይሄኛው መንግስት ለየት የሚለው በሃሰተኛ ምስክር ጉዳይ ነው። ድሆችን ወንጀለኞችን አቃቤህግ የሃሰት ምስክር አድርጎ አሰልጥኖ በሃገሪቱ ችሎት አደባባይ ይዞ የሚቀርብ ተቋም ነው። እንደ ሃገር የከሰርነው አቃቤህግን የሚያህል ትልቅ ተቋም ይህ ህዝብ ቀረጥ እየከፈለ ያቋቋመው ይህ ተቋም የሃሰት ምስክር ማሰልጠኛ ተቋም ከፍቶ እያሰለጠነ ተቃዋሚውን የሚያሰቃይ ፍትህን የሚበድል በመሆኑ ነው። አቃቤ ህግ የሃሰት ምስክር አሰልጥኖ ይህንን በማድረጉ ዛሬ ፍርድ ቤታችን ከመቼውም ጊዜ በላይ ቆሽሿል።
በሃገራችን የፍርድ ቤት ታሪክ ውስጥ በዚሁ በኢህአዴግ ዘመን የሆነውን ነገር ላጫውታችሁ። አንድ ጊዜ የቅንጅት ደጋፊዎች ላይ ፓሊስ የሃሰት ምስክር ይዞ ቀርቦ ነበር። ታዲያ አንድ አባት በሃሰት በአንዱ ወጣት ላይ ድንጋይ ሲወረውር አይቻለሁ ብለሁ መስክሩ ብሎ አሰልጥኖ ይዟቸው ፍርድ ቤት ይዞ ይቀርባል። ችሎቱ ሲቀጥል እኚህ አባት ሊመሰክሩ መሃላ ፈፅመው ይነሳሉ። የሚመሰክሩበት ለጋ ወጣት ይመሰከርበት ዘንድ እንዲቆም በዳኛው ታዞ እጆቹን ወደኋላው አድርጎ እንባ እያቀረረ እኒህን ሰው ያያል።
  ዳኛ ምስክሩን ጠየቀ ” ይህንን ሰው ያውቁታል?”
   ምስክር ” በሚገባ”
    ዳኛ “ምን ሲያደርግ አዩት?”
    ምስክር “ፓሊስ ላይ እየደጋገመ ድንጋይ ሲወረውር”
  ምስክር ይህ ወጣት ድንጋይ በፓሊስ ላይ ሲወረውር ነበር ብለው አስረግጠው ከተናገሩ በኋላ ዳኛው ለተከሳሽ ወጣት እድል ሰጡ።
ዳኛ ” የምትጠይቀው መስቀለኛ ጥያቄ ካለ”
ተከሳሹ ወጣት አይኖቹ በእንባ ተከድነው አንጀት በሚያላውስ መልኩ እንዲህ ሲል ምስክሩን ጠየቀ።
 “አባባ በእግዚአብሄር ይዤዎታለሁ እኔ ድንጋይ ስወረውር አይተዋል? እኔ አልወረወርኩም አባባ። በእግዚአብሔር አሁን እኔ ድንጋይ ወርውሪያለሁ? ”  ሲል የቅንነትና የእውነት ሳግ ጉሮሮውን እያነቀው ጠየቀ።
በዚህ ጊዜ እኚህ አባት ፊታቸው ተለወጠ። በዚህ ንፁህ ልጅ ላይ በሃሰት በሰጡት ምስክርነት መንፈስ ቅዱስ ወቀሳቸው። በዚያች ሰአት እውነቱን ተናግረው በሚመጣው የሉሲፈር ቁጣና እውነቱን ተናግረው እግዚአብሔርን ከማሳዘን በመቆጠብ መሃል አንዱን ይመርጡ ዘንድ ነፍሳቸው ተፋጠጠች።
ፍርድ ቤቱ ፀጥ ርጭ ብሏል። ከብዙ ሰከንዶች በኋላ እኒህ አባት ወሰኑ። ፊታቸውን ቆፍጠን አድርገው። ወደዚያ ወጣት እያዩ
” ልጄ ሆይ እኔ አንተ ድንጋይ ስትወረውር አላየሁም። ይቅርታ አላየሁም ልጄ……”   ሲሉ ፍርድ ቤቱ ላይ ድንጋጤ ወደቀ።
 ዳኛ ” ታዲያ ለምን ቀደም ብለው ድንጋይ ከፓሊስ ላይ ሲወረውር አይቻለሁ ሲሉ መሰከሩበት?”
ምስክር ” ፓሊስ አስገድዶ ፍርድ ቤት ቀርበህ ይህ ወጣት ድንጋይ ሲወረውር አይቻለሁ አሸባሪ ነው በልና መስክር ብሎኝ ነው…..ተገድጄ ነው…..”  ብለው ሃቁን ተናገሩ። ይህ ነገር የኢትዮጵያን ፍርድ ቤቶች ሴራ የሚያሳይ እስከ ሃቹ በፍርድ ቤት ታሪካችን የማይረሳ ነበር።
ዛሬ በእነእስክንድር ላይ የሚመሰክሩ ሰዎች እንደዚሁ ናቸው። አቃቤህግ የሃሰት ምስክር እያሰለጠነ ንፁሃንን ያሰቃያል። እንኪያስ ፍርድ ቤታችን የበለጠ መጫወቻ የሆነው ዛሬ ነው።
————————————————————
ከግብረ አበሮቹ ጋር የሜታ አቦ መኪና ሹፌርን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሎ ገንዘብ በመዝረፍ እና በመሳሪያ በመታገዝ ካቴድራል መንገድ ላይ ያለውን ንግድ ባንክ ለመዝረፍ ጥበቃዎችን በመግደል በፈጸመው የውንብድና ወንጀል እድሜ ልክ እሰራት የተፈረደበት። በማይድን በሽታ (ኤችአይቪ) ሰበብ ተደርጎ ከእስር የተለቀቀ። በአንዷለም አራጌ መጽሐፍ ላይ በማረሚያ ቤት በታራሚዎች ላይ ውንብድና የሚፈጽም ለወያኔ መንግስት ሲያገለግል የነበረ። በአዲስ አበባ ከተማ ከረዩ ሰፈር የሚኖር በዚህ መንግስት በሲቪል ደህንነት ተቀጥሮ ደመወዝ የሚከፈለው ሽጉጥ የታጠቀ እና ስራውን መከታ አድርጎ ኤችአይቪ እንዳለበት እያወቀ ከአምስት በላይ ሴቶችን የደፈረ መሆኑን የሰፈሩ ሰዎች በምሬት የሚናገሩበት እድሜው 54 ሆኖ 40 ነው ብሎ የሚዎሽ፣ ስሙ ይባስ የሚለውን ፋንታሁን ወደሚል በመቀየር የሚያጭበረብር….. ዛሬ የዐቃቤ ሕግ ሆኖ በዐቃቤ ህግ የሀሰት ክስ የሀሰት ምስክርነት ለመስጠት ቀርቦ ‘አቡነ አረጋዊ መስጊድን’ እንዲያቃጥል እስክንድር አዞኛል በማለት የሀሰት ቃሉን ሰጥቷል…

246719415 2981773945424272 8375259892310906487 n

247053175 2981774005424266 721299530587133396 n

Tamru Huliso

247492630 10220637469631340 7237169350600416001 n

ትላንት #እስክንድር ላይ ሊመሰክሩ ከተጠሩት ሰዎች መሃል ይባስ አሰፋ የሚባል የሰፈሬ ሰው በላ መሆኑን ሳውቅ ደንግጫለሁ። ይባስን ነፍሰ በላ ነው ስል ለማለት ያህል አይደለም። እዚያው ጡረታ ሰፈር ፣ ከረዩና ጭድ ተራ ፤ሰፈሬ ላይ የጭካኔና የአውሬ ተግባሩን እያየሁ ያደግኩኝ ስለሆንኩ እንጂ። ይባስ የሴት ልጅን ጡት በስለት ሲቀድ ነው የኖረው። ምሽት ላይ እጁ ላይ የጣላትን ሴት በቀኝ እጁ ግራ እጇን ፤በግራ እጁ ደግሞ ጩቤውን ይዞ እየተንጎራደደ ብዙ ጎረምሶቹን አስከትሎ ወደ “ቅጠል ተራ” ሲሄድ ልጆች ሆነን በድንጋጤ ነበር የምንሸበረው። ቅጠል ተራ ቀን ቀን ቅጠል የሚሸጥበትና ማታ ላይ እጅግ ጨለማ የሚሆን ገደል አጠገብ ያለ ቦታ ነበር። በቀኝ እጁ ይዟት የሂደውን ሴት መጀመሪያ ራሱ ቀጥሎ አስር አስር ሳንቲም እየተቀበለ ከኋላው ሲግተለተል ለነበረ ጎረምሳ ያስደፍራል። እከሊትን ለዳማ በ*ት ተብሎ በነጋታው ይወራል። ይባስ ይህ ነው። በነጋ ጠባ እህቴን ምን ያረግብኝ ብለህ እንድትሸበር የሚያደርግህ ፍጥረት። ይህ ሰው በከፋና በተደጋገመ ወንጀል እድሜ ልክ ተፈርዶበት ወህኒ ቤት ነበር የኖረው። የህጻኑ ልጅ ለውጥ ለሱም ሲሳይ ሆነለትና ለመፈታት በቃ። ዛሬ ደግሞ ይባስም ሰው ሆነና ለምስክርነት ደረሰ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢዜማ የተገደለ አባሉን አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል
በነገራችን ላይ ይባስ አንዷለም አራጌንም እስር ቤት ውስጥ ሆኖ የደበደበው ይመስለኛል። በወቅቱ ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ አንዷለምን የደበደበው ይባስ አሰፋ ይባላል ተብሎ ሳነብ በግሌ የማውቀው ይባስ ነው ብዬ ነበር። ማስረጃ ስላልነበረኝ ምንም አላልኩኝ።
ዛሬ ከነፎቶው አየሁት እስክንድር ላይ መስካሪውን አውሬ።
እስክንድር ነጋን እንደፖለቲከኛም እንደ ጋዜጠኛም ብዙ ጥሞኝ አያውቅም። ጋዜጣዎቹንም ከተማሪነት ዘመኔ ጀምሮ እንኳን በቁም ነገር አይቻቸው አላውቅም። ግን ለሚያምንበት ነገር ያለውን መሰጠት አደንቃለሁ። አንድ ጓደኛዬም “ለሚያምንበት ነገር ለመሞት የተዘጋጀ” ብሎ ይገልጸዋል። ይህ አይነቱ መሰጠት በዚህ ዘመን ብርቅ ነው።
አንዳንዶች ተለወጠ እያሉ የሚያደንቁት የመአዛ አሸናፊና የጢሞትዮስ የፍትህ ስርዓት እንግዲህ ይህ ነው።
እስክንድር የሚያምነው አምላክ ይሁነው እንጂ ምን ይባላል!
#ጃዋር እና #በቀለ ላይ የሚያስመሰክሩት የትኞቹን ወንበዴዎች ይሆኑ ደሞ?

1 Comment

  1. አረ ዶክተር አብይ የሀይማኖት መጽሀፍን አንብበሀል ፊደልም ቆጥረሀል ትግሬዎችን ተገላገልን ስንል የማይታሰር ሰው አስረህ ይባስ ብለህ ይህን ነብሰ በላ በክፋት የቆሸሸ ሰው አንተ ፍርድ ቤት ምስክር አድርገህ አንተን አዋርደህ ፍርድን አዋርደህ ቁጭ ትላለህ? ወ/ሮ መአዛ እንደሆነ ፍትህን ከመጠበቅ ሞዴሊንግ ላይ ተጠምደዋል ሲናገሩ በቄንጥ ነው ሲለብሱ ማን ይደርስባቸዋል ሲራመዱ ካት ዎክ የሚሉት አይነት ነው ከዚህ ሁሉ ጭንቅንቅ መሀል ፍትህ ለተበደለ ያሰፍናሉ ማለት የማይታሰብ ነው ተያይዞ ማለቅ ነው። አቶ ታዲዮስ ታንቱን እስክንድር ነጋን አስሮ ሰው እንዴት እንቅልፍ ይይዘዋል። እነዚህ አማካሪ የተባሉትስ የት ናቸው? አማካሪው አገኘሁ ተሻገር ሆነ እንዴ?

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.