በመቐለ የሚገኘው መስፍን ኢንዱስትሪያል የአሸባሪው ህወሓት የመሳሪያ ማከማቻ፣ መስሪያ እና መጠገኛ ሆኗል።

በመቐለ ከተማ የሚገኘው መስፍን ኢንዱስትሪያል የአሸባሪው ህወሓት የጦር መሳሪያ ማከማቻ፣ መስሪያ እና የከባድ መሳሪያዎች መጠገኛ መሆኑን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ታማኝ ምንጮች ነግረውናል። እንደምንጮቻችን ገለጻ አሸባሪው ቡድን በመቐለ ከተማ የሚገኘውን የመስፍን ኢንዱስትሪያልን ሙሉ በሙሉ የመሳሪያ ማከማቻ እና ማምረቻ እንዲሁም የከባድ መሳሪያዎች የጥገና ማዕከል አድርጎ እየተጠቀመበት ነው።
246488410 2116478211836849 7252238005556177769 n 1024x614 በመቐለ የሚገኘው መስፍን ኢንዱስትሪያል የአሸባሪው ህወሓት የመሳሪያ ማከማቻ፣ መስሪያ እና መጠገኛ ሆኗል።
246488410 2116478211836849 7252238005556177769 n

የኢፌዲሪ አየር ኃይል በመቐለ ከተማ የሚገኙና አሸባሪ ቡድኑ ለሽብር ተግባሩ የሚጠቀምባቸውን ስፍራዎች፣ እና መሳሪያዎች ላይ ካለፈው ሰኞ ጀምሮ እርምጃ መውሰድ ጀምሯል። መከላከያ ሰራዊቱ በአየር ኃይሉ አማካኝነት በመቐለ ከተማ የሚገኙ የግንኙነት መሳሪያዎችን እና ታወሮችን የሽብር ቡድኑ ሲጠቀምባቸው መቆየቱን በማረጋገጥ እርምጃ የወሰደ ሲሆን ዛሬም የአስቸኳይ ጊዜ ማጣሪያ ባወጣው መረጃ የሽብር ቡድኑ ለመሳሪያ ማከማቻነት እና ለጥፋት ስራው የሚጠቀምባቸው አካባቢዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን አረጋግጧል።

ምስል፡ ከድረገጽ
(ኢ ፕ ድ)

1 Comment

  1. የተገነባው በተሰረቀ በኛው ሀብት የተገነባዉ ኢትዮጵያን ለማጥፋት መሆኑ እየታወቀ ምን አሸማቀቃችሁ? የሌቦችን ንብረት ዱቄት አድርገነዋል የኢትዮጵያ ህዝብ ደስ ይበልህ ማለት ማንን ገደለ?

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.