ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በዋሽግተን ዲሲ- አሸባሪው ህውሃት ከአማራ ክልል ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለቀው እንዲወጡ

246548910 405111101237870 2650394162840123624 n

ነገ ዋሽንግተን ዲሲ ለአሜሪካ መንግስት ቀደም ብለን በጽ/ቤታቸው ውስጥ በአስረዳናቸው መሰረት መረጃወቻችንን ይዘን ፡ለወገናችሁ የምትቆረቆሩ ኢትዮጵያዊያን በሰልፍ ተገኝታችሁ ፡ለአሚሪካ መንግስት ውጭ ጉዳይ መስሪያቤት የኢትዮጵያ ጉዳይ ተጠሪ እናስረክባለን፡፡

ከጥያቄወቻችን በከፊል የሚከተሉት ናቸው

አሜሪካ ለአለም ምግብ ድርጅት የምትሰጠው የምግብ ድጋፍ ትግራ እንደሚላከው ሁሉ አማራ ክልልም በተመሳሳይ በአስቸኳይ እንዲላክ።

አሚሪካ ለኢትዮጵያ መከላከያ እንዲሆን በቀጥታም ሆነ በተዛዋሪ የፈቀደችው ዘመናዊ ጦር መሳሪያ ኦነግ ሸኔ በአማራ ህዝብ ላይ ጀኖሳይድ እየፈፀመበት መሆኑን እና በአሚሪካ የጦር መሳሪያ የተደራጀውን አሸባሪ ቡድን ለፈፀመው ፍጅት አስፈላጊውን እርምጃ እንድትወስድ።

የአለም ምግብ ድርጅት ለምግብ እርዳታ የላካቸው መኪኖች የአሸባሪው ህውሃት ሰራዊት እና የአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ሰራዊት የአማራን ህዝብ ለመግደል እየተጠቀሙባቸው በመሆኑን ጉዳዩን አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጡበት።

አሚሪካ ትግራይ ላይ ጦርነቱን ለማስቆም እና ሰላማዊውን ህዝብ ለመደገፍ ያሳየችውን ትጋት ፡ለአማራ ክልል ህዝብም በተመሳሳይ በአስቸኳይ ወራሪው አሸባሪው ህውሃት ከአማራ ክልል ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለቀው እንዲወጡ ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወሰድ።

እኛ በአሜሪካ የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን እንጠይቃለን

6 Comments

  1. እዉነት ነዉ እደግፈዋለሁ ጥያቄዉን ጦርነት ነዉ ወይስ ስርቆት እየተካሄደ ያለዉ ንፁሀኑ አለቀ በአማራ ክልል በወሎ ላይ እየተሰራ ያለዉ ነገር

  2. ኦነጉ አብይ አህመድ የኦሮሚያ ፖሊስን በሸኔ ስም እየተጠቀመ እንዲሁም ለወያኔ ነጻ መሬትና ስንቅና ትጥቅ እየሰጠ መከላከያም እንዳይዋጋ እያደረገ የሚጠላውንና የሚፈራውን የአማራ ህዝብ ዘር እያጠፋ ።

  3. አብይ አህመድ ታላቅ መሪ ነው። ነገር ግን ምን ያደርጋል ከሲዖል ከጥልቁ በወጣው የጨለማ ሰራዊት መንፈስ ሙሉ ለሙሉ ልብና አእምሮአቸው የተያዘው ወያኔና በዘረኝነት ሰይጣናዊ ሀሳብ የጦዙ ወያኔ የወለዳቸው እባቦች አላሰራ አሉት እንጂ፤ ግን ግድ የለም በአብይ ላይ በክፉ የተነሱትን ሁሉ ጌታ እግዚአብሔር በአብይ ፊት ቀድሞ እየተወጋለት ስለሆነ ሁሉም ተሸንፈው እጅም ሰጥተው ይቅርታ የሚጠይቁበት ጊዜ ሩቅ አደለም።

  4. ወንድማችንና ጠቅላዩን የሰጠን ሥሙ የሰራዊት አምላክ እ/ር ይባላል ። ክፉም ሆነ መልካምን መንግሥታትን የሚሾም እና የሚያስቀምጥ እ/ር ብቻ ነው። ስለዚህም ሀገራችን ለተጋረጠባት ፈተና የመጀመሪያው” ፀሎት” ነው ። አንድ ሰው ለመፀለይ እና ከእግዚአብሔር እንዲሰማ ለሚፀልይበት ነገር” መራራት” ያስፈልጋል ይሄ የርህራሄ መንፈስ በውስጡ ሲኖር ደግሞ መፀለይ ይቻላል ሲፀልይ ደግሞ እግዚአብሔር ይሰማል። ወገኖቼ ሀገራችን በዚህ እንታደግ እግዚአብሔር ያየላትን ከፍታ የምትወርስበት ቅርብ ነው።

  5. ጥያቄዎቻችንን ክልላዊ እና ብሄር ተኮር ከምናደርግ አገር ተኮር ብናደር ለሁለም ኢትዮጵያዊ ይበጃል እላለሁ።የዛኔ ወያኔ የዘራው ዘር ይጠፋል።ወንድማማቾችነት እና እኩልነት ይሰፍናል።ዘረኝነት የማንንም ሀገር ሲረዳ አልታየም።የሀገሬ ሰው ንቃ ወንድምህ አትግደል።

  6. ጥያቄዎቻችንን ክልላዊ እና ብሄር ተኮር ከምናደርግ አገር ተኮር ብናደር ለሁለም ኢትዮጵያዊ ይበጃል እላለሁ።የዛኔ ወያኔ የዘራው ዘር ይጠፋል።ወንድማማቾችነት እና እኩልነት ይሰፍናል።ዘረኝነት የማንንም ሀገር ሲረዳ አልታየም።የሀገሬ ሰው ንቃ ወንድምህን አትግደል።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.