የኢትዮጵያ መንግሥት ተፈጸመ የተባለውን የአየር ድብደባ አስተባብሏል

55725769 303

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቐለ ዛሬ ሰኞ የአየር ድብደባ መፈጸሙን የግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ሰራተኞች እና ዲፕሎማቶች ተናገሩ። የትግራይ ቴሌቭዥን ጣቢያ በፌስቡክ ገጹ ባሰፈረው ጽሁፍ በአየር ድብደባው ሶስት ሰዎች መገደላቸውን እና በ10 የሚቆጠሩ መቁሰላቸውን ገልጿል።የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ተፈጸመ የተባለውን የአየር ድብደባ አስተባብሏል።

በከተማው የሚገኙ ሁለት የግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ሰራተኞች የአየር ድብደባው መፈጸሙን በአጭር የጽሁፍ መልዕት ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት (AFP) ገልጸዋል።ሌሎች ሁለት ዲፕሎማቶችም ጥቃቱ መፈጸሙን እንደተናገሩ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
በዘገባዉ መሠረት የመጀመሪያው ድብደባ ዛሬ ሰኞ ጠዋት በመቐለ ዳርቻ ስሚንቶ ፋብሪካ ከሚገኝበት አካባቢ ተፈጽሟል።
ሁለተኛዉ ድብደባ ዛሬ ዕኩለ-ቀን በመቐለ ማዕከላዊ ክፍል ባለሥልጣናት የሚያዘወትሩት ፕላኔት ሆቴል አካባቢ እንደተፈጸመ የዜና ወኪሉ ዘግቧል። የህወሓት ቃል-አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በተረጋገጠ የትዊተር ገጻቸው የአየር ድብደባው መፈጸሙን አረጋግጠው “ሰኞ በመቐለ የገበያ ቀን ነው። [የጥቃቱ] ዓላማ ግልጽ ነው” ብለዋል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና የኢትዮጵያ መንግሥት እስካሁን በጉዳዩ ላይ የሰጡት መግለጫ የለም። በጥቃቱ የደረሰው ጉዳትን በተመለከተ በመቐለ ከሚገኙ የሕክምና ተቋማት ማረጋገጫ አልተገኘም።
የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ተፈጸመ የተባለውን የአየር ድብደባ አስተባብሏል። የመንግሥት ኮምዩንኬሽን አገልግሎት ኃላፊ ለገሰ ቱሉ “መንግሥት ለምን የራሱን ከተማ ያጠቃል? መቐለ የኢትዮጵያ ከተማ ነች” ሲሉ ለሬውተርስ ተናግረዋል።
DW
ተጨማሪ ያንብቡ:  የሀይማኖት መብታችን የሚከበረው በነፃነት ትግል ነው! - ሰማያዊ ፓርቲ

2 Comments

  1. አመነ አስተባበለ ምን ዋጋ አለው። በወሎ ህዝብ ላይ በወያኔ የሚፈጸመውን የማያቆም መንግስት ምን መንግስት ይባላል። ሴት ወንድ ሳይል ወያኔ የወሎን፤ የጎንደርንና የአፋርን ህዝብ እየጨፈጨፈ ለምን መንግስት ተብዬው በትግራይ መሬት ቆርጦ በመግባት ስንቅና ትጥቅ የሚያቀብልበትን መንገድ መዝጋት እንዳማይቻል አይገባኝም። ዝም ብሎ በከተማ ውስጥ ራስን ደብቆ መደንፋት ለማንም አይጠቅምም። በእውነት በወሎ የሚፈጸመው ግፍ መፈጠርን የሚያስጠላ ነው። ታዲያ ወያኔን መለማመጥ ምኑ ላይ ነው ጥቅሙ። ሰው ገድለው ቆሻሻ እዚያ ወድቋል የሚሉ ውሾች ናቸው። የወሎን ህዝብ የአብይ ሰራዊት መጥቶ ያድናችሁ እያሉ ቤት ዘግተው እሳት በመለኮስ ሰዎን የሚያቃጥሉ አራዊቶች ናቸው። ይህ ሁሉ ሰቆቃ እየተሰማ የኢትዮጵያ ህዝብ ዝም ብሎ ወደ እየቀን ስራው ሂዶ መመለሱ ዘግናኝ ነው። አንድ የወሎ ገበሬ እንዳለው እንዲህ ያለ ግፈኛ ሰው በህይወቴ አይቼ አላውቅም። ስለሆነም ውጫጭ ማሳደጌ ትቼ መዋጋት እፈልጋለሁ። አስታጥቁኝ። እንደ በአል ፍየል ተጎትቼ እንደ ጓደኞቼ ከምገደል ገድዬ እሞታለሁ ነበር ያለው። ከአንድ ቤት ዘጠኝ ቤተሰብ የሚሞትባት ሃገር መሪ ተሁኖ የትላንቱ ቀን ለዛሬ የማይሻል ከሆነ መንግስትነቱ ምን ይጠቅማል።
    አሁን መቀሌ አካባቢ የአየር ድብደባ ተፈጸመ ብለው የሚፈራገጡ ሙታኖች ወያኔ ከላይ በተጠቀሱት ስፍራዎች የፈጸመውንና በመፈጸም ላይ ያለውን ግፍ ቢመለከቱ ሰው መሆናቸውን ይረሳሉ። ገለው አታንሱ አትቅበሩ እያሉ ጅብ እንዲበላቸው የሚያረጉ ውሾች ናቸው። የሰሜን ጦር አባላትን እጅና እግር አስረው በጥይት ደብድበው በአስከሬናቸው ዙሪያ የሚጨፍሩ አናብስቶች እንዴት ነው ርህራሄ የምናሳያቸው። የዶ/ር አብይ መንግስት የዞረበት መንግስት ሆኗል። አንድ አዎን ደብድበናል ሲል ሌላው ቃል አቀባይ ደግሞ አልሆነም ይለናል። እውነታው ግን የሆነ ነገር ለመምታት ተሞክሯል። እህል፤ እንስሳ፤ እቃ ወደ ትግራይ ወያኔ ሲያመላልስ የአየር ሃይሉ ምን እየሰራ ነው? የፊትና የኋላ መኪናዎች ቢመቱ ወደፊት መሄዳቸው ለጊዜውም ቢሆን ይገታ ነበር። ግን በየመድረኩ ከመለፍለፍና ወጣቱ በየጫት ቤቱ ከመዳለቅ ባለፈ ወያኔ በህዝብ ላይ የሚያደርሰውን ግፍ ለማስቆም የሚደረገው ጥረት በቂ አይደለም።
    ሌላው ተንኮለኛ የቀበሌ፤ የወረዳና የአውራጃ ወይም ባለ ሌላ ባለስልጣን እባካችሁ ሰውን ከሰው አትለዪ። ለእርዳታ የመጣን የምግብና ሌላም ነገር እኩል አካፍሉ። አንተ አንቺ ከዚህ አካባቢ ኗሪ አይደለህም/ሽም በማለት ሰውን እየለያዪ ለባሰ ሰቆቃ ማዳረግ ከወያኔ ተግባር የሚለይ አይሆንም። አማራ ቅማት እያሉ መሞሻለቅ የኋላ ቀር እይታና የወያኔን ደጋፊ መሆን ነው። ዛሬ በወሎና በአፋር በጎንደር በወያኔ የሚፈጸመው ግፍ ቆይቶ ሁሉን ሊያዳርስ ይችላል። ጊዜ እያለ መደረግ ያለበት የአለምንም ሆነ የሌሎች ሃይሎችን ጫና ባለመፍራት ገዳይን መግደል፤ አፍራሽን ማፍረስ አስፈላጊ ይሆናል። ቀን ግን እየሮጠ ነው። ከወያኔ ሞት የተረፈው ሰው በመጠለያ ሞት፤ ረሃብ ሌላም ነገር ሊፈጠር ስለሚችል ወያኔ ለአንድ ጊዜና ለመጨረሻ ጊዜ መደምሰስ አማራጭ አይኖረውም።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share