በሰሜን ሸዋ ዞን ማጀቴ አርሶአደሮች ማሳ ላይ በተፈጸመው ድንገተኛ ጥቃት ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው እህል ወድሟል

245328159 2112541888897148 8138488649708454859 n
245328159 2112541888897148 8138488649708454859 n
በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ ግድም ወረዳ በማጀቴ አካባቢ ነዋሪ በሆኑ አርሶ አደሮች ማሳ ላይ ከትናንት በስቲያ ሌሊት በተፈጸመ ድንገተኛ ጥቃት ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት እህል መቃጠሉ ተገለጸ።
የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረጻዲቅ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ ከወቅታዊ የአገሪቷ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ በዞኑ ስጋቶች ስለነበሩ እንደ ዞን አቅጣጫ ተሰጥቶ የተለያዩ የጸጥታና ደህንነት ሥራዎች ሲከናወኑ ቆይቷል፡፡ በዋናነትም ከአርሶ አደሩ አንጻር የተሰበሰቡ ሰብሎች ማሳ ላይ እንዳያድሩና ከአደሩም ስምሪት ተሰጥቶ እንዲጠበቁ ሲደረግ ቆይቷል።
ይሁን እንጂ ከትላንት በስቲያ ጥቅምት 3 ቀን 2014 ዓ.ም ለጊዜው ምክንያቱ ባይታወቅም አደጋው በደረሰበት እለት ተረኛ የነበሩና የጥበቃ ስራን እንዲያከናውኑ ሃላፊነት የተሰጣቸው አካላት በስፍራው እንዳልተገኙ አረጋግጠናል፤ ይህንን ክፍተት ተጠቅመው ማንነታቸው ያልታወቀ ጉዳት አድራሾች የአርሶ አደሮችን ሰብል አቃጥለዋል ነው ያሉት አቶ ታደሰ።
245325750 2112542092230461 4546684717722009896 n
245325750 2112542092230461 4546684717722009896 n
የተሰበሰበውን የአርሶ አደሮች ሰብል ያቃጠለው ማን እንደሆነ፤ ከየትስ የመጡ ናቸው የሚለው ገና አልታወቀም ያሉት ዋና አስተዳዳሪው፤ በዞን ደረጃ የተለያዩ መረጃዎች እየደረሱ ቢሆንም ትክክለኛውን መረጃ ለማጣራት የአጎራባች ወረዳ አካላትና መርማሪ የፖሊስ አባላት የተቀናጀ የምርመራ ሥራ እያከናወኑ መሆኑን አስታውቀዋል።
የዞን፣ የክልል እንዲሁም የፌደራል አመራሮችና የጸጥታ አካላት መከላከያን ጨምሮ በቦታው እንደተገኙ የጠቀሱት አቶ ታደሰ፤ የጉዳት መጠኑን ለማወቅ በተደረገው ጥረት እስካሁን ባለው መረጃ ከ95 ኩንታል በላይ ጤፍ እንደተቃጠለና ይህም በብር ሲገመት ግማሽ ሚሊዮን ብር እደሚደርስ አብራርተዋል።
የማጀቴ ከተማ መሪ ማዘጋጀ ህንጻ ሹም ሃላፊ የሆኑት አቶ ያለው አየለ በበኩላቸው ጥቃት አድራሾቹ የኦነግ ሸኔ አባላት መሆናቸውን ገልጸዋል።
እነዚህ ታጣቂዎች በአካባቢው ላይ ጥቃት ሲፈጽሙ የመጀመሪያቸው እንዳልሆነም ነው አቶ ያለው ያስታወቁት።
እንደ አቶ ያለው ገለጻ፤ በአሁኑ ጥቃት የበርካታ አርሶ አደሮች የጤፍ ክምር ተቃጥሏል። ይህም በገንዘብ ሲተመን ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ይደርሳል።
በቀጣይ ተመሳሳይ ችግር እንዳይፈጠር በጊዜያዊነት አካባቢውን ሀላፊነት ያለባቸው አካላት ተውጣጥተው እንዲጠብቁ፤ የሰላም ኮሚቴዎች በጋራ እንዲሰሩ፤ የደረሱ ሰብሎች በፍጥነት እየተነሱ ከተቻለ ወደ ጎተራ ካልተቻለ ደግሞ በቅርብ ርቀት ተጓጉዞ የሚወቁበትን ሁኔታ እየተመቻቻ መሆኑን የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገልጸዋል።
በትናንትናው እለትም በርከት ያሉ ሰብሎች ከማሳ ላይ መነሳታቸውን ዋና አስተዳዳሪው አብራርተዋል፡፡
በጽጌረዳ ጫንያለው
(ኢ ፕ ድ)
ተጨማሪ ያንብቡ:  አብስኒያ- አድስ አበባ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share