ከእናቴ ጋር ቀጠሮ (አዲሱ ደረጀ)

“ከባለቤቴ ጋር ትዳር ከመሰረትን 21 ዓመት ሞላን …ባለቤቴ አንድ እራሴን እንድፈትሽበት ያደረገኝን ጥያቄ አቀረበችልኝ … ሃያ አንድ ዓመት ካንተ ጋር ስኖር አንድም ቀን ከእናትህ ጋር ለመዝናናት ስትወጣ አይቼክ አላውቅም … ዛሬ ማታ እናትህን እራት ምሽት ጋብዛትና አዝናናት አለቺኝ” ውዷ ባለቤቴ …ባቀረበችልኝ ሃሳብ ከመገረም በላይ መሰጠኝ ተስማማሁኝ እናም ወደ እናቴ ጋር ደወልኩላት ኡሚ ዛሬ ካንቺ ጋር ሽርሽር መውጣት እፈልጋለሁ አልኳት … ደነገጠች “ምነው ሰላም አይደል ልጆችህ ምን ሆኑ …ባለቤትህስ ሰላም አይደለች እንዴ ?” በማለት የድንጋጤ ጥያቄዎቿን አርከፈከፈችብኝ…”አብሽሪ ኡሚ ሁሉም ሰላም ነው ካንቺ ጋር ለመዝናናት ፈልጌ ነው” አልኳት … በጣም ደስ አላት ተስማማች … ወደ ማታ ተዘጋጅተሽ ጠብቂኝ አልኳት …

244532188 261792505952531 8218528289303574834 n ከእናቴ ጋር ቀጠሮ (አዲሱ ደረጀ)

… በቀጠሮዬ ሰዓት ወደ እናቴ ጋር ሄድኩኝ … እናቴ በረንዳው ላይ ቆማ እየጠበቀቺኝ ነበር … እናቴ ሁለመናዋ ተቀያይሯል እርጅና ተጫጭኗታል … ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ ወደ መኪናዬ አስገብቻት ጉዞ ጀመርን … እናቴ በጣም ደስታ ይነበብባታል “ልጄ ዛሬ ካንተ ጋር ሽርሽር እንደምወጣ ለሰፈር ሰዎች ሁሉ እንዲሁም ለዘመድ አዝማዶቼ በሙሉ ተናግርያለሁኝ” በጣም ከመደሰቷ የተነሳ አንድም የምታውቀው አልቀራትም ወሬውን ለሁሉም አዳርሳዋለች …

… ወደ ሆቴል ይዥያት ሄድኩኝ አስተናጋጁ የምግብ ዝርዝር ወረቀት የያዘ ኩፖን ሰጠን “ኡሚ ምረጪ” አልኳት… ፈገግ አለች ከእርጅና የተነሳ ማየት እንደማትችል ተረዳሁ … ላንብብልሽ አልኳት “ልጅ እያለህ ሆቴል ቤት ገብተን ልንመገብ ስንል የምግብ ዝርዝር አነብልህ ነበር … አሁን እዳህን ክፈል” ብላ ፈገግ አለች እኔም ፈገግ ብዬ አነበብኩላት … የለበሰችውን ልብስ ስመለከት ከአስራ ዘጠኝ ዓመት በፊት የሞተው አባቴ የገዛላት የመጨረሻ ልብሷ እንደነበር አስታወስኩ … ምግቡ ቀርቦ እናቴ ከደስታ የተነሳ ምንም እየበላች አልነበርም… ደስታ በደስታ ሆናለች … በሕይወቴ እኔም በጣም የተደሰትኩበት አጋጣሚ ነበር ከእናቴ ጋር ተዝናንተን ስናበቃ ይህ ምሽት እንዲደገም ፈልጌ “እማ መቼ ተመልሼ ልምጣና ልውሰድሽ..?” አልኳት … በእንደዚ ቀን ና ነገር ግን እኔ ነኝ የምጋብዝህ ከተስማማህ ና” አለቺኝ ፈገግ አልኩኝ “አብሽሪ ትጋብዥኛለሽ” አልኳትና ተለያየን … በመሃል እናቴ ታመመች ከህመሟ ድናልኝ አብርያት የማሳልፍበት ምሽት ናፈቀኝ … ነገር ግን ከእናቴ ጋር ዳግም አልወጣንም … እናቴ ወደ ማይቀረው የሞት ጉዞ ተጓዘች በጣም አዘንኩ አለቀስኩ …
… ከእናቴ ጋር ቀጠሮ ይዘን በነበርንበት ቀን አመሻሹ ላይ ከአንድ ታዋቂ ሆቴል ቤት ተደወለልኝ “ዛሬ እራት ከባለቤትህ ጋር በነፃ ተጋብዛቹሃል” የሚል ነበር። ግራ ተጋባው ማነው እንዴት … ለማንኛውም እሺ እንመጣለን ብዬ ስልኩን ዘግቼ ምሽት ላይ ከባለቤቴ ጋር ሄድኩኝ … ግብዣው ከደብዳቤ ጋር ቀረበልን ደብዳቤውን ከፈትኩት እንዲህ ይላል:-
“ልጄ ሰላም ላንተ ይሁን የእራቱን ግብዣ ስንቀጣጠር መገኘት እንደማልችል አውቅ ነበር … የሞት ቀጠሮዬ እየተቃረበ እንደነበር ነፍሴ ይነግረኝ ነበር ልጄ ይኸው እኔ በቃሌ መሰረት ጋብዥሃለው … በኔ ፋንታ ውዷ ባለቤትህ አብራህ እንድትሆን ፈቅጃለሁ!” ይላል ሳይታወቀኝ እንባዬ ወረደ አለቀስኩ 21 ዓመት ሙሉ የዘነጋሁትን ውድ ዕቃ አሁን ነው ማጣቴን ያወኩት…!
——–
ስንቶቻችን ይሆን ካገባን በኋላ እናቶቻችንን የምናስታዉሳቸዉ ?

1 Comment

  1. ድንቅ ነው እናት ያደረገችለትን ብድር ሳይከፍላት ካጣት ልጅ ህይወቱን ሙሉ ባዶ ይሆናል

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.