ክቡር ሚኒስትር ! (ይድነቃቸው ተሰማ)

244753209 4928546863839294 3996714677589570999 nአዎ ! እርስዎ እንዳሉት የህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሰራተኞች ከብሔ/ከዘር ፣ ከሐይማኖት እንዲሁም ከፖለቲካ ወገንተኝነት ፈጽሞ መራቅ አለባቸው ።
ግን እኮ ክቡር ሚኒስትር ፦
~ ይህ የሚሆነው በእርስዎ እናት ድርጅት ኢዜማ “በዜጎች የፖለቲካ የማህበራዊ ሥርዓት” እንጂ ” ብሔር ፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ” የፖለቲካ ሥርዓት አይደለም ¡¡
~ እርስዎም ” #ለህገ_መንግስቱ_ታማኝ በመሆን” የተሰጠኝን ኃላፊነት በቅንነት፣በሕግና ሥርዓት ለማገልገል ቃል እገባለሁ። ብለዋል ¡¡
~ በሕገ-መንግስቱ ደግሞ የሥልጣን እና የሀገሩ ባለቤት ብሔር ፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ፤ እንጂ ግለሰብን ወይም ሰውን በዜግነት የሚቀበል አይደለም ።
~ ምን ይሄ ብቻ ፦ እርስዎ የሚመሩት ተቋም ጨምሮ አብዛኛው የመንግስት የሠራተኞች የቅጥር የምልመላ መስፈርቶች መካከል አንዱ የብሔር ተዋጽኦ ጭምር ነው ¡¡
~ ከዚህም ከፍ ሲል ሠራተኞች “በብሔራቸው” በግዴታ ይሁን ወይም በፍቃድ በፖለቲካ ተቧድነው የገንዘብ መዋጮ ይጠበቅባቸዋል ¡¡
እናም ክቡር ሚኒስትር ፦ ለባለፉት 31 ዓመት በእንዲህ መልኩ የተቃኘው ሥርዓት ፤ አሁን እርስዎ እንደሚሉት እንዲሁ በቀላሉ በስብሰባ ” ብሄርና ዘር ቤታቸው” ትተው ሠራተኞች ይመጣሉ ?!
ሌላው ደግሞ ፦ “…በፖለቲካ ፓርቲ ደጋፊነት ተጠግቼ ይህን ላገኝ እችላለሁ ማለት በፍጹም አይሰራም ” ብለዋል ፤
ክቡር ሚኒስትር ፤ እርስዎ ይህን ኃላፊነት ወይም ሥልጣን ያገኙት በምንድነው ?!
ተጨማሪ ያንብቡ:  የቀድሞው የሻሸመኔ ከተማ ከንቲባና ምክትል ከንቲባ በሌብነት ተጠርጥረው ታሰሩ

2 Comments

  1. ብሬ ቦታውን ካገኘ ስለም ቢሉት ሰልማል ቁጭ በል ቢሙት ይታዘዛል ችግሩ ስልጣኑን ይለምደውና አትኩሮቱ የአብይ ወምበር ይሆናል

  2. እኝህን ሰው የኢትዮጵያ ህዝብ አይንህ ላፈር ብሎ አትድረስብን ብሎ ፓርቲያቸውን ዘርሮ ሜዳ ላይ ጥሏል እሳቸውን ወደ ስልጣን ማምጣት ህዝብ ጋር ብሽሽቅ መግጠም አይሆንም?

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share