የህወሓት የጦር ጄነራሎች የኮንትሮባንድ እቃዎችን በወታደራዊ መኪኖች ጭነው ይሸጡ እንደነበር ተገለፀ

45

የህወሃት የጦር ጀነራሎች ቀረጥ ሳይከፈልበት የገባ ጐማና መሰል የኮንትሮባንድ እቃዎችን በይፋ በወታደራዊ መኪኖች ጭነው ይሸጡ እንደነበር የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ገለፁ፡፡

አሸባሪው ህወሓት በመሪነት ጊዜው የንግድ ባንክ፣ የልማት ባንክ እና ሌሎችንም የፋይናንስ ተቋማት እየመዘበረ ኢኮኖሚያዊ አሻጥር በመፍጠር የገንዘብ ምንጭ አድርጓቸው ቆይቷል ነው የተባለው፡፡

ይህም በጊዜው ለአሸባሪው ህወሃት ሰዎችና በህገወጥ ሰንሰለታቸው ውስጥ ለሚሰሩ አካላት የባንክ ብድር መስፈርት ሳያሟሉ ጭምር ከፍተኛ ብድር የሚወስዱበት፤ ህጋዊ መስመሩን ተከትለው የሚነግዱ ዜጎች ደግሞ ብድር ተከልክለው ንግዳቸውን እንዳያሳድጉ የተጠና ጫና የሚደረግበት የተዛነፈ የኢኮኖሚ ሚዛን እንዲፈጠር አድርጎ መቆየቱን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

የአሸባሪው ይህ አሻጥር ምርትን ሰውሮ ለማከማቸት፣ ዋጋን ለመወሰን እንዲሁም በጥቅል የንግድ መስመሩን ለመቆጣጠር ያስቻለ የአደገኛው አሻጥር ገጽታ እንደነበር መገለፁን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አሸባሪው በግብር ሥርዓቱ ውስጥ የራሱን ሰዎች አሰማርቶ በህጋዊ መስመር የሚነግዱ ነጋዴዎችን ከሚገባው በላይ ግብር በመጫን ከገበያ እንዲወጡ በማድረግ የራሱን ድርጅትና ደጋፊዎቹን ግብር ሳይከፍሉ የሃገርን ኢኮኖሚ እየጐዱ በነጻነት እንዲኖሩ አስችሏል ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡

በሌላ በኩል በሁሉም የሃገሪቱ ኬላዎች ማለት በሚቻልበት ደረጃም ከጦር ሰራዊት የተመለሱ የህውሃት አባላትን ብቻ በመመደብ እና ኬላዎችን እንዲቆጣጠሩ በማድረግ ከአሸባሪ ቡድኑ ህገ ወጥ ንግድ እና አሻጥር ጋር በጋራ የሚሰሩ አካላት ቀረጥ ሳይከፍሉ እቃዎችን እንዲያስገቡና እንዲያስወጡ በመፍቀድ በህጋዊ የንግድ ሰንሰለቱ የሚሰሩ ዜጐች ከውድድር ውጭ እንዲሆኑና እንዲከስሩ ያደርጉ እንደነበር ተገልጿል፡፡

የህወሃት የጦር ጀነራሎች ቀረጥ ሳይከፈልበት የገባ ጐማና የመሳሰሉት የኮንትሮባንድ እቃዎችን በይፋ በወታደራዊ መኪኖች ጭነው መርካቶ ላይ ይሸጡ እንደነበር የተገለፀ ሲሆን ይህ አሻጥር ትላልቅ የጦር መኮንኖች እና ፖለቲከኞችም የተሰማሩበት ነበር ተብሏል፡፡

አዲስ አበባ፣ መስከረም 272014 (ኤፍ ቢ ሲ)

1 Comment

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.