የዓማራ መደራጀት ለኢትዮጵያ አንድነት እና ሉዓላዊነት ዋስትና ነዉ !! – ማላጂ

የኢትዮጵያን የ5500 ዓመት የነጻነት እና የአብሮነት ታሪክ ለማዛባት እና አገርን ለማናጋት ጠላት በረጂሙ አስቦ እና አቅዶ ለዘመናት ከሚጠቀምበት የማደናገሪያ እና የማጥላያ ቅስቀሳ እና ወቀሳ (ፕሮፖጋንዳ) ዉስጥ ከመነሻዉ  ጠላቴ የሚለዉ ኢምፔራሊስት ኃይሎች፣ ፅዮናዊነት እና ዓማራ በሚል ፍረጃ እንደነበረዉ ዓለም ያወቀዉ ፤ ፀሃይ የሞቀዉ ዕዉነት ነዉ ፡፡

ከዚህ አንጻር ዓማራ በንቃት፣በበቂ ዝግጅት ፣ አንድነት እና ህብረት  በዕዉነተኛ ማንነት እና ኢትዮጵያዊነት ላይ መደራጀት እና መዘጋጀት ፋይዳዉ ለመላዉ ኢትዮጵያ ብሎም ለመላዉ አፍሪካ ሠላም እና መረጋጋት አብይ ጠቀሜታ አለዉ ፡፡

ኢትዮጵያዊነት እና ዓማራነት የማይለያዩ የአንድ ምንጭ ዉኃ ከአንድ ወንዝ የሚቀዱ ናቸዉ ፡፡

የዓማራ አደረጃጀት እና ህብረት መኖር እና መጠናከር የሚያቀዠዉ  ፀረ ኢትዮጵያነት አባዜ እና ደዌ የተጠናወታቸዉ  ዕብሪተኞች፣ አፍራሾችእና የጠላት ጌኞች መሆናቸዉን ለመረዳት ጠንቋይ መቀለብ አያስፈልግም ፡፡

ስለዚህ ማንም ኢትዮጵያዊ ሆነ ዓለም የማይክደዉ  ዕዉነተኛ የኢትዮጵያዉያን እና ኢትዮጵያ  ሠባዊ ባህሪ ያለዉ ሠባዊ ፍጡር እና  ሠባዊ አፍቃሪ የዓማራ መደራጀት ወይም አለመደራጀት የመላ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን ህልዉና የመቀጠል እና ያለመቀጠል  ዕድል  በመላዉ ኢትዮጵያዉያን እና በተለይም በዓማራ ህዝብ ዕጂ መሆኑን ነጋሪ እና መካሪ የሚያስፈልግበት ጊዜ ላይ አይደለንም፡፡

እናም የዓማራ ህዝብ መደራጀት እና ህብረት ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና ለህዝቦች አንድነት እና ደህንነት ዋስ እና ከለላ ስለመሆኑ ወዳጂ ቀርቶ ጠላት ከአንድ ክፍለ ዘመን ላላነሰ ጊዜ “ኢትዮጵያን ለማዳከም ዓማራን ማክሰም  ” በሚል ትዉልድ የማደናገር ፤ታሪክ የማወናከር ድርጊት ምስክር ናቸዉ ፡፡

ማንኛዉም ለአገር እና ህዝብ  ዕድገት ፣ ስልጣኔ  አስተማማኝ እና ዘላቂ  ሠላም እና ደህንነት አስፈላጊ የሚባል ህዝባዊ እና ዓማራዊ አደረጃጀት እና ህብረት  ሊደገፍ እና ሊታቀፍ ይገባል፡፡

ዕዉነተኛ ኢትዮጵያዊነት በዕዉቀት እና በአንድነት የሚረጋገጥ እንጅ  ለአንደበት የሚነገርበት ጊዜ ያለፈበት  ከንቱ ዉዳሴ ከመሆን አያልፍም፡፡

የዓማራ ህዝብ  ብዝኃነት  እና ኢትዮጵያዊነት ላይ ጉንጭ አልፋ ግልብጥብጥ  ድግግሞሽ  ነገረ ወሬ ቁሞ ተግባራዊ ዕርምጃዉን ለራስ እና ለህዝብ ህልዉና አቅም እና ሁኔታ በሚፈቅደዉ በአንድነት እና በህብረት ዘብ መቆም ሠዓቱ አሁን እንደሆነ አሁን ነዉ ፡፡

“ስለሌሎች የሚያስብ  የራሱ ክብር እና ማንነት ያሳስበዋል  ይህም የሚሆነዉ  በአገር እና በወገን ነዉ ፤ ከዚህ ዉጭ ራስ ወዳድነት( ዶሮነት- ላልበላዉ ጭሬ ላጥፈዉ ) ነዉ ፡፡”

 

ማላጂ

“አንድነት ኃይል  ነዉ ”

 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.