በእናትና በአባቱ አስከሬን መካከል ለተገኘው የሁለት ዓመት ህጻንና ወንድሞቹ የተለያዩ ወገኖች ድጋፍ እያደረጉላችው ነው

በአሸባሪው የህወሓት ታጣቂዎች በአንድ ቀን እናትና አባቱን አጥቶ በደም ተጨማልቆ በወላጆቹ አስከሬን መካከል ለተገኘው የሁለት ዓመት ህጻንና ወንድሞቹ በርካታ ወገኖች ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን የልጆቹ አጎት የሆነው ወጣት ጋሻው አለባቸው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ተናግሯል።

እስካሁን ድረስ ሶስቱን ህጻናት ለማሳደግ የሚረዳ 50 ሺህ ብር ከተለያዩ ግለሰቦች ተበርክቶልናል ብሏል።

ረጂ ተቋማትና ግለሰቦችም ለሶስቱ የሟች ልጆች የሚሆን ገንዘብ፣ አልባሳት፣ የምግብ፣ የትምህርት ቁሳቁስና ፍራሽ ድጋፍ ማድረጋቸውን ጨምሮ ገልጿል።

በአንድ ቀን እናትና አባቱን በአሸባሪው ቡድን የተገደሉበት እና በወላጆቹ አስከሬን መካከል በደም ተለውሶ የተገኘው የነፋስ መውጫው የሁለት አመት ህጻን እና ወንድሞቹን በተመለከተ “እናንዬን ድው አደረጋት” በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘገባ መስራቱ ይታወሳል።

በወቅቱ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢዎች በአሸባሪው ቡድን በግፍ የተገደሉት ነዋሪነታቸው በጋይንት ወረዳ ነፋስ መውጫ ከተማ የሆኑና ባልና ሚስት የነበሩት አቶ ደሴ ጌታቸውና ወይዘሮ ገነት አለብኝ ለቅሶ ላይ በመገኘት ምን እንደተፈጠረ ለመረዳት ጥረት አድርገዋል።

የህጻናቱ አጎት ወጣት ጋሻው አለባቸው ከዘገባው በኋላ በርካቶች በስልክና በአካል ተገኝተው ሀዘናቸውንና አጋርነታቸውን እንደገለጹላቸው ተናግረዋል።

ልጆቹን አይቶ የማያለቅስ የለም። ከመላው የሀገሪቷ ክፍል ስልክ በመደወል ጭምር የሚያጽናኑን በርካቶች ናቸውያለው ወጣት ጋሻውበወላጆቹ ሬሳ መካከል ነደም ተጨማልቆ የተገኘውን የሁለት ዓመት ህጻን ጨምሮ ሁለት ወንድሞቹንም እናሳድጋቸው የሚሉ ሰዎችም ነፋስ መውጫ ከተማ ድረስ መጥተዋል። ከአያትና አጎቶቻቸው ጋር ይደጉ በሚል የማደጎውን ሃሳብ ለጊዜው በይደር አቆይተነዋልብሏል።

በጌትነት ተስፋማርያም(ኢ ፕ ድ)
ተጨማሪ ያንብቡ:  ትኩረት መረጃ: የአዲስ አበባ ወጣቶች በ126ኛው አድዋ ክብረ በዓል ሳቢያ እየታደኑና እየታሰሩ ናቸው!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share