አማራን ከእልቂት ማን ይታደገው? (እውነቱ)

ኢትዮጵያ እንዳትፈርስ በሚል ቂላቂልነት በወያኔና ኦሮሙማ ሁለት አራጅ ሀይሎች በየአቅጣጫው እየታረደ በማለቅ ላይ ያለው አማራ መታረዱ የሚቆምለት መቼ ነው? መቼስ ነው ራሱ አማራው መታረዴ በቃ ብሎና ለነጻነቱ አንድ ሆኖ የሚነሳው? አማራው እየተለየ እየታረደ በማለቅ ላይ ያለው አማራ በመሆኑ ብቻ እንጅ በሀይማኖቱ እስላም ወይንም ክርስቲያን ስለሆነ ወይንም የወሎ፣ የሸዋ፣ የጎንደር፣ የጎጃም ሰው በመሆኑ አይደለም፡፡

240802190 2072947982856539 6717742798187647366 n 698x460
የሽብር ተግባሩ ወደር ያልተገኘለት አሸባሪው ህወሓት በአንድ ቀን እናትና አባቱን ገድለው በወላጆቹ አስከሬን መካከል ጥለውት የሄዱት የነፋስ መውጫው ህጻን

ለሰፊዋ ኢትዮጵያ እንጅ በአማራነቴ ጠብቤ አልደራጅም” የሚለው የወረደና የወቅቱን ሁኔታ ያላገናዘበ አስተሳሰቡ አማራውን እስካሁን እንዳልጠቀመው ሁሉ ወደፊትም ከእልቂት አይታደገውም፡፡ የሚፈልጋት ኢትዮጵያንም ከመፍረስ አያድናትም፡፡ በተለይ በወያኔ በኩል እየተደረገበት ያለው የአማራን ዘር ጠራርጎ የማጥፋት ወረራ ጉዳዩ የህልውና ጦርነት ስለሆነ ትግሉ በስሌት ተመርቶና በእልህና በብቃት ተመክቶ ወያኔ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተጠራርጎ እስካልጠፋ ድረስ በህዝቡ ላይ እየተደረገ ያለው የፖለቲካ “ቁማር” እጅግ በጣም አደገኛ ነው፡፡ በኦሮሙማ በኩልም በተረኝነት የተቀነቀነው የበላይነት ከወዲሁ እንዲቆም ካልተደረገ ሄዶ ሄዶ ውጤቱ ከወያኔው የማይተናነስ ስለሆነ በቃ መባል አለበት፡፡ጥያቄው ታዲያ ምን ይሻላል ከሆነ መልሱ መሆን ያለበት ‘የሚሻለውማ አማራው በራሱ ብቻ ጠንክሮ መቆም መቻል አለበትነው፡፡ ህዝቡ ጠንቅቆ እንደሚያወቀው የአማራ ክልል መንግስት ተብዬው የሆድ አደሮች ስብስብ ከአድርባይነት ስልጣኑ በትግል ተሽቀንጥሮ ካልወደቀና [[ከሆድ አደርነትና ተላላኪነት እንዲወጣ ብዙ ተጥሮና ተመክሮ ባለመስተካከሉ]] እንደዚሁም የተወስኑ የአማራ ፖለቲከኞች ነን ባዮች (ዝርዝራቸው ለህዝብ ይፋ ይደረጋል) ወያኔን ለመቃወም ከኦሮሙማ ጋር መወገንን ኦሮሙማንም ለመቃወም ከተወሽቁበት የወያኔ ጉያ አለመውጣትን እንደ ትግል ስልት አድርገው ከቀጠሉና እነዚህም ሀይሎች የአማራውን ትግል ማኮላሸታቸውን እንዲያቆሙ እስካልተደረጉ ድረስ ችግሩም አይፈታም፣ እልቂቱም አይቆምም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  አፍሮ ታይምስ ጋዜጣ ቁጥር 5 - PDF ከአዲስ አበባ

አማራ እንደከብት በሚታረድበት በዚህ ወቅት እንዴ መይሳው ካሳና፣ በላይ ዘለቀን የመሳሰሉትን የዱሮወቹን ዘመን አይረሳሽ ጀግኖቻችንን ወደጎን ብለን ትናንት በእኛው ዘመን የነበሩትን የትናንቶቹን እንደነ ፕሮፊሰር አስራት ወልደየስ፣ ዶ/ር አምባቸው መኮንንና ጄነራል አሳምነው ጽጌ ወዘተ የመሳስሉትን ብንመለከት እነዚህ ሰማእታት የቱን ያህል አስተዋይ፣አርቆ አሳቢና ጀግኖች የነበሩ መሆናቸውን እንገነዘባለን፡፡ “ሀኪም ነኝ፣ አውሮፕላንም አበርራለሁ፣ ነፍጠኛም ነኝ” ሲሉ ለባንዳው መለስ ዜናዊ በኩራት መልስ የሰጡት አማራውን አደራጅቶ ከተደገሰለት እልቂት ለማውጣት በያኔው የወያኔ ዘመን የመላው አማራ ድርጅትን የመሰረቱት ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ነበሩ፡፡ ፕሮፊሰሩን የታዋቂው ባንዳ የዜናዊ አስረስ ልጅ መለስ ዜናዊ አስሯቸውና ህክምና ከልክሏቸው ተንገላትተው እንዲሞቱ አድርጓቸዋል፡፡ በተረኛው ኦሮሙማ ዘመንም አማራው ስላልተሳተፈበት የወያኔ ህገመንግስትን የመቀየር ጥያቄ አላስፈላጊነቱን በሚመለከት አብይ ልጥቀስ ለአንድ ክልል ተብሎ አይቀየርምሲል በእብሪት ተናገረ፡፡ዶ/ር አምባችውም እንዲህ ሲል መለሰለት፡፡ልጥቀስ ” ህዝቡ ይህ ይህ ብሎ ነቅሶ ያወጣውና ያልፈለገው በሙሉ ይቀየራል”’ ብሎ ነበር በድፍረት መልስ የሰጠው፡፤ ከዚያም ዶ/ር አምባቸው በአብይ አህመድ ጥርስ ተነከሰበትና በአማራ ክልል ተደረገ በተባለ የመንግስት ግልበጣ ሰበብ በሴራ ተገደለ፡፡ ከዚሁ የመንግስት ግልበጣ ከሚባለው የኦሮሙማ ሴራ ጋር በተያያዘም ግልበጣውን መርቷል የተባለው ጀኔራል አሳምነው ጽጌም አሁንም ደግሜ ልጥቀስ “ አማራው ከ500 አመት በፊት ደርሶበት ከነበረው መከራ የሚበልጥ እልቂትና መከራ እየመጣበት ነውና አንዲነቱን ጠብቆ ለዚሁ አይቀሬ እልቂት መደራጀት አለበት”’ ብሎ እንደ ነብይ የተናገረው ጀኔራል አስምነው ጽጌም በዚሁ ሴራ ተገድሏል፡፡ ሌሎችም እንደ ጅግናው ምግባሩ ከበደ (ስለአዲስ አበባ ጉዳይ በተናገረው) በዚሁ የመንግስት ግልበጣ ተብዬ ሴራ ተገድሏል፡፤ እዚህ ላይ አያሌ ስማቸውን አሁን ለመዘርዘር ያልቻልኳቸው ብዙ የፋኖ አማራ አርበኞች በፊት በወያኔ ኋላም በተረኛው ኦሮሙማ ገዳይ ቡድኖች እንደዚሁም በሆዳሙ የአማራ ክልል ባለስልጣናት እየታደኑ ተገድለውል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ለአዲስ ግጭት ዝግጅት መኖሩን ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ሂውማን ራይትስ ዎች አመለከተ

ወያኔ በአማራና አፋር ህዝብ ላይ ጦርነት ከፍቶ ላደረሳቸው እልቂቶች በመንግስት በኩል የተወሰደው እርምጃ እጅግ የሚያሳዝን ነው፡፡ መንግስት መጀመሪያ የትግራይ ገበሬ አርሶ እንዲበላ በማሰብ ትግራይን ለቅቄ ወጣሁ አለ፡፡ ቀጥሎም ወያኔ ዱቄት ሆኖ በንኗል ከባድ መሳሪያም የለውም አለ፡፤ወያኔ ግን ትንሽ እንኳን ሳይቆይ በከባድ መሳሪያወች በመታጀብ አማራንና አፋርን ወረረ፡፤ከዚያም የመንግስት ጦር ትጥቁን እያስረከበ እንዲያፈገፍግ ታዘዘ፡፤ ህዝቡም ጦሩን ትታችሁን አትሂዱ አድኑን ብሎ ቢለምንም ጦሩ ከበላይ አልታዘዝንም እያለ ትጥቁን እያስረከበ ለቅቆ ወጣ፡፡ይህም በመሆኑ ወያኔ እጅግ ሰቅጣጭ የሆኑ እልቂቶችን በህዝብ ላይ አደረሰ፡፡የሰውን እልቂት እዚህ አናነሳውም፡፡ወያኔ ከብቶችንም የአማራ ናችው ብለው በመርዝና ጥይት ፈጇቸው፡፡

ወያኔ ይህንን ጦርነት ለምን ጀመረው ብለን ብንጠይቅ የምናገኘው መልስ አንድ ብቻ ነው፡፡ ይሄውም ወያኔ በህልሙም በቁሙም የሚቋምጥለትና የዘለአለም ቅዠቱ አማራው በደሙ ዋዥቶ ያስመለሳቸውንና ታሪካዊ የአማራ ርስቶች የሆኑትን የራያና የወልቃይት ለም የአማራ መሬቶችን መልሶ በመውሰድ ታላቋ ትግራይ የምትባል ነጻ አገርን ለመመስረት ነው፡፡ከዚያ በኋላም ወደ ሱዳን መውጪያና መግቢያ በሩን ተቆጣጥሮ ኢትዮጵያን እያደሙ ለመኖር ነው፡፡ይህንኑም በድል ካሳካ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ታማኝ ተቀጣሪና ተላላኪ ባንዳነቱ በጌቶቹ ይረጋገጥለታል፡፡ለዚህ ቅዠቱ መልሱ አጭር ነው፡፡ ወያኔ እነዚህን ለም የአማራ መሬቶች ለዘለአለም አያገኛቸውም፡፡ ያኔ በባንዳነቱ ስለመላላክ ስራውና ቅጥሩ ጉዳይ ጌቶቹን ይጠይቃል፡፤

በመጨረሻም ሁለት ወሳኝ ማስጠንቀቅያወችን ይፋ እናድርግ፡፡ አማራ ሆይ፡፤ በአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብንዙሪያ ተሰባሰብና ፖለቲካህን አጥራ፡፤ ፋኖንም እየተቀላቀልክ ትግልህን አፋፍም፡፡ ለአንተው መዳን መፍትሄው አንተው ብቻ መሆን እንዳለብህ ሁኔታወች ግድ ይላሉ፡፤ ግፊቱ ከፌደራልም ይሁን ከአማራው ክልል መንግስት በአሁኑ አስቸጋሪ የህልውና ጦርነት ወቅት ለህዝብ አለኝታ በሆነው በፋኖ አደረጃጀት ውስጥ አላግባብ ገብቶ ነገር ማበላሸት የሁሉም ነገር የመጨረሻው መጨረሻ እንዳይሆን መንግስት በቶሎ እርምት መወሰድና ከዚህ ድርጊቱ መቆጠብ እንዳለበት ልናስጠነቅቅ እንወዳለን፡፡

የአማራ ህዝብ በአሸባሪው ትህነግ እና ኦነግ-ሸኔ የደረሰበት ስቅይ

1 Comment

  1. አቶ እውነቱ፦ ያቀረብከው ትንታኔ በሙሉ ልክ ነው፡፡ ኦሮሙማና አንተ የዘነጋሀው ቤንሻንጉል ጉምዝ ተብየወም (በኦሮሙማ ውስጡን እየታገዘ) እንደ ወያኔ የአማራን ዘር ጨርሶ ከምድር ላይ ለማጥፋት ባይዘምቱበትም በስልት አማራን እያደቡና እያሰለሱ እየፈጁት ነው፡፡ ስለሆነም ከእልቂቱ ለመዳንና ችግሩን ከስሩ ለማጥፋት ሌላ ማንም ሳይሆን አማራው ራሱን አደራጅቶ ከተቻለ በመሳሪያና ስልጠና የውጭ አገር ትብብርና እርዳታ ለማግኘት( ምሳሌ ከኤርትራ ጋር) ጥረቶቹን አስፍቶ እስከመጨረሻው ድል ድረስ መፋለም አለበት፡፡ በአጭሩ እንዳልከው አማራን ያለእራሱ ማንም አይታደገውም፡፤ ከአብይ አህመድ ጋር እሽኮለሌ እየተጫወቱ በወሎ አማራ ህይወት ላይ መቆመሩ የማያሳፍራቸው የብአዴን {አማራ ብልጽግና) ሆዳሞችና እንደዚሁም ሌሎች ምሳሌ እንደ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት አይነቶቹ (ኢንጅነር ይልቃል “”ጦርነቱ የህልውና አይደለም ይልቅስ ትግራይ እንዳትገነጠል ….ወዘተ እያለ መግለጫ ሲሰጥ ስለሰማሁ እንደዚህ አይነቶቹ ብዙ ጉዳት ከማድረሳቸው በፊት አንድ ሊባሉ ይገባል፡፤ ሞት ምንጊዜም ያው ሞት ነው፡፤
    አንድ ብዬ ላብቃ፦
    ጠላትማ ምንጊዜም ጠላት ነው
    አስቀድሞ መግደል አጎብጓቢውን ነው
    ይላል ወገኔ ሲፎክ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share