ህዳሴ ግድብን ለማደናቀፍ ማሰብ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ጉዳይ እንደማይደራደሩ ካለመረዳት የሚመነጭ ነው – ሌ/ጄ አስራት ዴኔሮ

242459655 4817529804945524 589096009719269987 n

የምድር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል አስራት ዴኔሮ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖች ታላቁ የህዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ፣ ለፕሮጀክቱ መሳካት እየተከናወነ ያለውን እረፍት አልባ የሰራዊቱ የግዳጅ አፈፃፀም አድንቀዋል፤ ምስጋናም አቅርበዋል።
ጄነራል መኮንኑ በጉብኝቱ ወቅት የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክትን ለማደናቀፍ ማሰብ ኢትዮጵያውያን በሃገራቸው ጉዳይ እንደማይደራደሩ በቅጡ ካለመረዳት የሚመነጭ ነው ብለዋል።
አክለውም ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማስተጓጎል ከውስጥም ሆነ ከውጭ የሚንቀሳቀሱ የውክልና ጦር አስፈፃሚ ቅጥረኛ ኃይሎች መቼም አይሳካላቸውም ማለታቸውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የፌስቡክ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
EBC

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.