በአሸባሪው ሸኔ ላይ በተወሰደው እርምጃ እስካሁን 373 የቡድኑ አባላት ተደምስሰዋል፦ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን

Oromia Police 633x440 በአሸባሪው ሸኔ ላይ በተወሰደው እርምጃ እስካሁን 373 የቡድኑ አባላት ተደምስሰዋል፦ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽንበአሸባሪው ሸኔ ላይ በተወሰደው እርምጃ እስካሁን 373 የቡድኑ አባላት መደምሰሳቸውን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በወቅታዊ የክልሉ ሁኔታ ላይ ያተኮረ መግለጫ ለሚዲያዎች ሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል አራርሳ መርዳሳ፣ አሸባሪው የሸኔ ቡድን ለኦሮሞ ሕዝብ ደንታ የሌለው እና የአሸባሪው ሕወሓት ተላላኪ ነው ብለዋል። የኦሮሚያ ክልል ሕዝብ ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን የክልሉን ሰላም እያስጠበቀ መሆኑን የገለጹት ኮሚሽነር ጄኔራል አራርሳ መርዳሳ፣ መንግሥት በአሸባሪው ቡድን ላይ በወሰደው እርምጃ 373 የሸኔ ቡድን አባላት ተደምስሰዋል ብለዋል።

መንግሥት የተኩስ አቁም ባደረገባቸው ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ አሸባሪው ሸኔ በ210 ሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሱን እና ወደ ሁለት ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረትንም እንዳወደመ ኮሚሽነር ጄኔራሉ ገልጸዋል።

የሕወሓት እና የሸኔ የሽብር ቡድኖች ጥምረት ሀገርን ለማፍረስ መሆኑን ተገንዝቦ ሕዝቡ እነዚህ ሁለቱ የጥፋት ቡድኖችን ለማጥፋት ሊታገላቸው እንደሚገባም ጠቁመዋል።

እንደ ኦቢኤን ዘገባ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን የክልሉን ሰላም ለማስጠበቅ እየሠራ መሆኑን እና በዚህም ውጤት እየተገኘ መሆኑን ኮሚሽነር ጄኔራል አራርሳ መርዳሳ ገልጸዋል።

የኦሮሞን ሕዝብ ጥቅም እናስከብራለን በሚል በተሳሳተ መንገድ ወደ ሸኔ የሽብር ቡድን የተቀላቀሉ የኦሮሞ ወጣቶች የቡድኑን ሴራ ተገንዝበው በሰላም ወደ ኅብረተሰቡ እንዲቀላቀሉም ጥሪ አቅርበዋል።

መላው ኅብረተሰብም እንደ ከዚህ ቀደሙ ከመንግሥት ጎን በመቆም እነዚህን የሽብር ቡድኖችን እንዳስወገደው ሁሉ አሁንም ድጋፉን አጠናክሮ የክልሉን ሰላም ማስጠበቅ እንደሚጠበቅበትም አስገንዝበዋል።

4 Comments

  1. Judging from OPDO’s usual reports, 373 is most probably the number of Amhara civilians murdered and not of OLA or Shene attackers killed.
    When will the OPDO (Oromo Prosperity Party ) leaders stop their jest with the public? Every time there is a genocide against the Amhara in Oromiya or Benshangul Gumuz, the authorities come up with fabricated news of destroyed terrorists.
    God will punish you for this nasty joke on victims. You are abusing your authority to govern the people.

  2. አረ ተው አትቀልዱብን ኣነግ ሸኔ ከዚህ ቁጥር በላይ ዜጋ እየቀጠፈ 373 ገደልን ብላችሁ ታላግጡብናላችሁ እስቲ ይሁና የፍርድ ቀን እስኪመጣ።

  3. መቀባባቱን፤መሽኮርመሙን ት ታችሁ ሸኔን -ኦነግ ሸኔ፤ ጁንታን -ትህነግ ወይም ህወሀት ብላችሁ የመጥራት ድፍረት ይኑራችሁ።

  4. The Mother of this lingering problem is the ethnic rule introduced by Woyane and implemented over 3 decades now, and still ongoing despite the talk about reform. The very people who are fighting OLF are organized along ethnic lines themselves but as Anistien said’ You can not solve a problem in the same box it was crated’. You have to get out of the box to find lasting solutions. The question is, are our leaders ready to change? The people of Ethiopia in all corners of the country have shown their readiness in this regard. Time for our leaders to read the ‘writing on the wall’ before it is too late.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.