ለምን ጌታቸው ረዳ “ትርትሩ ነኝ።ከመቀሌ!” ብሎ አይዘግብም? – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ   

getachew
getachew

“If you tell a lie big enough and keep repeating it, people will eventually come to believe it. The lie can be maintained only for such time as the State can shield the people from the political, economic and/or military consequences of the lie. It thus becomes vitally important for the State to use all of its powers to repress dissent, for the truth is the mortal enemy of the lie, and thus by extension, the truth is the greatest enemy of the State.”–

Joseph Goebbels

የጌታቸው ረዳ ቀደዳ ከሂትለሩ የፕሮፖጋንዳ ኃላፊ ዮሴፍ ጉብልስ (Goebbels, The Master of Lies ) እጅግ ይልቃል ፡እናም አከዚህ ትርትርነት ተነሥቼ ፣ የህሊና ቢሶቹ የትግራይ ፕሮፖጋዲስቶች ውሸት የሰው ስጋ ከሚበሉት አውሬዎች ህሊና ጋራ ይመሳሰላል ማለት እችላለሁ ። በቁመና ሳይሆን በአሥተሣሠብ  ፡፡ ” ሰማይ ላይ እህል ሲወቃ እብቁ ዐይኔ ገባ ፡፡ ” በሚል ውሸት እኮ አያበቁም ፡፡ የውሸት  መርሐቸው ግን ከላይ የጠቀስኩት የዮሴፍ ጉብልስ መሆኑን አንባቢ ተገንዘብ ፡፡

ዛሬ ይባስ ብለው ፣ ድሮን ጣልን ሲሉ ጎብልስ ቢኖር ኖሮ ” አቤት ውሸት ! ” ይላቸው ነበር ፡፡… ፡፡ ገና ለገና አነፍናፊው ድሮን ያለንበትን አውቆ ሊደመሥሠን ይችላል ብለው በመፍራት እኮ ነው የሚቀደዱት ፡፡

በደም የተጨማለቁ ነፍሰ ገዳዮች ነፍሳቸውን  ለማቆየት እንዲህ ሲቀላምዱ ። የትግራይ ደሀ ልጅ ( የገበሬና የከተማ ነዋሪ ) ምንም ትርጉም ለማይሰጥ ከወንድሙና እህቱ ጋር እየተጋደለ ያልቃል ። ያውም በሆዱ እና በእናት ፣ በሚሥቱ ና በልጆቹ እያሥገደዱት ። የእሱ ከንቱ እልቂት  ቅንጣት ያህል  አይዘገንናቸውም ፡፡ ትላንትም በደሀ ሞት እንደበለጸጉ ሁሉ ዛሬም በትላንት መንገድ ቀጥለዋል ፡፡ ያውም እነደማይሳካላቸው እያወቁ ፡፡

አገራችን የያዘቸውን ሀብት እንጂ  መኖራችንን ለማይፈልጉ እና አፍሪካዊያንን እንደአልሰለጠነ ህዝብ ለሚቆጥሩ ፤ በገንዘብ ተገዝተው በአገራችን የማያባራ የእርስ በእርስ ጦርነት እንዲነግስ እና አገር አልባ ህዝብ እንዲፈጠር በብርቱ እየሰሩ ነው  ፡፡ ኦነግ ሸኔ እራሳቸው ናቸው ፡፡ በውሸታቸው አንፎገር ፡፡… ይኸው ዛሬ ደሞ  ድሮን ጣልን አሉ ፡፡ የዛሬ 10 ወር በናጎርኖ ካራባክ ግጭት አርማንያ ስትጠቀምበት የነበረውን እና የተከሰከሰውን ድሮን እያሳዩን  ድሮን ጣልን ይሉናል ።

60 % የሚሆነውን አየር ኃይላችንን እና 60% ታንክ እና ሠራዊታችንን ካወደሙብን ኢትዮጵያ ምን ቀራት ?

ታዲያ እነ ጌታቸው ከጆሴፍ ጎብልስ በውሸት አልበለጡም ትላላችሁ ? ለምን ጌታቸው ረዳ ” ትርትሩ ነኝ ። ከመቀሌ ! ” ብሎ አይዘግብም ?

(What Armenians using against the Turkish-made Bayraktar TB-2 attack drones in Nagorno Karabakh )  ብላችሁ ዩቲዩብን ጠይቁ የወደቀውን ድሮን ታያላችሁ ።

2 Comments

  1. እረ እባካቹህ እግዜአብሄር ፍሩ። ከትግራይ የመከላከያ ሰራዊት የነበረው አስረክቡ እስከሚወጣ ያደረገ ሃይል። የ አማረ ክልል ወልድያ ላሊበላ የሚያህሉ ታዋቂ ከተሞች አሸንፉ ከወሰደባቹህም በሃላ ይህንን የማይረባ ንግግር ከምትናገሩ። ምንም ማድረግ ከማይችልበት ደረጃ ላይ ነው ያደረስነው ያልቹህ ጠቅላይ ሚንስተርና የመከላከያ ሚንስተር ልምን አትጠይቁም። ይህ ሁሉ ከባድ መሳርያ ታንክ ከየት አመጣው ብላቹሁ።

    • እቅጭ። እነሱ ቢቦተለኩ የልባቸውን እየሰሩ ነው። እንዴያው እንተዛዘብና ይቺን ቦለቲካ የጣፍካት እንዲያው ደህና ብትር ደህና ሽጉጥ አለችህ የሆን? ባዶ ምላስ እኮ ነን።ኤዲያልኝ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.