ከደሊላዊ  ወጥመድ  እንጠንቀቅ !! – መኮንን  ሻውል  ወልደጊዮርጊስ

አሜሪካ ለደሀ አገሮች ሁለንተናዊ ዕድገት ና ብልፅግና ደንታ የላትም ፡፡ የአፍሪካ አገራት ህዝቦች  ከጉስቁልና ተላቀው ሳቢ ውብት እንዲኖራቸው ከቶም አትፈልግም ፡፡አሜሪካ ለራሱ ና ለከበርቴዎቹ አማላይ ውበት ተጨናቂ  የሆነ ደሊላዊ ባህሪ ያለው መንግስት ያላት አገር ናት ። የደሊላን ማንነት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ታገኘዋለኽ  ( መፀሐፈ መሳፍንት ምዕራፍ 16 ን አንብብ  ። ) በቱጃሮችዋ የምትዘወረው ደሌላዋ አሜሪካ በተካነችበት ደሊላዊነት እንደ መፅሐፍ ቅዱሱ  ሳምሶን አዋዝታ የደሃ አገርን ፀጉር ላጭታ ፤ በአዋራጅ እግር ብረት ማሳሰር ልማዷ ነው ። እገር ከታሰረ ና ለጠላቶችህ መሳለቂያነት ከተዳረግህ  በኋላ ፣ ፈጣሪን የምትማጸነው  “ እባክህ አምላኬ አሥረው እያሰቃዩኝ ካሉት ጠላቶቼ ጋር አብረህ አጥፋኝ ። “ እያልክ ነው  ። ለዘመናት አሥረው ከሚሳለቁብህም የሳምሶን ሞትን ብተመርጥ ማን ይፈርድብሃል  ?

እንዲህ አይነቱን መሰሪነት ፣ አኩሪ ታሪክ ባላት አገርህ በኢትዮጵ ላይ ለመተግበር በአውዳሚ የጦር መሳርያ ባለቤትነቷ የምትተማመነው አሜሪካ በተለመደው ደሊላዊ ባህሪዋ የውስጥና የውጪ ጠላት አሰማርታ ግልፅ በሆነ ኢ – ሰብኣዊነት እየተንቀሳቀሰች ነው ፡፡ ይህ አገርን እና ህዝብን የሚዋርድ የአሜሪካ መንግስት እንቅስቃሴ  በቀደኛ ተባባሪው ፤ በትግራይ ህዝብ ሥም በሚነግደው ባንዳ ቡድን ተግባራዊ ከመሆኑ  በፊት ግን ፣ ዛሬ ና አሁን አንተ አርበኛው ጀግናው ኢትዮጵያዊ ፣ ለአገርህ ክብርና ህልውና ለመሰዋት ታላቁን ሴራ ማክሸፍ ይጠበቅብሃል ፡፡  ኢትዮጵያ ሊያስገብሯት የቆመጡትን ሁሉ ትላንትና ፣ድል አድርጋለች ፡፡  በሃፍረት ወደ መጡበት መልሳቸዋለች ፡፡  ዛሬም የኢትዮጵያ ጠላት የሆኑትን  ባንዳዎች ፊት አስቀድመው ከኋላ እየወጉን ያሉትን ፣ ለብዝበዛቸው ቀጣይነት የሚሟሟቱትን የጀግኖቹ ልጅ የዛሬው ትውልድ ከኢትዮጵያ ምድር ያጠፋቸዋል ፡፡ አትጠራጠሩ ፡፡

የዛሬው ትውልድ ፤ ዛሬ ና አሁን ፣  የአሜሪካ መንግስት ” በደሊላዊነት ”  በአፍጋኒሥታን ሠላማዊ መሪ ና ህዝብ   ላይ  የፈፀመው ሸፍጥ፣  ትልቅ ትምህርት ይሰጠዋል ብዬ አምናለሁ ፡፡ የአሜሪካ  የሸር ሥራዋና ፉገራዋ በሙሉ፣  የሚተገበረውና  የሚከወነው በደሊላዊነት መሆኑን ምንጊዜም አትርሳ ፡፡  ደግሞም ፣ አሜሪካ በሲአይኤ አማካኝነት  በየደሀ አገሩ  አያሌ ለብዝበዛ የሚመቻምቹ ደሊላዊያን   በብዛት እንዳሏት አትዘንጋ !!

ደሊላዊያኑ ፤  በዶላር  በማማለል ህሊናን የሚያሸጡ ከመሆናቸውም በላይ፤  ደካሞችን በባትሪ እየፈለጉ፣  የብዝበዣቸው አጋር በማድረግ ይታወቃሉ ፡፡ በሙስና የተጨማለቁ ኢትዮጵያዊያንን አሜሪካዊ ዜግነት  እንዲያገኙ በማድረገ ሀብት ማሸሽም የዘወትር ተግባራቸው ነው፡፡  አገርን በዝብዘው  የሚያሥበዘብዙ ።  በልዩ ጥቅማ ጥቅም ህሊናቸውን ሽጠው የአገርን ቅርስና ክብር  እንዲጠፋ በማድረግም የተካኑ ናቸው፡፡ …   ውጫቸው ሲታይ መልአክ የሚመሥሉ … ውሥጣቸው ግን እንደ ዳቢሎሥ ጨካኝ የሆነ ፤  ለአሜሪካ ከበርቴዎች ዘረፋ መንገድ ጠራጊ ወኪሎችን በሥፋት የጥሬ ሀብት ጥቅም በሚያገኙበት ለመበልጸግ በሚታትር አገር ውስጥ  ሁሉ በማሰማራትም የታወቁ ናቸው።

አሜሪካ በገዘፈ ሀብቷ የተብለጨለጩ ፣ አማላይ የገንዘብ አቅም  ያላቸውን ደሊላዎች በመላው ደሃ አገር አሰማርታለች።  እነዚኽም  ፍቅር ሳይኖራቸው ፣ አፍቅረናል ብለው ያዙኝ ልቀቁኝ በማለት የሚያወናብዱ ፣ የሚያጭበረብሩና በአዞ እንባ አንቢነታቸው የሚታወቁ አጭበርባሪዎች ናቸው ፡፡ እንደ ደሊላ የሆነ መልክ ያላቸው …።  ( በሰው አፍቃሪነት ፣ በፍትህና ርዕት ወዳድነት የተሽሞነሞነ ቃላትን የሚያዘንቡ ሐሳዊ መሲህ የሆኑ ህቡ ወኪሎችን የትም አስርገው ለማስቀመጥ የሚችሉ ፡፡)  የሚፈልጉትን ካሳኩ በኋላ ” አራት እግርህን ብላ ! ” በማለት ወደሀገራቸው እብስ ሲሉ ካልሆነ የማይታወቁ ፡፡ … የአሜሪካንን ቱጃሮች ጥቅም ብቻ የሚያሥጠብቁ ፤ ሆኖም ይህንን ዓላማቸውን በሰብአዊ መብት፣  በዴሞክራሲ ና በነፃነት ሥም ሸፍነው በሥውር የሚንቀሳቀሱ ማሽንክ ናቸው ። ደሊላዊያኑ ፡፡

አሜሪካ የትም አገር በማይታጡ ፣ በአማላይ ደሊላዎቿ  እያዋዛች፣ ጎዋዳህ ድረስ ሰተት ብላ በመግባት የምትፈልገውን ካገኘች በኋላ ለብዝበዛዋ የማይመች እንቅፋት ከገጠማት ወይም ደግሞ የብዝበዛ ተልኮዋን ከፈፀመች ከመቅሥፈት  እንደምተሸበለል የቅርብ ጌዜ ታሪኳ ይመሰክራል።  ለብዝበዛ የቆመጠ ዓይኗ ላይ  በሩን ከርችሞ አገሬን አላስበዘብዝም ባለ መንግስት ላይ፣ በበዝባዥ ከበርቴዎቾ ሚዲያ አማካኝነት በቅጥፈት ወሬ ብዛት ዓለምን በማደናገር በዓለም ህዝብ ፊት ያ የደሀ አገር መንግስት ሥሙ በመጥፎ እንዲነሳ ከማድረጓም በላይ እኔ የዓለም ፖሊስ ነኝ ብላ በሀሰት ትርክቷ ተደግፋ ልታጠፋው ትነሳለች።  በበዛ ጡሩንባ የዓለምን ህዝብ በውሸት ፕሮፖጋንዳ ስላደናገረችም የሚቃወማት እንብዛም አይኖርም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደተለመደው ይወርፏቸዋል፤ እንደራሴዎቹ ግን በሳቅ ያጅቧቸዋል - ከመርሐጽድቅ መኮንን አባይነህ

(ሲኤንኤን ፣ ሮይተር፣  ቢቢሲ ወዘተ።  ሥለ አገርህ የእርስ በእርስ ጦርነት ሲያወሩ የአገርኽ መንግሥትን እንደሌለ ቆጥረው፣ አገር ለማፍረሥ ከሸፈተው ፣ ከ80 በላይ ቋንቋ በሚነገርባት ኢትዮጵያ ፤   በአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ሥም በመንቀሳቀሥ የዘረኝነት አረምን ለመትከል  ከሚተጋው ጭራቅ ከሆነ ቡድን ጋር ወግነው እንደሆነ፣ ስትገነዘብ፣ እውነቱን በግልጽ ትረዳለህ ።)

ደግሞም፣ ደሊላዊቷ  አሜሪካ ፣ ማሽንክ ናት ። እባብ ፡፡ በዓለም ላይ ባሉ ደሀ አገራት ሁሉ  ተበዝባዢ መንግሥት እንዲኖር ሥለምትፈልግ ፤ ነገረ ሥራዋ ሁሉ እንደ እባብ ካብ ለካብ ነው።  ከብ ለካብ እየሄደች ለቱጃሮቿ የሚሆን ግዳይ  ትጥላለች። ደሊላነቷን ሳታሥነቃ ። በእርሷ የበላይነት ወይም የገንዘብ ድጋፍ የሚንቀሳቀሱ ዓለም አቀፍ ባንኮች   በላይ በላዩ ብድር እንዲያበድሯቸውም በማድረግ ፣ መክፈል በማይችሉት ዕዳ ትዘፍቃቸውና በእጅ አዙር ባርያ ታደርጋቸዋለች። ደሃ ና አቅመ ቢስ መንግሥት በማድረግም፣ የእርሷ ፈቃድ ፈፃሚ ሎሌዋ ይሆናሉ  ።

አንገቱን ያቀና ለአገሩ ብልፅግና ብቻ የሚሰራ የደሃ አገር  መንግሥት በየትኛውም ደሃ አገር እንዲኖር አሜሪካ ከቶም አትፈልግም ። ይኽም በምታደርገው እርዳታና ድጋፍ ይገለፃል ፡፤ ለአፍሪካ አገሮች የምታደርገው ድገፍ ከዳቦ ልመና የሚያወጣቸው ሳይሆን ፤ ሆድን ለመደለል የሚውል ብቻ ነው ፡፡ ” ዕድሜ ለአሜሪካ የሚያሰኝ የፉገራ ዕርዳታ ። ”  የምታበድረውም ብድር ለመበልፀግ የማያሥችል ፣ የበለጠ የእርሷ ጥገኛ የሚያደርግ ነው ። በረጂ ድርጅቶቾም አማካኝነት እንደ ፈጣሪ እንድትታይ እየጣረች ፣ በጎን ደግሞ ለብዝበዛዋ ያልተመቻቸላትን መንግሥት ከሥልጣን ለማውረድ ተቃዋሚዎችን ከሥንዴ ጋር ቀላቅላ በላከቻቸው የሲአይኤ ቅጥረኞች ማደራጀት፣ ማሠልጠንና ትጥቅ ሰጥታ ማሰማራት የተለመደ ሴራዋ ነው። …

የሴቶችን እኩል ተጠቃሚነት ለማሳደግ ፣ ድሆች በልተው እንዲያድሩ፣ ” ሴፍቲ ኔት ” በማለት የደሃ አገርን ህዝብ በማደናገር ደሊላዊ ፍቅሯን ሁሌም ታሳያለች ፡፡ ህዝብ የአሜሪካንን ሥንዴ ጠባቂ እንዲሆን በማድረግ   ደሀን በሆዱ የመያዝ  ስልቷ ዛሬም ቀጥሏል ፡፡  የዓልሚ ምግብ እና የሥንዴ እርዳታ ደሀ አገርን አያበለጽግም ፡።  የብድር ባርያ የሆነ መንግሥት መፍጠርም አገርን አያለማም ። …

ወደጄ ፣ አሜሪካ የደሃ አገራት መንግሥታት የእርሷን ፈቃድ ፈፃሚ ፣ ታዛዥ ሎሌ እንዲሆኑ እንጂ  በአገር ፍቅር ሥሜት የጋሉ ፣ ብዝበዛን ተፀያፊ፣ የልማት ና ብልጽግና  አርበኞች እንዲሆኑ ከቶም አትፈቅድም ።

አሜሪካም ሆነች የቀድሞ  የአፍሪካ ቅኝ ገዢዎቻችን ፤ አገራቸውን ለማበልፀግ ቆርጠው የተነሱ አራት ዐይና መሪዎች በአፍሪካ ከተፈጠሩ ቶሎ ብለው ያጠፏቸዋል።… ለእነሱ ብዝበዛ የሚመቹ ፣ የራሳቸውን ህዝብ እርስ በእርስ በማጋጨት የሚታወቁ ፣ ዘረኛ ና አምባገነን መንግሥታትን የለሥማቸው ሥም በመስጠት ያቆላጵላጥሷቸዋል። በዚህም መንገድ ፣ አምባገነኖቹ የአፍሪካ መንግስታት፣ በግብዝነት በመመጻደቅ ፤ የድህነት ሸምቀቆውን  በህዝባቸው ላይ የበለጠ  እንዲያጠብቁ ያተጓቸዋል ፡፡ አገርን ተመፅዋች  በማድረግ አገረ መንግስቱንም ወደፈቀዳቸው መንገድ  የሚጋለብ ገራም ፈረስ  ያደርጉታል ።

( የዛሬዋን ትግራይን እና የቀደመውን የወያኔ አገዛዝን ተመልከት ። የዳቦ ጥያቄ ያልተመለሰለትን ህዝብ ነው በሆዱ ሰበብ ለጥፋት አላማው ፣ ሲጋልበው የነበረ ። …  የሚልሰው ና የሚቀምሰው የሌለው ና ሥለዓለም ፖለቲካ አንዳችም ዕውቀት ወይም ግንዛቤ የሌለውን ተርታውን ህዝብ ለእኩይ አላማው ወያኔ ማሰለፉ  አይገርምም ፡፡ በችጋር የሚሰቃይ ህዝብ ምንጊዜም ዳቦ እሰጥሃለሁ ካለው ጎን ይሰለፋል  ። ምናልባት ጥያቂ የሚጀምረው በህይወት ሰንብቶ ፣ የዕውቀት ጮራ ሲያገኘው ና ከዳቦ ችግር ሲላቀቅ ብቻ ነው ። በአገርም ሁኔታ ብታየው ይኸው ነው ። ደሃ አቅመ ቢሥ ነው ። …)

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጆሲ ሚዲያን “ፈይሣ አዱኛ” ይይልህ! - ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

የአሜሪካ መንግሥትም ሆነ አንዳንድ የበለፀጉ የዓለም አገራት በዓለም ላይ ያሉ ደሃ አገራት በሙሉ በአምሥት ዓመታትት   ከድህነት እንዲላቀቁ ለማድረግ የሚችል አቅም አላቸው።  ይኑራቸው እንጂ እጅግ ሲበዛ ስግብግቦች ና አስመሳይ ኃይማኖተኞች በመሆናቸው አይናቸው የዛሬ 200 ዓመት ጀምሮ እጅግ ከተጠናወታቸው የጥሬ ሀብት  ብዝበዛ ሥላልተነቀለ የሚታያቸው የአፍሪካ እንቁ ፣አልማዝ ና መአድናት ብቻ ነው። እናም እያንዳንዱ ባለፀጋ አገር የደሃ አገራትን የአምሥት አመት በጀት የሚሆን ብር ለወታደራዊ በጀት  እያወጣ እርስ በእርሱ ትከሻ ለትከሻ ይገፋፋል  ። ( ለምርምር ሥራ ፣ ለጦር መሣሪያ ና ለሎጀሥቲክ ቢሊዮን ዶላር በሀብታሞቹ አገራት ይበተናል …) ከዚህ የጥፋት ወጪ ግማሹን እንኳን ቀነሰው  ለአፍሪካ ብልፅግና በብድር መልክ በመስጠት ለልማት ሥራ  ቢያውሉት ና በህበረት ተቀናጅተው በመሥራት ደሃ አገራትን ለማበልፀግ  ቅን ልቡና  ቢኖራቸው ኖሮ ውብ የሆነች ዓለምን ለመፍጠርና ችጋርን እና ድህነትን ከአለም ማጥፋት ይቻል ነበር ።

በዚህ ረገድ የበለፀጉት አገራት ሲገመገሙ ፣ በህሊና አንፃር የቀጨጩ ና እልም ያሉ ማይማን ሆነው ይገኛሉ ፡፡  ምክንያቱም ዓለምን ተባብሮ በማልማት ፣ ሰው ሁሉ እየተዟዟረ የሚጎበኛት ፣ በምድር አጭር ጊዜ ቆይታው የበዛ ስቃይ የማያይባት ዓለምን መፍጠር ሲችሉ  ፣ እነሱ ጠግበው ያጋሳሉ ፡፡  እነሱ በፈጠሩት ግጭት ና ጦርነት በሶርያ ፣ በየመን ፣ በአፍጋኒሥታን ፣ በኢትዮጵያ በእርስ በእርስ  ጦርነት ሰበብ በተፈጠረ ሥደት  ሰው በርሃብ አለንጋ እየተጠበሰ እያየን እነሱን አወቂዎች ና ኃይማኖተኞች ናቸው ለማለት አንችልም ፡፡

( አሜሪካ አፍጋኒሥታን የገባችው ታሊባን ከምር  የአልቃይዳ መጠለያ ምሽግ ነው ብላ  አሸባሪነትን በግንባር  ከምር ለመዋጋት ብቻ ነበርን ? ታሊባንን ለማጥፋት ተብሎ የሚገዛው የእልቂት መሳርያ ከየትና ከነማን ነበር ? ተጠቃሚዎቹስ እነማን ነበሩ ? … የኦፕዬም ያልተቆረጠ ዘረፋ በአፍጋኒስታን ውስጥ አልተካሄደም  ?  የመድሃኒት ካምፖኒዎቿን ፍላጎት ከሚገባው በላይ አላረካችምን ? ታሊባን ተመልሶ የአፍጋን መንግሥት እንዲሆን ሥትፈቅድ ወደፊት ዘላቂ ጥቅሞን የሚያሥጠብቅላትን ሥውር እጃ ሳታሥቀምጥ ዝም ብላ የወጣች ይመሥላችኋልን ? ጆን ባይደን አሜሪካ በየደሃ ና በአንዳች ውድ ሀብት በበለፀጉ አገራት ውሥጥ  ጣልቃ የምትገባው  ለፅድቅ ሳይሆን የግል ጥቅሟን ለማሥጠበቅ ( ለብዝበዛ ) መሆኑንን እኮ በግልጽ  ነግረውናል ። )

የአሜሪካ መንግሥትም ሆነ ፣ አንዳአንድ የበለፀጉት አገራት መንግሥታት ህሊና ቢሶች በመሆናቸው ሰው ሆነው ሳለ ፣ ለሰው የማያዝኑ ናቸው ፡፡  የሌሎቹን አገሮች ትተን በአገሬ በኢትዮጵያ የሚፈፅሙትን ሤጣናዊ ተግባር ማሥተዋሉ ብቻ ይህንን ያረጋግጣል ። በተለይ አሜሪካ ይፋ የሆነ ጣልቃ ገብነትን የመረጠችውና በደሌላዊ የሴራ ፖለቲካ እነ ሳማንታ ፓወርን በመሳሰሉ የጥፋት ሴራ መሪዎች አማካኝነት የሤጣን ተግባር እየፈፀመች ያለችው ፤ ኢትዮጵያ ውሥጥ በአሸባሪው ትህነግ በኩል ስታከናውነው የነበረው  እጅግ ትርፋማ የሆነ ብዝበዛ ሥለተቋረጠባት ብቻና ብቻ እነደሆነ የዛሬ የውሸት ኡ!ኡ? ታቸው ይመሰክራል  ። ይህንን ለመገንዘብ በአሜሪካ ና በአውሮፓ አሥፖልት ላይ በጥጋብ የሚከባለሉትን የመሣፍንቶቹን የትህነግ ልጆች መመልከት ብቻ በቂ ይሆናል ።  እነዚህ ጥጋበኞ ፣ በጣት የሚቆጠሩ የትህነግ ዓባለት ፤ አያሌ ቢሊዮን ዶላር በአሜሪካ ና በስዊዝ ባንክ እንዳከማቹ ይታወቃል ። ዛሬም ይኸው የደም ብር እየተቆነጠረ በመውጣት ለጥፋት ዓላማ በአገር ውሥጥ ይበተናል ። በዚህ የደም ብርም “ሴት ለሚፈልገው ሴት ፤ ሥጋ ለማፈልግ ሥጋ ይገዛበታል ። ” የጦር ና የፖለቲካ አሻጥርም ይፈፀምበታል ። በግንባር በጦሩ ላይ ፤ በማህል አገር በጠቅላዩ ላይ ይሴርበታል ።…

ተጨማሪ ያንብቡ:  አበራ ለማ፡ ለባሉ ግርማ፡ አስቦ ወይንስ ሌላ? (ከማተቤ መለሰ)

ትላንት ታላቁ ና ጀግናው  የኢትዮጵያ ሠራዊት ጠመንጃውን ከዱላ በታች ቆጥሮ አንገቱን ደፍቶ ከሰሜኑ የአገራችን ክፍል ወደማሀል አገር ና  ወደቀየው የገባው ፤ ጥቂት የማይባለውም  በበርሃ በውሃ ጥምና በርሃብ ክልትው ብሎ የቀረው ፤  አብዛኛው ወደሱዳን ና የመን  ተሰዶ በመግባት በሥተኋላ ወደአገሩ ተመልሶ ተመፅዎች የሆነው ፤ በሴት ና በሥጋ በተታለሉ ወታደራዊ ና ሲቪል ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣኖች እጅና እግሩ ታሥሮ ለእርድ በመቅረቡ ነው ።ከዚህ አንፃር ደሊላዊነት ትላንትም ገዝፎ እንደታየ አትርሳ !

ይህንን እውነት ዛሬ ለማውሳት የፈለኩት ፣ በዓሉ ግርማ ” በኦሮማይ ” መፅሐፉ ጠቁሞን ያለፈው ፣ የሚያሥቆጭ ፣ ለሆድና ለሴት ተገዝቶ አገርን የመሸጥ አፀያፊ ተግባር  ዛሬም እንዳይደገም በማሰብ እንደሆነ  አትዮጵያን አፍቃሪ የሆናችሁ ሁሉ እንድትገነዘቡልኝ እወዳለሁ።

የአገራችንን የዛሬ ችግር ለመፍታት የሚያሥፈልገን፣ የተጋነነ እና የተደጋገመ  የሚዲያ ዲሥኩር አይደለም ።  ዛሬ የሚስፈልገን   ለኢትዮጵያ አገሩ ክብር ና ነፃነት ሲል በልበ ሙሉነት ከጠላት ጋር አንገት ለአንገት የሚተናነቅ ዜጋ ገድልን መስማት ና እናም የአባቶቻችን ልጆች መሆናችንን ማሳወቅ ነው ። ይህንን በመንጋ የታገዘ የዘራፊው እና የአእምሮ ቢሱን ወረራ በመቀልበስ ቀንደኛ ሴጣኖችን ከምድረ ኢትዮጵያ ማጥፋት ነው ፡፡

ከኢትዮጵያዊያን ባህሪ አንዱ በጀግንነት ግለት ወደፊት ተራምዶ ጠላትን መግቢያ መውጫ አሳጥቶ ፣ ትንፋሽ እንዳያገኝ በማድረግ ጦርነትን በአጭር ጊዜ መጨረሥ እንጂ በተራዘመ ጦርነት መሠላቸት ከቶም አይደለም ። እናም በሴት ፣ እና በዶላር የሚገዙ የጦር ና የፖለቲካ ሹማምንቶች እንዳይኖሩን የደህንነት ሥራችን ከምንጊዜም በላይ ጠንካራ መሆን አለበት ። ያልተገባ ና የተንዛዛ የመከላከያ ሚኒሥቴር ቢሮክራሲ ና አዛኝ ቅቤ አንጎች የሆነ የጠቅላይ ሚኒሥቴሩ አማካሪ ካለ ፣ ከሥፍራው ገለል መደረግ ይኖርበታል ።  ዛሬ አሜሪካ በሲአይኤ በኩል ሚዲያዎቿን በሙሉ አሥተባብራ ኢትዮጵያን ለማሽመድመድ እና ለአሸባሪው ትህነግ ቀኝ እጆን በመዘርጋት ከመቃብሩ ለማውጣት ደሊላዊ በሆነ ምግባሯ አሳይታናለች ፡፡ አሻንጉሊት መንግሥት በኢትዮጵያ ለመፍጠር በማሰብ ደፋ ቀና እያለችም ነው  ፡፡ ይኽ አካሄድዋ እጅግ ደካማ እና ኢትዮጵያዊያንን ከማያወቅ ጭንቅላት የመነጨ እንደሆነ እናውቃለን ፡፡  በመሆኑም እኛ ጀግኖች ኢትዮጵያዊያን፣  አሸባሪውን ና  ጭራቁን ወያኔ  ከትግራይ ምድር ለማጥፋት የምናደርገውን ትንቅንቅ ፣ ለአሜሪካ ብዝበዛ እጅ ያለመስጠት እነደሆነ እናውቃለን ፡፡

ደግሞም ፤   የአሜሪካው ሲአይኤ ዛሬም በሴት ና በዶላር  ( በሥጋ )  የኢትዮጵያን ከፍተኛ የጦር ና የፖለቲካ ባለሥልጣናት በማጥመድ በደሊላዊ ሴራ . በቀናት ውሥጥ አገር እንዲሸጡ የማድረግ ብቃት እንዳለውም እናውቃለን። ከኢትዮጵያ የጦር ና የፖለቲካ  ከፍተኛ ባለሥልጣናት ሥንቶቹ ” ከአውዳሚ ሱስ ” ነፃ እንደሆኑ እና ለገዛ ህሊናቸው ታማኝ እንደሆኑ በመጠየቅ የነገሩን አደገኝነት መረዳት አይከብደንም። ለማንኛውም አሜሪካዊያኑ በጠቅላይ ሚኒሥቴር አብይ አህመድ የገዘፈ አእምሮ ና አገር ወዳድነት  የተቋረጠባቸውን ብዝበዛ በትህነግ አማካኝነት እንደገና የሚያገኙት ከሆነ ይህንን በቢሊዮን ዶላር የሚገመት ዓመታዊ   ጥቅም በማንኛውም መንገድ ለማግኘት መጣራቸው ዛሬ ግልጽ ሆኖል ፡፡ የውጪ ቅጥር ተዋጊዎችን ና ነፍሰ ገዳዮችን ሳይቀር ከወያኔ ጋር ከማሰለፍም ወደኋላ አይሉም፡፡  እናም የኢትዮጵያ ደህንነት መሥሪያ ቤት ፣ ከሌሎች ወዳጅ አገር የደህንነት ዓባላት ጋር ተቀናጅቶ በዘመነ ቴክኖሎጂ ፣ በከፍተኛ ባለሥልጣነት እና የጦር አዛዦች ላይ ሃያአራት ሰዓት የክትትል ና የቁጥጥር ሥራ መስራት እንደሚጠበቅበት በማሳሰብ ጽሑፌን እቋጫለሁ  ። …

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share