ደብረ ዘቢጥን ወርሮ የነበረው አሸባሪው ወራሪ የትግራይ ኀይል በጀግናው የወገን ጦር ከፍተኛ ድብደባ እየተካሄደበት ነው

453 ደብረ ዘቢጥን ወርሮ የነበረው አሸባሪው ወራሪ የትግራይ ኀይል በጀግናው የወገን ጦር ከፍተኛ ድብደባ እየተካሄደበት ነው

የአሚኮ የጋዜጠኞች ቡድን ደብረ ዘቢጥን ወርሮ የሚገኘው አሸባሪው ወራሪ የትግራይ ኀይል አይቀጡ ቅጣት እየተቀጣ መሆኑን ግንባር ድረስ በመገኘት ተመልክቷል።

መድፍ ተኳሽ የሆነው 50 ዓለቃ አሚን ስሩር ሕዝባዊ ሠራዊቱ በከባድ መሳሪያ አሸባሪው የትግራይን ኀይል እየደመሰሰ ነው ብሏል። ወራሪውን የትግራይ ኃይል ከአማራ ክልል ብቻ ሳይሆን የትም ቢገባ አሳድደን እንቀጠዋለን ነው ያለው።
“በሁሉም ዘርፍ ከፍተኛ ድጋፍ ላደረገልን ሕዝብ ከሕይወት በላይ ሌላ ዋጋ ብንከፍልለት ደስ ይለን ነበር” ብሏል። በአሁኑ ወቅት ጠላት ወደኋለ እየሮጠ ነው፣ እኛም ጠላትን ተከትለን እየተደመሰሰ መሆኑን ተናግሯል።
የመድፍ ተኳሽ የሆነችው 10 አለቃ ወጋየሁ ዳምጠው ጠላት በገባበት አካባቢ መውጫ እስኪያጣ እየተደበደበ ነው ብላለች። በጦር ግንባር ከወንድሞቻችን ጋር ሆነን ጠላትን አይቀጡ ቅጣት እየቀጣን ነው ብላለች።
ጠላት ስለተበታተነ መቀጥቀጥ እንጂ ምንም አይነት ምላሽ እየሰጠ አይደለም ነው ያለችው። “ወራሪውን ቡድን አጥፍተን ኢትዮጵያ ረፍት እንድታገኝ እንፈልጋለን ለዚያም ጠንክረን እየታገልን ነው” ብላለች።
10 ዓለቃ ብዙዓየሁ አዳሙ የከባድ መሳሪያ (ቢ ኤም) አስወንጫፊ ናቸው። ደብረ ዘቢጥ አካባቢን ወርሮ የነበረው ጠላት ዋጋውን እያገኘ ነው ብለዋል። ጠላት ከገባበት አካባቢ የሚወጣበት እድል የለውም ነው ያሉት።
ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ-ከደብረ ዘቢጥ ግንባር
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 21/2013 ዓ.ም (አሚኮ)

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.