ስለ እኛ ጉዳይ “ቢዚ ነኝ” የማይለውን የኢትዮጵያ ወዳጅ

61+cdvcizul
David Steinman

Money, Blood and Conscience: A Novel of Ethiopia’s Democracy Revolution Kindle Edition

እውነት ለመነጋገር ብዙዎቻችንን “ቢዚ” የሚያደርገን ነገር ብዙ ቢሆንም ስራ ዋነኛው ነው። እርግጥ ነው፣ ኑሮን አሸንፎ ለመኖር ስራ ያስፈልገናል። ግን ደግሞ የደመወዝ ባሪያ ሆነን ሌላውን ሁሉ ጉዳይ እርግፍ አድርገን ትተን የግል ጉዳያችን ላይ ብቻ እድናተኩር ካረገን ስራችን ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። ሁሉም እንደየ አቅሙ ቢዚ ነው!

ሰሞኑን የአገራችንን ጉዳይና የተቀበሩ እውነታዎችን አጉልተን ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ማሰማት፣ መሞገትና ድምችንን ማስተጋባት ይገባል በሚል እምነት በተለይ በኢንግሊዝኛ ቋንቋ የመጻፍና የመናገር ችሎታ አላቸው ተባብረን ብንሰራ በጋራ ለውጥ እናመጣለን ብዬ ያመንኩባቸውን ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በስፋት አናግሪያለሁ። ለመተባበር ፈቃደኛ የሆኑ በርካቶች የመኖራቸውን ያህል አስቀድመው “በጣም ቢዚ ነኝ” የሚሉትም አገር ወዳዶች ብዙ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ። በእርግጥ አይገርምም!

 

Money, Blood and Conscience: A Novel of Ethiopia’s Democracy Revolution Kindle Edition

እኔም በጣም ቢዚ ነኝ። የስራና የቤተስብ ጉዳይ እንደ አብዛኛው ሰው ቢዚ ያደርገኛል። ግን ደግሞ ህዝባችን በየመንደሩ እየተገለደለና አገራችን የህልውና አደጋ በገጠማት በዚህ ፈታኝ ሰአት ከራሳችንም ይሁን ከቤተሰባችን ትንሽ ሰአት ሰርቀን ወገን ብንረዳ ሌላው ቢቀር የህሊና እረፍት እናገኛለን። ትዊተር ላይ የሚደረገው እርብርብ እንደ ተጠበቀ ሆኖ ክፍተቱ አደገኛ ደረጃ ላይ ደርሷል።

የሚገርመው ባንዲራ በማውለብለብና ዘራፍ በማለት ማንም የማይቀድመው ተግባር ላይ ግን ወገቤን ከሚለው አገር ወዳድ ይልቅ ኢትዮጵያን ለመርዳት “ቢዚ ነኝ” የማይሉና ያቅማቸውን ሁሉ የሚረዱን በርካታ የውጭ አገር ሰዎች አሉ። ፈታኝ በሆነ ሰአት ከጎናችን ቆመው ስለ እኛ የተሟገቱ ዕውነታችንን አጉልተው ያሰሙ ያልሸለምናቸውና ያልዘመርንላቸው የክፉ ቀን ደራሽ የሆኑ ከኛ ያልተወለዱ ግን ደግሞ ስለ ዕውነትና ፍትህ ሲሉ ከእኛ ጋር የወገኑ የኢትዮጵያ ወዳጆች አሉ።

እኔም ሆንኩ ሌሎች ትብብር በጠየቅነው ጊዜ ሁሉ አቅሙ የፈቀደውን የሚያደርገው አስተማማኝ የኢትዮጵያ ወዳጅ ከሆኑት መሃል አሜሪካዊው ዴቪድ ስታይንማን በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ነው። ዴቪድ ለኢትዮጵያ ያደረገውን የተግባር አስተዋጾ አብዛኛው ያገሬ ሰው አልሞከረውም።

ህወሃቶችን እንደ ዴቪድ የሚያውቅና ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ ለማጋለጥ ጥረት ያደረገ የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም። የጀመርኩትን የሚድያ ፕሮጄክትም አብሮ በመስራት ለማሳካትም ከጎኔ ቅድሚያ የተሰለፈው ደከመኝ ሰለቸኝ የማይለው ዴቪድ ነው።

ዴቪድ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለ ኢትዮጵያ ጉዳይ መሞገት የጀመረው ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን ያ ለዛሬ ውጥንቅጥና እልቂት ኢትዮጵያን አዘጋጆቶና አጣ ፈንታዋን አወሳስቦ ያለውፈው መለስ ዜናዊ የሚባል እኩይ በግፍ አስሮ ሲያሰቃያቸው ተቃውሞውን ለማሰማት ለነበር።

ዴቪድ ስለኢትዮጵያ ብዙ ጽፏል፣ ብዙ ተናግሯል። ከሶስት አመት በላይ ደክሞና አምጦ በህወሃት ክፋትና ወንጀል ላይ ያተኮረ “Money, Blood & Conscience” የሚል ርዕስ ያለው መጽሃፍ ጵፎም ለንባብ አብቅቿል። በቅርቡም ቴድሮስ አድሃኖምን እስከ አይሲሲ ድረስ የወሰደ ያልተዘመረለት ጀግና ነው።

ይሁንና ብዙ ጊዜ ዴቪድ መጽሃፉን ምንም የማይመለከተው የውጭ ዜጋ እየገዛ ሲያነብ አብዛኛው ያገሬ ሰው ለማበረታት እንኳ ለምን እንደማይገዛው ይገርመዋል። በዚህም ጉዳይ ላይ በቅርቡም ስሜቱን አጋርቶኛል።

ወገኔ ሆይ! የዴቪድ አይነት ሰዎች ለኢትዮጵያ፣ በእጅ የያዙት ወርቅ ሆነውብን ነው እንጂ፣ እጅግ በጣም ያስፈልጉናል። ወያኔ ብዙ ገንዘብ እየከፈለ ነጮች እያስለፈለፈ ውሸትን በአለም ዙሪያ ሲናኝ እኛ ቢያንስ እንደ ዴቪድ አይነት ሰዎች አምጠው የጻፉትን መጽሃፍ እንግዛቸው፣ እናንብብላቸው። ልጆቻችንንም እንዲያነቡት እናበረታታቸው። ያው እንደ ተለመደው እንዲህ አይነት ሰዎች በቃኝ ብለው ሲርቁን ምን ያህል እንዳጎደሉን በቁጭት አጣናቸው እያልን ማውራታችን አይቀርም።

የዴቪድን መጽሃፍ ካልገዙ አሁንንው ቀጠሮ ሳይሰጡ ለመግዛት ሊንኩን በመጫን አማዞን ላይ ይግዙት ። መጽሃፉ ህወሃት ዛሬ የጀመረውን መጠነ ሰፊ የሽብር ጦርነት ወስጠ መሰረት ቁልጭ አርጎ ያሳያል።

ስለ እኛ ጉዳይ “ቢዚ ነኝ” የማይለውን የኢትዮጵያ ወዳጅ በመተባበርና በማገዝ ብዙ እናትርፍ!

1 Comment

  1. Thank you very much this man deserves recognition by Ethiopians at least by buying his book I have bought hard copies two one for me one for a friend. Please keep up rewarding Ethiopian friends in every form.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.