ከሰዓት በኋላ በመዲናዋ በጣለው ከባድ ዝናብ የተከሰተው ጎርፍ በሰዉ ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገለፀ

235265585 2065343783616959 6121603854253175781 n

ከሰዓት በኋላ በመዲናዋ በጣለው በረዶ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ ምክንያት የተከሰተው ጎርፍ አደጋ በሰዉ ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገለፁ ።

ከክረምቱ ጋር ተያይዞ ዛሬ ከሰዓት በኋላ አዲስ አበባ በጣለው በረዶ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ ምክንያት በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች የጎርፍ አደጋ ተከስቶ በሰዉ ሕይወት እና ንብረት ላይ በደረሰው ጉዳት ማዘናቸውን ከንቲባዋ ገልጸዋል ።

235195293 2065343816950289 6811480159796519442 n

በአስኮ፣ በአደይ አበባ፣ በጀርመን አደባባይና በጎልፍ ክለብ አካባቢዎች በደረሰው ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ እስከአሁን ድረስ መንገዶች ተዘግተዋል፤ የድንገተኛና የእሳት አደጋ ሰራተኞቻችን በቦታዎቹ በመገኘት ሰብዓዊ ጉዳት እንዳይደርስ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኛሉ ብለዋል።
ተጎጂዎችን ወደ ህክምና መስጫ በማጓጓዝና የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ በማድረግ ላይ እንገኛለን ብለዋል።
በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ከክረምቱ ጋር ተያይዞ የጎርፍ አደጋ እንዳይከሰት አስቀድሞ የመከላከል ስራዎችን እየተሰራ ቢሆንም የዛሬው አደጋ ተጨማሪ ስራዎችን መስራት እንደሚገባ አመላካች መሆኑን ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ጠቁመዋል ።
የብሄራዊ ሜትሮዎሎጂ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በመጪዎቹ ቀናት ከፍተኛ መጠን ያለዉ የዝናብ ስርጭት ስለሚኖር ነዋሪዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደርጉ ምክትል ከንቲባዋ ጥሪ ማቅረባቸውን የከተማዋ ፕሬስ ሴክሬታሪያት መረጃ ያመለክታል።
(ኢ ፕ ድ)

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.