የህወሓት የሽብር ቡድን በጋይንት፣ ወልዲያ፣ መርሳና ሰቆጣ ከባድ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ እየደረሰበት ነው

gizachew

የህወሓት የሽብር ቡድን በደቡብ ጎንደር ዞን ጋይንትና አካባቢው፤ በሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ፣ መርሳና አካባቢው፤ እንዲሁም በዋግህምራ ዞን ሰቆጣና አካባቢው እየተሰወደበት ባለው ወታደራዊ እርምጃ ከባድ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ እየደረሰበት መሆኑን የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ገለፀ፡፡
የፅህፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከኢቲቪ ጋር ባደረጉት ቆይታ የሽብር ቡድኑ ትላልቅ አዋጊዎች መገደላቸውን እና በርካታ የቡድኑ ታጣቂዎችም መማረካቸውን ገልፀዋል፡፡
የህወሓት የሽብር ቡድን በኃይል በወረራቸው አካባቢዎች ወጣቶች ታፍነው ተወስደዋል፣ ሴቶች ተደፍረዋል፣ ንብረቶችም ተዘርፈዋል ብለዋል፡፡
በዚህ ሳቢያ የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥርም በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ መሆኑን አቶ ግዛቸው አስታውቀዋል፡፡
የህወሓት የሽብር ቡድንን ለመደምሰስ የተላለፈውን ሀገራዊ ጥሪ ተከትሎ ህብረተሰቡ የሽብር ቡድኑን ግብዓተ መሬት ለማፋጠን ያሳየው ተነሳሽነትና ርብርብ የሚደነቅ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
አቶ ግዛቸው በአጠቃላይ ህብረተሰቡ በተለይ ደግሞ ወጣቱ ተደራጅቶ አካባቢውን በንቃት መከታተል እና ከሽብር ቡድኑ ሰርጎ ገቦች መጠበቅ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
በውጭ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም የህልውና ዘመቻውን በገንዘብና አቅማቸው በፈቀደው ሁሉ እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በሰለሞን ፀጋዬ
EBC
ተጨማሪ ያንብቡ:  ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው የሰው እጅ እንዳላይ መንግስት ጠበቃ ያቁምልኝ አሉ | ወንድማቸውና የቀድሞዋ የETV ጋዜጠኛ ታሰሩ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share