የጋይንት ህዝብ አሁንም ጀግንነቱን እያስመሰከረ ነው !!

234600522 2640852816221970 8477544751668545894 n

~ ከትናንት በፊት ጋይንት ጁንታውን አይቀጡ ቅጣት ቀጥቶ ልኮታል
~ አሁንም ጋይንትና ነፋስ መውጫ በህዝባዊ ሰራዊቱና በወጣቱ ቁጥጥር ስር ይገኛሉ
~ ነገር ግን ማታ ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ ወደ ጋይንትና ነፋስ መውጫ መግቢያ ያጠው ይህ ተላላኪ እርሻ ለእርሻ ቆረጣ ሞክሯል ሳሊ መገንጠያ ላይም ከፍተኛ ውጊያና ተኩስ ሲያካሒዱ አድረዋል
~ ይህ የተቆራረጠ ጁንታ ዋና ፍላጎቱ ጉና ተራራን ለመያዝ ቢሆንም ሳይሳካለት ቀርቶ ግማሽ ጎኑን ተመቷል እንዲሁም በቁጥር ከ 19 በላይ ጁንታ እስከወዲያኘው ተሸኝቷል
~ ይሁን እንጅ ይህ ጁንታም ትናንት ማታ ሳሊ ላይ ህዝቡን ነገ ስብሰባ አለን እንድትወጡ እያለ ሲያሸብርም አምሽቷል
~ አሁን ላይም በርካታ የአማራ ህዝባዊ ሰራዊት ወደ ቦታው አቅንቶ ጁንታውን መፈናፈኛ አሳጥቶታል
~ መፈናፈኛ ያጠው ቁራጭ ጁንታም ሌላ መንገድ ቀይሶ ስማዳ ወረዳ በሚወስደው መገንጠያ ወለላ ባህር አካባቢ ለመሔድ እየሞከረ ስለሆነ ሁላችንም የአካባቢው ማህበረሰብና ወጣት ዋና ዋና በሮችን እንዝጋ
~ የደብረታቦር ፣ የክምር ድንጋይ፣የጋሰይ ፣ የሳሊ ፣ የጎብጎብ ፣ የስማዳ ህዝብና ወጣት በነቂስ ወጥቶ እንደ ህዝብ የመጠውን ጥቃት እንደ ህዝብ መመከት አለብን።
ማሳሰቢያ:- ሌላ ነገር አትበሉኝ ዝም ብላቹህ መረጃውን አዳርሱና ባላቹህበት ፀንታቹህ ቁሙ። እንናበብ ።አሉባልታን እንከላከል።
( Derbew Ameshe)

ጋይንትና ነፋስ መውጫ !!!!

236107763 1803712939799560 1791566186635754759 n
236107763 1803712939799560 1791566186635754759 n

* አሁን ከመሸ ጁንታው ጋይንት ገባ , ነፋስ መውጫ ሰፈረ የተባለው ፍፁም ሀሰት ነው

* ጋይንትም ነፋስ መውጫም ነፃ ናቸው
— ዝርዝር ሁኔታ —
~ በነፋስ መውጫ ቆራጣ በምትባል የገጠር ቀበሌ አካባቢ ጁንታው ለመግባት ቢሞክርም አልተሳካለትም
~ አሁንም ድጋሜ በሳሊ ለመግባት ሞክሯል ይህም አልተሳካለት
~ ከታች ተነስቶ ሲመጣ የነበረ አንዳንድ የጦር ቁስለኞችና ወላድ እናቶች የሚሔዱበትን መኪና መምታት ጋይንትን መያዝ ማለት አይደለም
~ በአጭሩ በታች ጋይንትና በላይ ጋይንት ላይ የተቆራረጠው ጁንታ እየተመታ ነው አሁን ላይ ምንም የለ
* ጎብጎብ ላይ በርካታ ህዝባዊ ሰራዊት ወጣቱን ይዘው በመኪና እየዞሩ ይገኛሉ እንጅ ጁንታው እየገባ አደለም
* አሁንም የሀሰት ፕሮፖጋንዳ እያሰራጩ ያሉት እየተለዩ እየተያዙ ነው
* የነፋስ መውጫ ፣ የሳሊ ፣ የጎብጎብ ወጣትና ህዝብም ወጥቶ አካባቢውን በንቃት እየጠበቀ ይገኛል።
Derbew Ameshe
https://youtu.be/A1T4JrTGZuA

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.