በአፋር የጁንታው አንድ ክፍለ ጦር ተደምስሷል!!!!!

235902644 4181648611882786 9219797526045594648 n 960x442 በአፋር የጁንታው አንድ ክፍለ ጦር ተደምስሷል!!!!!

ዛሬ ነሐሴ 3/2013 ዓ.ም በአፋር ግንባር እጅግ ታላቅ ድል እየተመዘገበ ነው!!!!! ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ እየተካሄደ ባለው መጠነ ሰፊ ጥቃት ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን እና አናብስቶቹ የአፋር ልዩ ኃይላችን በጁንታው ተይዘው የነበሩ ቦታዎችን በአስደናቂ ጀብዱ እያፀዱ ይገኛል!!!!! በከፍተኛ እልህ እና ወኔ እየተዋደቀ የሚገኘው ጀግናው የአፋር ህዝባችንም ትልቅ ክብር ይገባዋል!!!!

ጁንታው በአፋር ህዝባችን ላይ ያደረሰው አሰቃቂ ግፍ በተለይ በጋሊኮማ መጠለያ ጣቢያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን የአፋር ህፃናትን እናቶችን እና አዛውንቶችን መጨፍጨፉን ተከትሎ መላው የአፋር ህዝብ ከሊቅ እስከ ደቂቅ : የታጠቀም ያልታጠቀም : ፍየል ጠባቂው: የተማረው: ወንድ ሴት ሳይል ሁሉም የህልውና ዘመቻውን ተቀላቅለው በጊሌ እና በገጀራ ጭምር የጠላትን አንገት እየቀሉ ታንክ መማረካቸውን ወደፊት ታሪክ በደማቁ ይዘግበዋል!!!! የአፋሩ ጀግና ሃመዱ የጁንታውን ታንክ ተኮሽ ታንኩ ላይ በመውጣት በጊሌ አርዶታል!!!! የአፋር አባት በጁንታው የተገደለበትን ልጁን ሳያነሳ በቀጥታ ጠላትን ለመበቀል ወደ ፍልሚያ ገብቷል!!!!! የአፋር እናት የተገደለባትን ልጇን ከመቅበር ይልቅ የልጇን ገዳይ ለመግደል እንባዋን ዋጥ አድርጋ ዘምታለች!!!!! ሁሉም ወደፊት ብቻ ይገሰግሳል!!!!ብዙ የሚነገሩ አፈ ታሪክ የሚመስሉ አንፀባራቂ ተጨባጭ ታሪኮች እየተመዘገቡ ነው!!!!!

235810984 4181630388551275 3984442519483811112 n 960x442 በአፋር የጁንታው አንድ ክፍለ ጦር ተደምስሷል!!!!!

የህዝብ ማዕበል አስነስቶ የመጣን ጠላት የታጠቀ ሰራዊትን ብቻ በማሰማራት ሳይሆን በእንዲህ ዓይነት ተመሳሳይ የህዝብ ማዕበል ነው መመከት: መቀልበስ ብሎም መልሶ ማጥቃት እና ማፅዳት የሚቻለው የሚለውን ሃቅ የአፋር ህዝብ በተግባር አረጋግጧል!!!! ይህ ዘመቻ የህልውና ዘመቻ እንጅ ቀበሌን ወይም ከተማን የመያዝ አለያም የማስለቀቅ የዥዋዥዌ ጨዋታ አይደለም!!!! የህልውና ዘመቻ ማለት ህልውናህን ሊያጠፋ ቀዬህ ድረስ የመጣን አራጅ ጠላት መክተህ እና ቀልብሰህ ህላዌህን ማረጋገጥ ማለት ነው በትንሹ!!!! ምርጫው ሁለት ነው!!!! ወይ ህልውናህን ማረጋገጥ አለያም መጥፋት ነው!!!! ሌላ ሶስተኛ ምርጫ የለም!!!! ይህን የተረዳው ጀግናው የአፋር ህዝብ ትንሽ ትልቅ ሳይል ሰበብ ሳያበዛ ህልውናውን ለማስቀጠል በተግባር እየተፋለመ ነው!!!! ለዚህ ደግሞ የአፋር አመራሮች ህዝባቸውን ሞቢላይዝ በማድረግ ረገድ የተጫወቱት ታሪካዊ ሚና በቃላት የሚገለፅ አይደለም!!!!! ሌሎች አመራሮችም ከዚህ ሊማሩ ይገባል!!!!

235438460 4181630225217958 6745313618171901318 n 960x442 በአፋር የጁንታው አንድ ክፍለ ጦር ተደምስሷል!!!!!

ጀግናው መከላከያችን እና የአፋር ልዩ ኃይላችን ከጫፍ እስከ ጫፍ የተነቃነቀውን መላውን የአፋር ህዝብ ደጀን በማድረግ እነሆ በዛሬው ዕለት ሃያል ጀብዱ እየፈፀሙ እና ጠላትን አይቀጡት ቅጣት እየቀጡ ጣፋጭ ድልን እያጣጣሙ ይገኛል!!!! ጁንታው ከባድ መሳሪያዎቹን ተክሎ እና ያለውን ሃይል አሰልፎ ወደ ጭፍራ እሻገራለሁ ብሎ የሃይል ማዕከል አድርጎት የነበረችው ኡዋ ከተማ ከማለዳ ጀምሮ በተካሄደው ጦርነት ጁንታው የሰራዊታችንን እሳት ክንድ መቋቋም አቅቶት ኡዋን ለቅቆ ወደ አውራ በመሸሽ ላይ ይገኛል!!!!

በደረሰኝ ተጨባጭ መረጃ “ኡዋ” ላይ
= የጁንታው አንድ ሙሉ ክፍለ ጦር ከጥቅም ውጭ ሆኗል!!!!
= የሙት ቁጥር ጧት ከተመዘገበው ከ 300 ወደ 650 ተጠግቷል!!!!
= 265 ቁስለኛ እና 47 ምርኮኛ ተመዝግቧል!!!
የጁንታው 265 ቁስለኛ እና 47 ምርኮኛ በሰራዊታችን እጅ ገብቷል!!!! ይህ በተጨባጭ የተቆጠረው ነው!!!! በየጊዜው ሊጨምር እንደሚችል ይጠበቃል!!!!
= የቀረው ሃይል እግሬን አውጭኝ ብሎ በስምንት ተሳቢ ወደ አውራ ሸሽቷል!!!! የአየር ፀባዩ ለ air strike ብዙም አመች እንዳልነበር ተነግሯል!!! ይህ በእንዲህ እንዳለ ጁንታው ኡዋ ከተማን ለቅቆ ሲወጣ ከተማዋን በፈንጅ እንዳጠረ ሰራዊታችን ባለው ጠንካራ ወታደራዊ መረጃ እና ደህንነት አስቀድሞ በመገንዘቡ ከጁንታው ነፃ የሆነችውን ከተማዋን ከመቆጣጠር ይልቅ በጥልቅ ወታደራዊ ጥበብ ሌሎች (እዚህ የማይገለፁ) ወታደራዊ ስራዎችን በአስደናቂ ሁኔታ እየሰራ ነው!!!! በተጎዳኝ የፈንጅ አምካኞቻችን ስራም በዝቷል!!!!
ለጀግናው መከላከያችን ለጀግናው የአፋር ልዩ ኃይል እና ለበርሃ አናብስቱ የአፋር ህዝባችን እና አመራሮች ባርኔጣችንን አውልቀን ከፍ አድርገናል!!!!! ሰራዊት እና ህዝብ ትክክለኛ መሪ ሲያገኝ ውጤቱ እንደዚህ ነው!!!!! ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን!!!!! በሁሉም አቅጣጫ ያሉ ዘመቻዎችም እየተስተካከሉና ክፍተቶች እየተሞሉ በቀናት ውስጥ ድል በድል እንደምንሆን የአፋር ግንባር ህያው ምስክር ነው!!!!! በተናጥል ድል የምንረካ አለያም በትንሽ ክፍተት የምንደነግጥ እርብትብቶች አይደለንም!!!! ትልቁን ስዕል ማየት ግድ ነው!!!! ይልቅ ከሰራዊቱ ጎን እንቁም!!!! የጠላትን የፕሮፖጋንዳ ውዥንብር እንድፈቅ!!!! ካልገባን ዝም እንበል!!!! ካሳሰበን እንፀልይ!!!!! እውነት እላችኃለሁ በመጨረሻ ኢትዮጵያ ማሸነፏ ቅንጣት ጥርጥር የለውም!!!!!
EBC

1 Comment

  1. ደብረ ጽዪን ተደራደሩ አለበለዚያ ትደመሰሳላችሁ፤ የአማራና የአፍር ክልል ህዝብ አጨብጭቦ እየተቀብለን ነው፤ የኢት. መንግስት ያለው አማራጭ ያቀረብንለትን ቅድመ ሁኔታ ተቀብሎ መደራደር ካልሆነ መደምሰስ ነው በማለት ነበር ከቀናት በፊት የደነፋው። ዲክተተሮች እንደዚህ ናቸው። እውነትና ውሽት የተላተመባቸው። እየሞቱ ገደልን፤ እየሸሹ አባረርን፤ ህዝብን አረንቋ ውስጥ እየዘፈቁ ለምለም ሜዳ ላይ አደረስናችሁ ነው የሚሉት። ወያኔ ገና ከጅምሩ ውሸትን የተጋተና ያስጋተ አጥፊ ሃይል ነው። ይህ ደግሞ ከጥላቻ የመጣ አነጋገር ሳይሆን የበረሃው ታሪካቸውና የከተማ አለቃ ከሆኑ በህዋላ የፈጸሙት ሰቆቃ እልፍና አመላካች ነው። እብድ ሰው ብቻ ነው አዲስ አበባ ገብቼ እንደገና በትረ መንግስቱን እይዛለሁ ብሎ የሚያምን። ምን ያህል ወያኔን የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ ተጸየፈው መረዳት የተሳነው በምናብ ዓለም ውስጥ የሚኖረው ደብረጽዪን ይህን ሁሉ ጉራ የሚናገረው በውጭና በውስጥ ያለውን ጭፍን ደጋፊዎቹን ደስ ለማሰኘት ብቻ ነው። ዳግም ለወያኔ አገዛዝ ማንም አይንበረከክም። ትግራዋይ እንጂ ኢትዮጵያዊ/ት አይደለንም የሚሉትም ከዚሁ ከእብደት ጽዋ የተቃመሱ የእብድ ስብስቦች ናቸው። መጋዝ ሲሄድም ሲመለስም ይቆርጣል እንዲሉ የወያኔ ተጋዳላይ በህይወትም እንኳን ቢተርፉ ወገናቸው፤ የትግል ጓደኞቻቸው እጎናቸው ሲረፈረፍ አይተው ጤናማ ይሆናሉ ብሎ መገመት የሰውን ስነ ልቦና አለማወቅ ነው። ባጭሩ ሰው ደንዝዟል። ወገኑ በደም ተጨማልቆ እያየ እኖራለሁ በማለት ሌላውን መግደል አውሬነት ነው። የውጭ ጠላት አልመጣብን እንዴት ወገን ወገኑን ይገድላል። መገደል ያለባቸው ሂዱና ግደሉ ብለው ወደ እሳት የሚማግዷቸውን መሆን ነበረበት። ግን ማን ልብ አለውና ነው መጣብህ መጡብህ መጣንብህ እየተባለ በውሸት የፓለቲካ ፕሮፓጋንዳ እቃ እቃ ተጫውተው ያልጠገቡ ልጆችን እሳት ውስጥ የሚማግደው ወያኔ ግፈኛና በትግራይ ልጆች ደም የሚነግድ ነው። ልክ እንደ መጋዙ ወያኔ የሚያጠፋው ሲሄድም ሲመለስም ነው። ለዚህ ነው የህዝብ ሃብት ዘራፊና ጨካኝ ማፊያ ነው የምንለው።
    አሁን እንሆ ከላይ በቀረበልን ዘገባ መሰረት እየተላለቅን ነው። የእኔ ጥያቄ ግን መድፉን፤ ከባድ መሳሪያውን፤ ሮኬቱን ወያኔ ከየት አገኘው? እንዴትስ ነው በነፋስ የተበተነው ድቈት ላሊበላን፤ አፋርን፤ ወልዲያና ሌሎችን አካባቢዎች ሊያስጨንቅ የቻለው? የሰሜን እዝን በተኛበት ሲያርድና የሴቶችን ጡት ሲቆርጡ (አኖሌን ያቆመው ወያኔ) ወታደሩ እንደገና ተሰባስቦ አመድ አደረጋቸው አልተባልንም ነበር? ውጊያው አሁን መሆን ያለበት ወያኔ ተደብቆበት የነበረውን ዋሻና ሸለቆ ቀድሞ በመያዝ ነው። ያ ከተያዘ ምንም ማምለጫ የላቸውም። ያው የኤርትራው የመከላከያ ሃላፊ እንዳለው ” አይጥ ከጉድጓዷ በራቀች ቁጥር በህይወት የመመለስ እድሏ የመነመነ ነው”. ሻቢያና ወያኔ ስለ ቀበሮ ጉድጓድ ያውቁ የለ። ስለሆነም አይጧ ለቃ የሄደችውን ጉድጓድ ሁሉ መድፈን ወይም በስፍራው ሰራዊት ማስፈር ነው። ተመልሶ ቤት አይኖርምና! የትግራይ ህዝብ ወያኔን አክ እንትፍ ብሎታል። ችግሩ በእልፍ ካድሬ ታፍኖ የተያዘ በመሆኑ ለመተንፈስ አይፈቀድለትም። ዛሬም አዋጡ፤ ትላንትም ልጆቻቹሁን አምጡ (ያኔ እንኳን ተዘፍኖ በመሳም ነበር) የዛሬው ልክ እንደ ደርግ ከመንገድ ላይ ማፈስ ነው። አታድርስ። ይህ ነው ነጻነት፤ ይህ ነው ለትግራይ ህዝብ የሚገባው? ግን እሰጣ ገባ እንደ ሰለቸው ሰው አታድርስ ከቀን እብዶች ጠብቀኝ ብሎ ከማለፍ በስተቀር ድርጊታችውን በጠራ ጭንቅላት ለማስላት መሞከር ራስን ማሳበድ ነው።
    ጸሃፊው ስለ አፋር ተጋድሎ ነግሮናል። አፋሮች ከጅምሩ ጀግኖች ናቸው። የሰው አይነኩም የራሳቸውንም አያስነኩም። በኢትዮጵያዊነታቸው አይደራደሩም። ዛሬም ወደፊትም ያው ናቸው። ወያኔ የአፋርን ህዝብ መጨፍጨፉ ማሰሪያውን ለማሳጠር እንደሆነ የታወቀ ነው። የእርዳታ እህል አልገባልን አለ እያለ ትላንትም ልመና ዛሬም ልመና የተሰማራው የወያኔ መንጋ ራሱ በድሎ ራሱ ነው የሚያለቅሰው። የአፋር ህዝብ ፈሪሃ እግዚአብሄር ይዞት እንጂ መንገድን ሙሉ በሙሉ መዝጋት ይችላል። ልጆቹን እየገደለ ያለው ወያኔ እንዴት ነው በሚገድለው ህዝብ መካከል የእርዳታ እህል የሚያልፈው? የኢትዮጵያ መንግስት ደንቆሮ ነው። በተለይ የፕሮፓጋንዳ (እውነት ላይ የተመሰረተ) አሰራሩ ሽምድምድ ነው። ነጻ የውጭና የሃገር ውስጥ ጋዜጠኞችን በውጊያው ቀጠና በማሰማራት የጦርነቱን እውነተኛ መልክ ለሃገርና ለውጭ ማሳወቅ ሲገባው ሁሌ መግለጫ፤ ሁሌ በድህረ ገጽ ወይም በቲዊተር ላይ መደንፋትና መጻፍ አላዋቂነት ነው። በፎቶ፤ በቪዲዮ በዓይን እማኞችና ተማርከዋል ቆስለዋል የሚባሉትን ያለ ምንም ጫና በራሳቸው ፈቃድና ቋንቋ የሚናገሩትን ለአለም ህዝብና ለወገናችን ማድረሱ መልካም ነበር። ቢቢሲ፤ አልጀዚራ፤ የአሜሪካው የውሸት ቱልቱላ ስ ኤን ኤን፤ ሌሎችም ጭራሽ መግባት የለባቸውም። እነዚህ የውሸት ቋቶች ሲከፋም የአሜሪካ የስለላ መረብ ወሬ አቀባዪች ናቸው። አሉ ለሰው ልጆች መብት የሚታገሉ ራስ አገዝ የሆኑ እውነቱን ብቻ የሚዘግቡ ሚዲያዎች እነርሱን ማለቴ ነው። አሁን ለምሳሌ የአፋር ልዪ ሃይልና ህዝብ ጀብድ ተጽፎልናል። ተቀርጿል? ለልጅ ልጅ የሚተርፍ በእውነት ላይ የተመረኮዘ ነገር አለ ወይስ እንዲህ እና እንዲያ ተብሎ የሚታለፍ የዛሬ ብቻ ወሬ ሆኖ ነው የሚቀረው? ባጭሩ ወያኔ እያለ ሃገር ሰላም አትሆንም። ይህ ጉዳይ አልገባኝም የሚል ካለ በአውሮፓ፤ በአሜሪካ፤ በላቲን አሜሪካ፤ በካናዳ፤ በአውስትራሊያ አልሞት ባይ ተጋዳይ የወያኔ ደጋፊዎች ኢትዮጵያን ለማሳነስ የሚሰሩትን ተንኮልና ደባ ማየት፤ መስማት፤ ማንበብ ብቻ በቂ ይሆናል። በቃኝ!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.