ከምር መንግሥት አለ? ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ከኮረም እስከ ወልዲያ የተፈፀሙ አሳፋሪ ድርጊቶችን አጋለጠ!!!! | ENDF | Woldiya

 

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ነጭ ነጯን!! ከኮረም እስከ ወልዲያ የተፈፀሙ አሳፋሪ ድርጊቶችን አጋለጠ!!!! | ENDF | Woldiya

 

የወሎ አማራ ተሸጧል

230885139 2883197801892147 7180770649284854504 n
230885139 2883197801892147 7180770649284854504 n

እኔ በራያ ግምባር ከዋጃ ጀምሮ በጦርነቱ ተሳትፌያለው ። በሁሉም ግምባር ማለት ይቻላል ። በሚዲያ እንደምንሰማው የፋኖም ሆነ የክልል ልዩ ሃይሎች በጦርነቱ አላየሁም ።

የተወሰነ ጦርነት እያካሄዱ ያሉት የአማራ ልዩ ሃይልና በቁጥር ትንሽ የሆኑ የመከላከያ ሰራዊት ናቸው ።
ጠላት ይመጣል ። እኛም ቦታ ይዘን እንጠብቃለን ከመከላከል ወደማጥቃት ስንሄድ አፈግፍጉ የሚል ድምፅ እንሰማለን ። ወደኋላ አፈግፍጉ ።
በጦርነቱ መካከል የወገን ጦር ነው የተባለው ኃይል ከኃላ ወግቶናል ።
በ4 ግምባሮች ተሰልፌያለው ። በሁሉም ቦታ ይህ ነው የሚባል ጦርነት አልተካሄደም ። በቃ አፈግፍጉ በሚባል ሠዓት መከላከያ ሰራዊቱ ትጥቁን ጭምር ለወያኔ ጥሎ ነው የሚያፈገፍገው ።
ከዛም . ከ2 መቶ የማይበልጡ የወያኔ ሚልሻዎች አቋርጠው ሌላ ከተማና ወረዳ ያዝን ብለው የጥይት ድምፅ ሲያሰሙ አስቀድሞ የሚፈረጥጠው አመራሩ ነው ። የአማራ ክልል አመራሮች ከፍተኛ የሆነ ድክመት አለባቸው ። አገር በውሸት አትመራም ።
ለምን እንወሻሻለን ? የወሎ አማራ ተሽጧል ።
ከፍተኛ ለወታደራዊ ስልጠና የተዘጋጁና ያልሰለጠኑም ወጣቶች ህይወታቸውን ለመስጠት ቆራጥ ነበሩ ። ግን ምን ያደርጋል ፡ አስታጥቁን ሲሉ ለናንተ መሳሪያ አንሰጥም ። ችግር ልትፈጥሩብን ትችላላችሁ ነው የተባሉት ።
ክተት ብሎ አውጆ ግምባር ላይ የስንቅና ትጥቅ አቅርቦት ሳይኖር ፡ ክተት ብቻ ምንም ቁም ነገር የለውም ።
የወልድያ ወጣቶች ቆራጦች ናቸው ።መሳሪያ መንግስት አስታጥቋቸው እንዳይመስልህ ። በጥልቆም ፡ በገጀራም በተገኜው ነው እየተዋደቁ ያሉት ።
ዋና ችግሩ የአመራሩና የመከላከያ ነው።
አርቲስት ዱባለ መላክ

1 Comment

  1. በሁሉም የውጊያ ቀጠና በመሳተፍ ከውጊያ ቀጠና በመመልስ “የወሎ አማራ ተሽጧል” በተባለው ዱባለ መላክን የምጠይቀው ቢኖር 1) የውትድርናው ስልጠና በየት ከይት ወሰድክ? ውትድርናህስ መክላከያ፣ልዩ ሃይል፤ሚሊሺያ ወይንስ ፋኖ? 2) መቸም አንድ ሰው ወደ ጦር ሜዳ ግዳጂ ሲጠራ ከሃምሳ አለቃ እስከ ክፍለ ጦር ከዚያም ሊያልፍ ይችላል ለዚህም መሪዎች አሉት ታዲያ አንተው ራስህ መሪ ተዋጊ ቃፊር ሀኪም አውጊም ነበርክን? እንዲያው ዱባ አለ መላክ ከነተረቱ የማይርባ ነገር ለሚስትህ አትንገር እንዲሉ።ይህንን ከንቱ ውሸት ለማውራት የተገደድከው የትህንግ መልክተኛነትህ ለማረጋገጥ አርቲስት ተብለሃል በደካማነትህ በፌስ ቡክ መታየት ባለመቻልህ የግዢ ወሬህን ለመበተን ሲሆን ከኋላህ ያነገብከውም እንኳን ተዋጊ ሃይል ይቅርና አይጥም አይገል ቀርቀሃ ነው በአንገትህም የጠመጠምከው ከጨምዳዳ ጽጉርህ የሚረግፉትን ተባዮች መሰበስቢያ እና የዱባአለ ፍሬ መቋጠሪያ እንጂ የውትድርና መለዮ አይደለም። ዱባ አገሩ ገባ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.