ዓለም አቀፍ ቅርስ የሆነው የላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት ደህንነት ጉዳይ እጅግ እንደሚያሳስበው ዩኔስኮ አስታወቀ

223110058 1584664091925427 6945988796470203945 n
223110058 1584664091925427 6945988796470203945 n

የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ዓለም አቀፍ ቅርስ የሆነው የላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት ደህንነት ጉዳይ እጅግ እንደሚያሳስበው አስታውቋል።

ዩኔስኮ እጅግ ድንቅ በሆነው ዓለም አቀፍ ቅርሱ ላይ ምንም አይነት ጉዳት እና ዝርፊያ እንዳይፈፀም እንዲሁም በዓለም አቀፍ ህግጋት መሰረት አስፈላጊው ጥበቃ እና ጥንቃቄ ሁሉ እንዲደረግለት ጥሪ አቅርቧል።
በኢትዮጵያ በ13ኛው ክፍለ ዘመን በአስደናቂ ጥበብ የታነፁት የላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት በምእመናን የሚጎበኙ፣ የአምልኮ እና የሰላም ስፍራ እንጂ የነውጥ እና የግጭት ማስተናገጃ ስፍራ አይደሉም ያለው የዩኔስኮ መግለጫ ስፍራው እኤአ ከ1978 ጀምሮ በዓለም ቅርስነት ተመዝግቦ እንደሚገኝም አስታውሷል።
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
EBC

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.