መልአክት፡ ለትግራይ ትምህርት ህብረተሰብ

ለትግራይ ዪኒቨርሲቲዎች ኮሌጆች ትምህርት ቤቶች አስተማሪዎች ተማሪዎችና ቤተሰቦች በጥውሉ የውደፊቱን መሪ አሳዳጊዎች

1606039008823

እኔ ወንድማችሁ ወገናችሁ አበበ ነኝ እንደምን ውላችሁ አድራችኋል አምላካችሁ አምላኬ ነው ይህ ቸርነት ጸጋና ምህረት የመላው አምላክ ቸርነቱን ጸጋውን ምህረቱን ያብዛልን
በየአጋጣሚው በሶሺያል ሚድያም ሆነ በአካል ከትግራይ ወግኖቼ ተጎራብቻለሁ የትግራይ ተማሪዎቻቸውንና ታታሪ አስተማሪዎቿን አውቃቸዋለሁ ከትግራይ አልፈው ከኢትዮጵያ ተርፈው ዓለምን የሚያገለግሉ ጎበዞችና ጎበዛዝት እንኳን በአካል አይቻቸው በህልሜም የማደንቃቸው ድንቅ ልጆች እንደ ምንጭ ፈልቀዋል እድል ገጥሞኝ የዛሬ አስር አመት መካከላቸው ነብርኩ እንደአባትም እንደ መምህርም ያዩኛል ትሁቶች ሰው አክባሪዎች ግብረገብነት ያላቸው በእምነታቸውና በሃይማኖታቸው ጥብቅ የሆኑ አገራቸውን የሚወዱ ዜጎች ወላድ በድባብ ትሂድ የሚስብሉ ምርጥ የአለም ዜጋ ናቸው

በእናንተ በወንድሞቼና እህቶቼ ከቅናት አልፌ ኩራት ተጎናጽፌአለሁአሁን ያላችሁበት ሁኔታ ከባድ ነው እንኳን ለናንተ ወንድሞቼ እህቶቼ ና ልጆቼ ይቅርና ለምጠላው የማልመኘው ነው  በዚህ ችግር ጽኑ ኢትዮጵያውያን እንሁን
ሰው ለመኖር ብቻ ሲል ከክፋት ጋር ይኖራል እንደምናየው ኢትዮጵያውያን በዘር ተከፋፍለው ጉርብትናቸውንና ጋብቻቸውን ክደው አሁንም ጥላቻን ተሸክመው ይኖራሉ ለዚህ ሁሉ ሞትና ስቃይ ሃላፊ አለው ሁሉን ብለናል
ግን እውነቷ ስትመጣ ሃላፊው ይታወቃል
ይሄ አሳዛኝ በታሪክ ዋጋው ትንሽ የሆነ ጦርነት ነው ወገንና ጠላት ተበጅቶለታል  ተፋላሚው የራሱን እውነት ይዟል እውነት የሚላትን ለማረጋገጥ ይተናነቃል
በዚህ ትንቅንቅ ውስጥ ስናልፍ በኢትዮጵያዊነታችን እንጽና አያቴ ስለ ኢትዮጵያዊነት በአስርቱ ትዛዛት ልክ እንዲህ ብለው ነግረውኛል- እኛ ኢትዮያውያን፡ አሉ

1. እኛ ውቅያኖስ ነን የትም አንፈስም
2. እኛ ወንዞች ነን የትም እንፈሳለን
3. እኛ ተራሮች ነን አንነቃነቅም
4.እኛ ሃማኖተኝች ነን አንሸሽም
6. እኛ አምላክ አለን አንፈራም
7. እኛ ሰው ነን ሰው እናከብራለን
8. እኛ ህግ አለን ህግ እናከብራለን
9. እኛ ዕውቀት አለን እውቀት እንሻለን
10. እኛ ታሪክ አለን መንገዳችንን እናውቃለን

ሁሉም አያት አለው ሁሉም ታሪክ አለው በአባቶቻችሁ ምክርና በእምነታችሁ ጽኑ
ሰው ማለት ሰውን የጠቀመ ማለት ነው
ሳትውሉ ሳታድሩ ሰው አድርጉኝ

ወንድማችሁ
አበበ ከበደ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.