አዲሱ የውክልና ጦርነት በኢትዮጵያ? ከትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ግንባር ሆድቃ የተገኘ ጥቁር ሰንዱቅ!!!

ኢት-ኢኮኖሚ
ሚሊዮን ዘአማኑኤል (ኢት-ኢኮኖሚ)

et32
et32

ትህነግ ለሃያ ሰባት አመታት ኢትዮጵያን በአንባገነን አገዛዝ በመምራት  በስብዓዊ መብቶች ጥሰት፣ በግድያ በቶርቸር፣ በዘር ማፅዳት፣ ህዝብ በማፈናቀል፣  በስደት ወዘተ አገዛዙ የተነሳ በአሜሪካ ኤች አር 128  ተጠቅሶበት የነበረ ሽብርተኛ ድርጅት ነው፡፡ ዛሬ ትህነግን ለማዳን አሜሪካ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ የአረብ ሊግ ፣ ግብፅ፣ ሱዳን ወዘተ አገራቶች  አዲሱ የውክልና ጦርነት በኢትዮጵያ? ከትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ግንባር ሆድቃ የተገኘ ጥቁር ሰንዱቅ!!! Ethiopia: A New Proxy Battlespace? “Black Box in the TPLF’s Belly”  ትህነግ  በሚያካሂደው ጦርነት አሸናፊ እንዲሆን የሳተላይት መረጃ በአሜሪካኖችና የአውሮፓ ህብረት እንደሚደርሰው አለመገንዘብ ቂልነት ነው፡፡ ዘመኑ የመረጃ ዘመን፣ ጦርነቱም መረጃ ማን አለው ነው፡፡ ትህነግ ወታደራዊ መንግሥቱን የጣለው በምዕራበዊያን የስለላ ከፍተኛ ድጋፍ በማግኘቱ እንደነበር አንዘንጋ፡፡

  • ‹‹የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ወይም ሞት!!!››ግድቡ ለመቶ አስር ሚሊዮን ህዝብ የህልውና ጉዳይ ነው፡፡ አገራችን ኢኮኖሚ በግብርናው ዘርፍ ጠኔና ርሃብ የእለት ቀለባችን ሆኖ ለዘመናት በመቀጠሉ በዓለም አቀፍ ህብረተሰብ ቀለብ ሲሰፈርልን ኖረናል፣ የህዝባችን የርሃብ የሞትና የስደት ታሪካችን አክትሞ ኢትዮጵያ በምግብ ራሶን እንድትችል የቀጣዩ ትውልድ ህይወት እስትንፋስ ጥያቄ ላይ ምንም ድርድር አይኖርም፣ በኢንዱስትሪ የፋብሪካ ምርቶችና ሸቀጣ ሸቀጦች ምርት መትረፍረፍ፣ እንዲሁም  የአገልግሎት ዘርፍ መሰረተ ልማቶች ግንባታ የመንገድ፣ የባቡር፣ የዓየር፣ የኤሌትሪክ ኃይል ማስፋፋት መሰረተ ልማት ለስልሳ አምስት ሚሊዮን ህዝብ ለዘመናት በጨለማ ውስጥ ያለ ብርሃን መኖር ሊያበቃ ግድ ይላል በዚህ ምንም ድርድር የለም፡፡ አገራችን በዓለም የፖለቲካና ኢኮኖሚ ሴራ የግብፅ፣ ሱዳን፣ የአረብ ሊግ፣ እስራኤል፣ አሜሪካ፣ የአውሮፓ ህብረት ወዘተ አገራቶች እጃቸውን ከኢትዮጵያ ሃገራችን ላይ እጃቸውን ማንሳት ግድ ይላቸዋል፡፡ የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አራት የኒውክለር ማብላያ እምቅ ኃይል ያላት አገር ሆናለች፡፡ ይህን ለማስቆም ነው በባዕዳን ኃይሎች ከሃገር ውስጥ የሽብር ኃይሎች ጋር የውክልና ጦርነት ከተለያየ አቅጣጫ ጦር የሚወረወርባት፡፡ ኢትዮጵያን የነካ!….ግድቡን የነካ!.. የውኃ ጥፋት ዘመን … የኖህ ዘመን ያሸጋግራቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ሆኖ ጠላቶቹን በመመከት የሚቀጥለውን ዘመን መሻገር የህልውና ጉዳይ ነው፡፡
  • ዩኤስ አሜሪካ በአወጀችው አዋጅ መሠረት ብሔራዊ ደህንነትና (national security) የኢኮኖሚ ደህንነት (economic security) በተናጥል ሊታዩ አይገባም፡፡ ዩኤስ አሜሪካ በደህንነት ስትራቴጂክ ማዕድናት  አቅርቦት መሠረት፣ የአፍሪካ ቀንድ አገሮች ስትራቴጂክ ማዕድናት አሎቸው ከነዚህም ውስጥ- ኮፐር፣ ታንታለም፣ ኒዬቢየም፣ ፎስፊት፣ ናቹራል ጋዝና፣ ሌሎች የተፈጥሮ ኃብቶች በአፍሪካ ውስጥ ተቆልፈው ይገኛሉ፣  እናም ለመጠቀም ዝግ ናቸው፡፡ ስለዚህ ልዕለ ኃያላን ሃገራት የአፍሪካን ብረታ ብረት ማዕድናት በመጠቀም አረንጎዴውን ኢኮኖሚ መገንባት ፍላጎት አላቸው፡፡ ቻይና መንግሥት በአፍሪካ ቀንድ አገሮች የኢኮኖሚ ግንባታና የትራንስፖርት መሰረተ-ልማት ግንባታ፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በዲጂታል ቴክኖሎጅ፣ የፋይናንስና ባንኪንግ ዘርፍ ለአፍሪካ አገራት፣ የባንክ ብድር አገልግሎት በመስጠት ለአፍሪካ ህዝብ ተደራሽ በመሆናቸው  የቻይና ልዕለ ኃያልነት በአፍሪካ ተመራጭ ለመሆን ችለዋል፡፡ አሜሪካ የቻይና የኢኮኖሚ የበላይነት በአፍሪካ ምድር በመስፈኑን ለማስቆም የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡ ሆኖም ዘመኑ በማይመጥነው ባአረጀና ባፈጀ  በስመ ዴሞክራሲ የሚጫወቱት የቅኝ ግዛት ዘመን ፖሊሲ፣ አንባገነናዊ አገዛዝ በአፍሪካ እንዲሠፍን በማድረግ፣ በአፍሪካ ሉዓላዊ ሃገራት መብቶች ጣልቃ በመግባት፣ የዓለም አቀፍ ባንክ፣ አይ ኤም ኤፍ ወዘተ የበሰበሰ ሥርዓት ለመገርሰስ ታዳጊ አገራቶች ከቻይና፣ ሶብየት ህብረት፣ ህንድ፣  ወዘተ ጋር ህብረት ፈጥሮ የዓለም አቀፍ ሥርዓት መለወጫው ጊዜ በአሜሪካ የውሸት ዴሞክራሲ መቃብር ላይ መሆኑ ለዓንድ አፍታ አትጠራጠር፡፡አሜሪካ በኢራቅ ህዝብ፣ በሲሪያ ህዝብ ላይ፣ በየመን ህዝብ ላይ፣ በሊቢያ ህዝብ ላይ የፈጸሙት የመንግሥት ለውጥ ‹‹régime Change ›› ታሪክ ይቅር ማይለው የአሜሪካ ልዕለ ኃያል መንግሥት አገዛዝ መውደቅ አይቀሬ ነው፡፡ አሜሪካ በኢትዮጵያ ‹የመንግሥት ለውጥ› የፖለቲካ ሴራ እውን አይሆንም፡፡ አበው ‹‹ኃይማኖት የግል ነው፣ ሃገር የጋራ ነው›› ያሉት ብሂል ዛሬም የዘር ፖለቲካ የግል ነው፣ ሃገር የጋራ ነው በማለት የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድ ላይ ቆሞል፣ ከቶል፡፡
  • የማህበራዊ ሚዲያ፣ የኮምፒውተር ኪቦርድ (keyboard warriors) የኮምፒውተር ቁልፎች ጦረኞች የዓለም አቀፍና የአፍሪካ ቀንድ የዲጂታል ዲፕሎማት የትምህርት ሥልጠና በመስጠት ከፍተኛ አልሞ ተኮሽ ወጣት የድህረ ገፅ ብሎገሮችና አክቲቪስቶች ማፍራትና እውቅና መስጠት የጊዜው አንገብጋቢ ጉዳይ ነው፡፡

 

ትህነግን ለማዳን አሜሪካ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ የአረብ ሊግ ፣ ግብፅ፣ ሱዳን ወዘተ አገራቶች  ለምን ፈለጉ? ትህነግ የአማራ፣ የአፋርና ኤርትራ  መሬቶች ቢመለሱለት ትግራይን እያስተዳደረ ይኖርል ብሎ መሬቶቹን ቀስ በቀስ ለትህነግ እየለቀቁ የመሄድ የጦር ስትራቴጅና  ስልት ነገ ትህነግ አዲስ አበባ ቤተ መንግሥት ሰተት ብሎ እንደሚገባ ማድረግ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡  የአሜሪካና የአውሮፓ ህብረት የሚፈልጉት በትህነግ ‹‹የመንግሥት ለውጥ ‹‹régime Change ›› ማድረግ መሆኑን መዘንጋት ፖለቲካ ማሃይምነት ነው፡፡  ይህ አዲሱ የውክልና ጦርነት በኢትዮጵያ? ከትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ግንባር ሆድቃ የተገኘ ጥቁር ሰንዱቅ!!! Ethiopia: A New Proxy Battlespace? “Black Box in the TPLF’s Belly”

አዲሱ የውክልና ጦርነት በኢትዮጵያ? Ethiopia: A New Proxy Battlespace? በፕሮፌሰር አን ኤም ፊዘርላንድና ሆን ሁህ ሴጋል የቀረበ ጥናታዊ ፁሁፍ በኢትዮጵያ ሃገራችን ላይ በልዕለ ኃያላን መንግሥቶች የፖለቲካ ሴራ  አዲስ የውክልና ጦርነት በመክፈት የአገራችን እጣ ፈንታ እንደ ኢራቅ፣ ሶሪያ፣ ሊቢያ፣ የመን  እንዲሆን ተፈርዶብናል፡፡ የእንጊሊዘኛውን ፁሁፍ ከድር-ገፁ ማንበብ ይችለሉ፣ መልካም ንባብ፡-

 

የአሁኑ ወቅት ትርክት (Current narratives)

በአሁኑ ጊዜ የተከሰተው የትግራይ ጦርነት ትርክት ስፋት ካለው  ከርቀት እይታ፣ አስተያየት እንዲሁም  የተለያዩ  ጥቅም ያላቸው አገራቶች ሚናቸው በኢትዮጵያ ምን እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል፡፡  በኢትዮጵያ በስተ ሰሜን በትግራይ ክልላዊ መንግሥት የተቀሰቀሰው ጦርነት ውስጥ ለውስጥ እርስ በእርሳቸው የሚገናኙና  የተያያዙ ሁለት የጦር ግንቦሮች ተከፍተዋል፡፡  የመጀመሪያው  በአካል በምድሪቱ ላይ የተከፈተው  የጦር ግንባር ሲሆን ሁለተኛው  የጦር ግንባር ደግሞ አደገኛው  የመረጃ መረብ ዘመቻ የተከፈተው በማህበራዊ ሚዲያ በኩል ሲሆን ህዝቡን ለማነሳሳት፣ ለመሳብ፣ ለመጠምዘዝ እና ቀጥተኛ ዓለማ አቀፍ አጸፋዊ  የዘረኛነት ስሜት  ያስተጋባል፡፡ በተመሳሳይ በአፍሪካ ቀንድ አገራት ላይ የጂኦ ፖለቲካል ጥቅም  ያላቸው በአካባቢው ያሉ የተለያዩ ዋነኛ ኃይል ያላቸው አገራቶች እንዲሁም ልዕለ ኃያላን አገራቶች ለምሳሌ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ቻይና፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ፈረንሳይ አገራቶች ጥቅም ድብቅ ሆኖ ቆይቶል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታዎችና ሌላ ቦታና በፊት እያቆጠቆጠ የመጣ ስትራቴጂክ ጥቅምና የዓለም አቀፍ ተዋናዬች ውሳኔዎች ሊጫወቱ የሚችሉት ሚና ከሁለት አንዱ ለአካባቢው ግጭትና ጦርነት ዘለቄታዊነትና ቀጣይነት ያለው መፍትሄ ማስገኘት ወይም ግጭትና ጦርነቱን ማባባስና ማቀጣጠል ሚና ይኖራቸዋል፡፡

 

ተወዳዳሪውና ተፎካካሪው ትርክት (Competing Narratives)

የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ግንባር (ትህነግ) በተቀናበረ ፕላን ‹‹መብረቃዊ ጥቃት›› በመፈፀም ግጭቱንና ጦርነቱ የቀሰቀሰው በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥት የሰሜን እዝ መከላከያ ሠራዊት ወታደራዊ መከላከያ ጣቢያና ካንፖች ላይ ነበር፡፡ ሆኖም የማህበራዊ ሚዲያ፣ የኮምፒውተር ኪቦርድ (keyboard warriors) የኮምፒውተር ቁልፎች ጦረኞች ከፍተኛ ሥራ የትህነግ የመከላከል እርምጃ ‹‹መብረቃዊ ጥቃት››‘(pre-emptive attack’) እንደሆነ በመግለፅ በተቃራኒው በማቀድ የተሳሳተ ዜና በመፍጠር በኢትዮጵያና ኤርትራ  ላይ የተባለ የጋራ ስጋት መግለጫ በማውጣት የዓለምን ህብረተሰብ አሳሳቱ፡፡ ከባድ ማስረጃ ያልቀረበበት ክስ በዘር ማጥፋት ላይ ተሠራ፣ በአባሪነትም የኤርትራ ወታደሮች የወሲብ ጥቃት መፈፅማቸው ተወራ፡፡ በማህበራዊ ሚዲያ የስብዓዊ ድጋፍ (humanitarian aid) ለማድረግ የትግራይ ክልል ሰማንያ በመቶ ሥነ-ምድራዊ አቀማማጥ ረድኤት ለመድረስ አስቸጋሪ የሆነ የማይደረስበት በመሆኑ የጠኔና የርሃብ አደጋ እንደሚከሰት ዘገቡ፡፡ የትህነግ አፈቀላጤ ከሚቆጣጠሩት አካባቢ ሆነው የተገንጣይነት ስሜት እንዳለ የሚጠቁም የመገንጠል ስሜት  በትግራይ ህዝብ  ዘንድ እንዳንዣበበ ያትቱ ነበር

 

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥት ለአራት ሚሊዩን ሁለት መቶ ሽህ ህዝብ የስብዓዊ ድጋፍ በትግራይ ክልል ውስጥ ማከፋፈሉን በተደጋጋሚ አሳስቦል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት በታሪካዊዋ የአክሱም ከተማ የሰባት መቶ ኃምስ ሰዎች ግድያ ታማኝነት ማስረጃ ያልቀረበበት ክስ ላይ ጥያቄ አቅርቦል፡፡ እንዲሁም የምዕራባዊን ሃገራት ሚዲያ የፌዴራላዊ መንግሥት በጦር ወንጀለኛነት ይከሳሉ፡፡  የምዕራባዊያን ሚዲያ ትህነግ በፌዴራል መንግሥት የሰሜን እዝ ወታደሮች ላይ ወታደራዊ ጥቃት  እንዳልጫረ አረጋግጠናል ይላሉ፡፡ እንዲሁም በህገወጥ መንገድ የኤርትራ ወታደራዊ ዩኒፎርም በትግራይ ፋብሪካዎች የማኑፋክቸሪንግ ሥራ አስመሳሎ አለመሠፋታቸውን አረጋግጠናል ይላሉ፡፡ የፌዴራል መንግሥት በትግራይ ክልል የሚገኙ ስደተኛ ካንፖች በአስር ሽህዎች የሚቆጠሩ የኤርትራ ስደተኞች እንዲሁም ከአስር ሽህ የሚበልጡ እስረኞች በትህነግ ቁጥጥር ሥር ያሉ እስካሁን እንዳልተመዘገቡ አረጋግጠዋል፡፡

የአዲስ አበባ ባሥልጣናት መሰረቱን በትግራይ ምድር ያደረገ ነባራዊ ሁኔታን የሚያሳይ አስረጂ የሚዲያ ሪፖርት መኖሩን በተከታታይ አውቀው ዘንግተውታል:: ይህም የሚያካትተው ‹‹አንድ ለአምሥት›› (‘one in five’ authoritarian intelligence network) የትህነግ አንባገነኖች የስለላ መረብ በትግራይ ምድር የትም ቦታ ከአምስት ሰዎች አንዱ ሰላይ የሆነበት የትግራይ አንባገነን መንግስት  መሆኑን በተጠናከረ ማስረጃ ማጋለጥ ከፍተኛ ውጤት ያስገኛል፡፡  በ2005እኤአ (1997ዓ/ም) ኢህአዴግ   በአዲስ አበባ ከተማ የፌዴራል ምርጫ አንድ ወንበር ካጣ በኃላ ወያኔ የማርክሲስት ሌኒኒስት የቁጥጥር ሥርዓት ዘርጋ፡፡ ይህ አንባገነናዊ የፖለቲካ ባህል መዘርጋት ሁለት ነገሮች ማድረግ አስቸሎታል ትህነግ በማስፈራራት እና አስፈላጊ ቁጥጥር ‹በግጭት ትርክት› ላይ ማድረግ ቻሉ፡፡ በተጨማሪም ለአራሹ ገበሬ ሥልጠና ሰጥቶ የማስታጠቅ የቆየና የኖረ ብህልና ልምድ  በቀጣይነት 250000 (ሁለት መቶ ኃምሳ ሽህ)  ክልላዊ ሚሊሽያ ጦር በመገንባት ከብሔራዊ መከላከያ ሰራዊት ጋር አመሳሰሉት ገነባ፣  ትህነግ  ከማዕከላዊ ኮማንድ የተገለሉ የትግራዋይ የሠራዊቱ አባሎች ተግባራዊ የሽምቅ ውጊያ ሥልጠና ታክቲክ ይሠጡ ጀመር፡፡  ምንም እንኳን ሁለቱ ትርክቶች ዋልታ ረገጥ ቢሆኑም የምዕራባዊያን ሚዲያዎች ምርጫቸውን በመያዝ ትህነግ ‹‹የሰው መቀለጃ›› አሳዛኝ ድርጅት አድርገው በመግለፅና  በመሳል እንዲሁም በስፋት ቶሎ የሚያምንና በቃላት የሚደለል  መልእክት ያስተላልፉ ነበር፡፡ ሆኖም አንዳንድ የውጭ ተዋናዬች  ደግሞ ፍርድ ለመስጠት በመቸኳል የኢትዮጵያ መንግሥት ዘር በማፅዳት እና የውጭ ሠራዊት በማስገባት የክልሉን ተቃዋሚ ትህነግን ከወንጀሉ ገለልተኛ በማድረግ ተጨባጭ ሁኔታውን ይበልጥ እንዲወሳሰብ አድርገዋል፡፡ ስለዚህ ነፃና ገለልተኛ ምሁራዊ ምርመራ በማድረግ ከህግ ጋር ተያያዥነት ያለው ሳይንሳዊ ማስረጃ በማቅረብ እውነቱን ማጣራትና ማወቅ አስፈላጊና አስቸኳይ ነው፡፡

 

ሠፊው የጦር ሜዳ (The Wider Battlespace)

ይህንን ከመመርመራችን በፊት፣ መጠየቅ ያለበት ነገር ቢኖር ለምን ዋነኛዋ የአፍሪካ ሃገርና የረዥም ዘመናት የምዕራባዊያን ሃገራት ወዳጅ የነበረች ሃገር በድንገት እንደ አሮጌ ቁና ተጥላ፣ ተገልላና ድርጊትና ተግባሯን ጥንብ እርኩሷን አውጥተው የመረጃዋን ፍሬ ነገር  በተሳሳተ መንገድ መተርጎምና መረዳት ምዕራባዊያን ሃገራት ከጀመሩ ውለው አድረዋል፡፡  ይህን ጥያቄ ለመመለስ በመጀመሪያ አስፈላጊ የሆነውን ከሁኔታው የሚዛመደውን ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑትን ሁለቱን የውኃና የተፈጥሮ ኃብት ሁኔታዎች በአፍሪካ ቀንድ ጂኦ ፖለቲካል ውድድርና ፉክክር ሁኔታን መተንተን ያስፈልጋል፡፡

ግብፅ አሁንም በዩኤስ አሜሪካና በመካከለኛው ምስራቅ የሠላም መርሃ ግብር ዋና ተዋናይ ስትሆን እንዲሁም ሱዳን ደግሞ በሁለቱም  የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ (Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD)) ወኃ ለመሙላት ተወዳዳሪ ፕላን በማቅረብ እና  የውኃ ድርሻ ክፍፍል ዝግጅት በማድረግ ትሳተፋለች፡፡  የሱዳን ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር በመውረርና ብዙ ገበሬዎችን በማፈናቀል በተፋላሚና ተፎካካሪ ድንበር ማህበረሰብ (contested border community) ገዥ መሬት በመውረር ለመያዝ ችለዋል፡፡ ለረዥም ጊዜ ግብጽ ፀረ- ኢትዮጵያ የሽንገላ ንግግር እየጨመረ በመሄድ የጠበኛነት ሰሜት፣ የካይሮ ማስጠንቀቂያ ለአዲስ አበባ ታሪከዊ የውኃ ድርሻ የማይነካና የማይካፈል የበላይነት ስሜት የመጫን አንባገነናዊ አገዛዝ የናይል ውኃ ድርሻ ለውይይት የማይቀርብ (non-negotiable) ይሉታል፡፡ በጋራ በመሥራት ግብፅና ሱዳን የጋራ የዓየር ኃይል ወታደራዊ ልምምድ (demonstration of joint air power ) ሲያደርጉ በማግስቱ ትህነግ የትግራይ ግጭት ጫረ፡፡ ሁለተኛው የጦር ልምምድ ክፍል መጠሪያው የናይል ኢግልስ ‹‹‘Nile Eagle’›› ዘመቻ  ትኩሱ የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ  ውይይት ከመጀመሩ አንድ ቀን በፊት በአፕሪል ስድስት ነበር፡፡ የግብፅ፣ ሱዳንና ኢትዮጵያ የሥስትዬሽ  ውይይት ሲጨናገፍ የማይግባቡበት ደረጃ ሁኔታ ተባብሷል፡፡  የዓለም አቀፍና ክልላዊ ተዋንያኖች የሥስቱን አገራቶች ውይይት እንዲቀጥል ለመርዳት የግድቡን ውኃ ሙሌት የማይስማሙበት አጣብቂኝ ነጥቦች  ለማቃለል መፍትሄ በመፈለግ  የአፍሪካ ህብረት፣ የአውሮፓ ህብረት፣ ሳውዲ አረቢያና ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ ላይ ተገናኝተው ነበር ፡፡ እስራኤል ደግሞ  ከግብፅ ውጤት መሳካት ጋር ቀጥተኛ ጥቅም  ታገኛለች፣ የናይል ውኃን በሲናይ በርሃ በኩል በማሸጋገር (the transfer of Nile water across the Sinai) ወደ ደቡባዊ እስራኤል ኒጌቨ በርሃ ውሃው እንዲዘልቅላት ትፈልጋለች፡፡ እስከዚ ድረስ የዲሞክራክቲክ ሪፓብሊክ አፍ ኮንጎ ፕሬዤዳንት ፌሊክስ ሺሴኪዲ የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የግድቡን የሶስትዬሽ ውይይት (tripartite negotiations) እንዲዘጋጅ ጥረዋል፡፡ በ2019እኤአ የኮንጎ ታላቁ ኢንጋ ግድብ  የአረንጎዴ ኢነርጂ ዋነኛ መልህቅ ሆኖ በመዘዋወርና በአፍሪካ ያለን የኤልትሪክ ኃይል እጥረት  መፍትሄ ሆኖል:: የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተመሳሳይ የግንባታ እምቅ  ኃይል ይዞል፡፡

 

የልዕለ ኃያላን ተሳትፎ (Great Power Involvement)   

በልዕለ ኃያላን አገሮች ተዋናዬች የህብረት ግንባር በመፍጠር የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕላን እንዲቀየር ግፊት በማድርግ ላይ ይገኛሉ፣ አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዤዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር የላከው ጠንካራ ሴኔተር ክሪስ ኩንስ ወደ አዲስ አበባ ሄደው  የኢትዮጵያን ጠቅላይ ሚኒስቴር እንዲያገኙ ታዘው ነበር፡፡ ለማመን የሚከብደው ነገር የናይል ወንዝ በአጀንዳው ውስጥ አልነበረም፡፡ ዩኤስ አሜሪካ በአወጀችው አዋጅ መሠረት ብሔራዊ ደህንነትና (national security) የኢኮኖሚ ደህንነት (economic security) በተናጥል ሊታዩ አይገባም፡፡ በዚህም የተነሳ ሃሳብ በማፍለቅና በማበረታታት የመቶ ቀናት ግምገማ ምርመራ በጃክ ሱሊቨአን፣ ብሔራዊ ደህንነት አማካሪ፣ ዩኤስ አሜሪካ በደህንነት ስትራቴጂክ ማዕድናት (ሚኒራልስ) አቅርቦት መሠረት፣ የአፍሪካ ቀንድ አገሮች ስትራቴጂክ ማዕድናት አሎቸው ከነዚህም ውስጥ- ኮፐር፣ ታንታለም፣ ኒዬቢየም፣ ፎስፊት፣ ናቹራል ጋዝና፣ ሌሎች የተፈጥሮ ኃብቶች በውስጥ ተቆልፈው ይገኛሉ፣  እናም ለመጠቀም ዝግ ናቸው፡፡ አረቢያን-ኑቢያን ሼልድ  ለዩኤስ አሜሪካ ጥቅም አላቸው፡፡

በዩኤስ አሜሪካና በቻይና መኃል ባለ የዓለም አቀፍ ንግድ ውድድር ማደግ የተነሳ ቻይና በአሁኑ ጊዜ የዓለማችን የኢኮኖሚ እድገት በአረንጎዴውና በመረጃ ዘመን ቴክኖሎጂ ፣ቤልት ኤንደ ሮድ  እንዲሁም በሌሎች ኢንቨስትመንት እድገት – የዓለም አቀፍ ቁልፍ የብረቶች አቅርቦትን መቆጣጠር  ችላለች፡፡ አሜሪካ ከቻይና በኢኮኖሚ እድገት ወደኃላ ቀርታለች፣ ቻይና በአፍሪካ ኢንቨስትመንት የኢኮኖሚክ አጋር ሆናለችና አሜሪካ በመከተል ላይ ትገኛለች፡፡ በአገባቡ በተጠቀሰ መሠረት የትግራይ ጦርነት በኢትዮጵያ ውስጥ መታየት የሚገባው የጦርነት ትያትር አንዱ ተውኔት የውክልና ጦርነት  በውጭ ኃይሎች  የሚከናወን ሲሆን በሂደቱም የኢትዮጵያ ፖሊሲ አውጭዎች ላይ ተፅዕኖ ማሳደር ነው፡፡ ህጋዊ ሰውነት ያለው የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርብ ጊዜ ውስጥ የተደነቀው ከኤርትራ ጋር ባደረገው የሠላም ስምምነት በዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ዘንድ ድጋፍ አግኝቶል፡፡ በትህነግ  ሠላም ለማደፍረስ የሚደረገውን የህልውና ስጋት መክቶ መመለስ ከባድ ሥራ ያስፈልጋል፡፡ የዘገየውን ህዝባዊ ምርጫ አከናውኖ  አንባገነናዊ መንግሥታዊ ባህል ማስወገድና የትግራይን  የጦር አበጋዞች የሽምቅ ውጊያ ለዘለቄታው ማስቆም ያሻል፡፡ ምን ያህል ኢትዮጵያዊያን በዓለም አቀፍ ህብረተሰብ ድጋፍ ያገኛሉ ሌሎች አማራጭ ውጤቶችን ጠቀሜታ ላይ መዋሉ እንዲታይ ያሻል፡፡

የምዕራባዊያን አገሮች ህጋዊና ታማኝ ተቆርቆሪነት ለክልላዊ መረጋጋት በተጨማሪ ካላቸው የኢኮኖሚ ጥቅማቸው ምዕራባዊያን አገሮች እየተካሄደ ባለው የትግራይ ጦርነት ፍርድ ለመስጠት መቸኮል የለባቸውም፡፡ በሱ ፈንታ ምዕራባዊያን አገሮች ከዴሞክራቲክ ፌዴራል የኢትዮጵያ መንግሥትን በማበረታታትና መደገፍ ቃል በመግባት የጋራ  ጥረት ቢያደርጉ  ይሻላል፡፡ ምዕራባዊያን በኢትዮጵያ የሃገር ውስጥ ጉዳይ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳይ መሻሻሎች በማየትና  የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውይይት ምክንያታዊ በሆነ አሳማኝ መረጃዎች በመደገፍ ቃል መግባት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ መደራደሪያ ጥሩ እድል ለአፍሪካ ቀንድ አገራትን ወደ ብልፅግና ያመራቸዋል፡፡ ይህ ተግባራዊ ካልሆነ በአፍሪካ ቀንድ አገራት አለመረጋጋት ማንሰራራት አይቀርም፣ ሌሎች ተዋናዬች ጣልቃ ገብነት ማስቀረት አይቻላቸውም፣ በቀጠናው አል ሻባብ መራሽ የሽብር ኃይል ጥሶ መግባትና መውረር  እንዲሁም  አዲስ የህዝብ ስሜትና በማነሳሳት ለሥልጣን ማግኛ የሚጠቀሙ የጦር አበጋዞች በአፍሪካ ቀንድ አገራት ማቆጥቆጡ አይቀሬ ነው፡፡ ትህነግ በማህበራዊ ሚዲያ ግነት፣ የተጋነነና የሚያጋንን የሚያነሳሳ የስክሪን ጭስ የሃገር ውስጥ ተዋናዬችን የወሰዱት አቌም ስር የሰደደ የውሸት ዜና ምሽግ ገንብቶል፣ በተለይ የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብና የዓለም አቀፍ የልዕለ ኃያላን ሃገራት የአፍሪካን የተፈጥሮ ኃብት የብረታ ብረቶች ማዕድናቶችን ለእራሳቸው አረንጎዴ ኢኮኖሚ ጥቅም ላይ ለማዋል ሁኔታዎች እንዲመቻቹላቸው ይሻሉ፡፡  ይህ አደገኛ ጨዋታ ነው፣ ጨዋታው ከተሸነፉ ክፍተቱ እየሠፋ ሄዶ፣የወደፊት እጣ ፈንታ የቻይና የኢኮኖሚ የበላይነት በአፍሪካ አገራት ላይ አይቀሬ የሚሆነው፡፡ የምዕራባዊያን የተፈጥሮ አጋር ኢትዮጵያ ነበረች፣ ይህን ድክመትና መሰናከል ምርጫ፣ ድጋፍና ግጭት ለመገንዘብ ከባድ ሥራና ጥረት በእኩልነት ይጠይቃል፣ ይህን ችላ ማለት የታላቁ የስትራቴጅክ ተጠቃሚነት ከአጋር አገራቶች ጋር አለማጣጣም በእርግጥ የአፍሪካ ቀንድ አገራቶች የሠለምንና ደህንነትን በስፋት ያናጋል፡፡‹‹The TPLF-inspired social media hyperbole makes a compelling smoke screen as local players entrench their positions regarding the Nile’s water and global powers seek to secure access to African metals for their green economies. This is a risky game – and if lost, it is sure to widen the space for China’s future economic dominance in the region. The West’s natural partner is Ethiopia; failing to embrace this choice and help it with its conflict efforts is tantamount to ignoring the greater strategic benefits that come with partnership, and will surely destabilise the region further.››

ወደፊት ዩኤስ አሜሪካ ከአዲስ አበባ ጋር ወዳጅነትና አጋርነት ከመሠረተች፣ የጦርነት ግጭቱን ባለማማባስ በሁለቱም ዘርፎች አንደኛው አደገኛው  የመረጃ መረብ ዘመቻ የተከፈተው በማህበራዊ ሚዲያ ሲሆን ሁለተኛው በአካል በምድሪቱ ላይ የተከፈተው  የጦር ግንባር ነው፡፡ ዩኤስ አሜሪካ ሁሉም ፓርቲዎች ላይና አጋር አገራቶች እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት ጋር  በመሆን  የተቆረጠውን ውይይት ማስቀጠልና በመርዳት ግብፅና ሱዳን ለውኃው ግጭት መፍትሄ በመስጠት ይኖርባታል፡፡ ‹‹If the US wants to partner with Addis in the future, it should be helping to de-escalate the conflict – both in the media and on the ground. It should use its considerable influence over all parties and partner with the African Union to help broker a fair and reproducible solution to the water crisis with Egypt and Sudan.›› The views expressed in this Commentary are the authors’, and do not represent those of RUSI or any other institution. ››

ምንጭ፡-

Ethiopia: A New Proxy Battlespace?Professor Ann M. Fitz-Gerald and The Hon. Hugh Segal OC OOnt CD/19 April 2021 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.