የትግራይ ሕዝብ እባክህ ንቃ! ተወያኔ ተፋታና እንደ ታሪክህ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ተጋባ!

e66sobwwua0fal9

የትግራይ ሕዝብ እባክህ ንቃ! ወያኔ በስምህ እየነገደ ልጆችህን የሚያስፈጀው እስከ መቼ ነው? ወያኔ ያልነበረ ታሪክ እየፈጠረ በአንተ ስም አገርህን ኢትዮጵያን እንደ ጣቃ ጨርቅ ቦጫጭቆ ጣለ!

ወያኔ ልጆችህን በእሳት ማግዶ አስጨርሶ በውጪ ሐይሎች ትከሻ ስንልጣን ሲይዝ ተሞት የተረፉትን ልጆችህን ወደ መጡበት መልሶ የራሱን ልጆችና ዘመዶች በሐብት ሲያጎልበት፣ በውጪ አገር በተዘረፈ ገነዘብ ሲያስተመርና ሲያንደላቅቅ ኖረ፡፡ ወያኔ ኢትዮጵያ እንዳትቦጫጨቅ የተቃወሙትን የትግራይ አዛውንት በአንተ ስም እየነገደ ጨፈጨፈ!

ወያኔ በስምህ እየነገደ የአማራንና የኦሮሞን ሕዝብ በመደዳ ሲገድልና በእስር ቤት ሲያጉር፣ ጉራጌውን ተስራ ሲያገል፤ ሲዘርፍ ኖሮ ሕዝቡ በምሬት ሲነሳበት አሁንም ራሱን ሊያድን ልጆችህን ለጦርነት ማገደ! ወያኔ በስህ እየነገደ ጋንቤላን ወሮ አኝዋኮችን ጨርግዶ መሬቱን እያረሰ በሐብት ሲደልብ ኖረ፡፡ ወያኔ በስምህ እየነገደ የኢትዮጵያን ሱማሌዎች በጀታቸውን ሲበላና እየረሸነና መሬት እየጎተተ ሲያሰቃያቸው ኖረ፡፡

ወያኔ የኢትዮጵያን ሐብት እየዘረፈ በአውሮጳና አሜሪካ ሲያከማች ኖረ፡፡ ወያኔ የኢትዮጵያን እናቶች፣ አባቶችና ልጆች እየገደለ መሬቱን ደም ስለቀባው ዛሬ እዳው ለአንተም ተረፈ፡፡ ወያኔዎች የራሳቸውን ልጆች በውጪ እያንደላቀቁ ዛሬም አንተን አታለውና ሕፃናት ልጆችህን አስገድደው በጦርነት እየማገዱ ነው! የትግራይ ሕዝብ ልብ በል! የኢትዮጵያ ሕዝብ ድሮ ተነብሩት፣ ዛሬም ታሉት ሆነ ነገ ከሚመጡት የትግራይ ልጆች  ወንድምና እህት ነው፡፡ ችግሩ ተጭራዉ ተወያኔ ጋር ነው፡፡ የትግራይ ሕዝብ እባክህ ንቃ! ተወያኔ ተፋታና ከኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ ታሪክህ ተጋባ!

1 Comment

 1. የሰው እንባና ደም የማይገደው ወያኔ የትግራይ ህዝብ መንቃት እንዳይችል ካደነቆረው ቆየ። ሁልጊዜ መጡባችሁ በማለት ሰውን ከሰው፤ ሃገርን ከሃገር እያላተመ ዛሬ ላለበት የሞትና የሽረት ትግል ደርሷል። ሻቢያ ሊበላህ ነው፤ አማራ ቀንደኛ ጠላትህ ነው እያለ አሁን ደግሞ የአብይ ጦር ጨረሰን ድረሱልን እያለ ነጩንና ዓረቡን አለም የሚያማታው ወያኔ ከሰው ተራ የወጣ የእንስሳት ክምችት ነው። በቅርብ ጊዜ ከሆኑ ነገሮች ጥቂቶቹን ላስረዳ።
  ወያኔ ጦርነት ከፍቶ ራሱ በ 27 ዓመት ያደራጀውን ጦር ከተኙበት ካረደ በህዋላ በተከፈተው ያልሞት ባይ ተጋዳይ ፍልሚያ ብዙዎች ከሁለቱም በኩል አንቀላፍተዋል። ሰዎችም ወደ ሱዳን ተሰደዋል። ሱዳን ባሉ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ አሁን ወያኔ መቀሌን ተቆጣጠርኩ የኢትዪጵያን ሰራዊት በሚያስደንቅ ውጊያ ድምጥማጡን አጠፋሁ እያለ በሚፏልልበት ጊዜ ወደ ሃገራችን መመለስ እንፈልጋለን ያሉ የትግራይ ልጆች በሱዳን ይደበደባሉ፤ ይሰደባሉ፤ ምግብ ይከለከላሉ። ለምን? ለወያኔ ዋና የመለመኛ ኮሮጆና የወታደር ምልመላው የሚከናወነው በስደተኞች ካምፕ ውስጥ ነው። ከደ/ሱዳንና ከዳርፉር አንመለስም ያሉ የቀድሞ የወያኔ የመከላከያ ሰራዊት አባሎችና ሌሎችም ስልጠናውን በመስጠት ትጥቅና ስንቅ ከሱዳንና ከግብጽ በመበቀበል አሁን እንሆ ህዝባችን እንደገና ለድጋሚ መጨራረስ እያዘጋጅት ይገኛሉ። ከዚህ ባሻገር መሬታችን እናስመልሳለን በማለት ከራር እየተመታለትና ከበሮ እየተደለቀለት በሃሺሽና በሌላም መተት ተተብትቦ ዛሬ በአማራ ክልልና በአፋር ግንባር እንደ ቅጠል የሚረግፈው የትግራይ ወጣት ቤቱ ይቁጠረው።
  በፓለቲካ ሴራ ብቻ በስልጣን ላይ መኖር የሚሻው ወያኔ ነጻይቱ ትግራይ እያለ ” በውሸት በእልልታ ብቻ በባርነት መኖርን” ለትግራይ ህዝብ ያስተማረ አፋኝ ድርጅት ነው። ይህን መረዳት የሚችል ሰው አይኑ የተከፈተለት በዘርና በቋንቋው ወይም በሃይማኖቱ ተገን ያልያዘ ገለልተኛ ፍጡር ብቻ ነው። የትግራይ ህዝብ ከወያኔ ጋር ለመፋታት ሆ ብሎ በመነሳት ወያኔንና ካድሬዎችን ማጥፋት ይኖርበታል። ያ ደግሞ ጭራሽ አይታሰብም። እግሩና እጅ በወያኔ የውሸት ቱልቱላ የታሰረ ህበረተሰብ በራሱ አስቦና አልሞ መኖር አይቻለውም። ገና የዚህ ዓይነት ሃሳብ ዘሩ ሲዘራ የወያኔ ገዳይ ሃይሎች ፈጥነው የሚያስቡ ሰዎችን ያጠፋሉ። ትላንት በኢትዮጵያ ለ 27 ዓመት ሲንደላቀቅ የነበረው ወያኔ ለትግራይ ህዝብ የሚጠጣ ውሃ እንኳን አላቀረበለትም። ግን አሁን በራሳቸው የፓለቲካ ስህተት ከስልጣን ተሽቀንጥረው በትግራይ ሲወሸቁ ህዝቤ፤ ሃገሬ ማለታቸው ራስን በስልጣን ላይ ለማሰንበት እንጂ ለትግራይ ህዝብ ትርፍ የለውም። የትግራይ ህዝብ ለጋዜጠኞች እንኳን የሚናገረውን እንዲህ በሉ ተብሎ ተነግሯቸው ነው የሚናገሩት። ወይም አስተርጓሚው አጣሞ እንዲያስተረጉም መመሪያ ይሰጠል።
  ሁለተኛው ነጥብ በአፋር ግንባር የተማረኩ የወያኔ ሰዎች ሲናገሩ እንደተሰማው ውሸት እንደተጋቱ በትክክል መረዳት ይቻላል። መሪዎቹ ሮጠው ያልጠገቡ ህጻናት ልጆችን ጦርነት ውስጥ ማግደው እንደሚሸሹ እየተናገሩ ነው። ከበሮ ይዞ መዝለልና ፊት ለፊት በውጊያ ቀጠና ውስጥ ገብቶ መዋጋት ለየቅል ነው። የፎከረው ሲሸሽ፤ ያፏከረው ሲያዝ፤ ቀሪው ሲሞትና ሲቆስል ጦርነት ቀልድ አለመሆኑን ልብ ያለው ያኔ ይረዳል። ለምንድን ነው የትግራይ ልጆች ዛሬም በወያኔ ግፊት የሚሰውት? እኔ እነርሱን ቢያረገኝ በምንም ሂሳብ ለትግራይ ለገለ መሌ ብዬ አልሞትም። ማምለጫ መንገድን እፈልጋለሁ እንጂ። የአዲስ አበባው መንግስት አሁን ሃገርህ ተደፍራ እንዲህና እንዲያ ሆነህ ሲል ግርም ይለኛል። ትላንት ወያኔና ሻቢያ እያስታጠቁ ለ 30 ዓመት ያጋደሉን አይደል እንዴ አሁን በፈጠራ ዜናና የትግራይ ህዝብ አለቀ በማለት ውሸትን የሚያናፍሱት? እውነቱማ ጦርነቱን የጀመረው ወያኔ “መብረቃዊ” በሆነ መንገድ ሰዎች በተኙበት ነበር። ግን መብረቁ ለሁሉም ተረፈና አሁን እንሆ እንተራረዳለን። የሃገር ነጻነት እንዲህ ከሆነ ባፍንጫዬ ይውጣ።
  30 ዓመት ሙሉ ሻቢያ የኤርትራን ነጻነት ፍለጋ ተፋልሞ አሁን አፍሪቃዊቱ ሰሜን ኮሪያ መሆኗ የአፍሪቃን የፓለቲካ ቆሻሻነት አጉልቶ ያሳያል። ትላንት ጎረቤት ሃገሮች እንዲገነጠሉ ሲረድ የነበሩ ሃገራት ዛሬ የራሳቸውንም ሃገር ቆርሰው አስረክበዋል። የደ/ሱዳንና የሱማሊያ ለሁለት መገንጠል ለዚህ ምሳሌ ነው። አፍሪቃ የገንጣይ ገንጣይ ያስገንጣይ ተገንጣይ በውጭ ሃይሎች እየተረዳ የሚጨፍርበት አህጉር ነው። ወያኔና ሻቢያም የዚሁ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው። ለዚህ ነው ፓለቲካ ቤት የሌላቸው ውሾች ለመኖር የሚያደርጉት የመነካከስ ውጤት ነው የምለው። ህዝብ የመነገጃ ጆኒያ እንጂ ለውጥ አግኝቶ አያውቅም። ደርግ መጣ ወያኔ ገባ፤ አብይ ተተካ የጊዜው የፓለቲካ ነፋስ እንጂ በፍትህ እጦትና በችጋር ለሚጠበሰው ሰፊ ህዝብ እፎይታ ለግሶት አያውቅም። ዛሬ በትግራይ ክፍለ ሃገርና በአጎራባች ስፍራዎች የምናየው እብደትም የዚሁ ዘመን የሸፍጥ ፓለቲካ ውጤት ነው።
  ስለሆነም አይኑን ተሸፍኖ መሳሪያ ጭንቅላቱ ላይ የተደገነበትን ህዝብ ንቃ፤ ተነስ ማለት ማፌዝ ነው። የትግራይ ህዝብ ሙሉ ነጻነትና ምርጫ ቢኖረው ወያኔን አንድ ቀን በህይወት እንዲኖር አይፈቅድለትም። ግን በአንድ ለአምስት ተመድቦ በወያኔ የስለላ መረብ የታፈነን ህዝብ እንዴት ነው ከወያኔ ጋር የሚፋታው? ለዚህ ብልሃት ካለህ አስታውቀን። ልክ አንድ ጸሃፊ ከረጅም ጊዜ በፊት እንዳሉት የሃበሻው ታሪክ መደምደሚያ የለውም። “ሲገሉ፤ ሲገዳደሉ ይኖራሉ” እንጂ። በቃኝ!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.