አሜኬላ በመንቀል ስም ዕንክርዳድ እንዳይቀር ይተኮር ”  – ማላጂ

abiy

“አለባብሰዉ ቢያርሱ ባረም ይመለሱ ” የሚለዉ የአገራችን  እና ህዝቧጥንተ  ብሂል ለአገራችን ከትናንት አስከዛሬ ለደረሰባት እና እያስተናገደች ላለዉ መጠነ ሰፊ መከራ መንስዔ እና ሁነት ዓይነተኛ መማሪያ ነዉ ፡፡
የዘንድሮዉን ትተን ያምና ታቻምነዉን ብናይ  በአገራችን አሁን ላይ የሚታየዉ የሞት ሽረት የኅልዉና እና አገር አድን ትግል ከቅድመ ኢ.ኃ.አ.ዴ.ግ ወደ ስልጣን በፊት በተደጋጋሚ እና በማያወለዳ ቋንቋ እና ስያሜ ተገልፆ  እንደነበር እና ብዙ መስዋዕት  ስለመከፈሉ ለማንም ኢትዮጵያዊ በዘመንም ሆነ በታሪክ የቅርብ ክስተት ነዉ ፡፡

በወቅቱ ከነበረ ዕዉነተኛ የአገር አንድነትን ለማስጠበቅ እና ለመታደግ ከነበረ ቁርጠኝነት የተነሳ ስለ ተካሄደዉ ብሄራዊ ትግል እና የአፍራሽ ኃይሎች ስያሜ ፣ የአጭር፣ መካከለኛ እና የረጅም ጊዜ ግብ የኢትዮጵያን እና ህዝቧን ታሪክ በማዛባት አገር የማፍረስ እና የመጨረሻ ግብ ብለዉ የተነሱበትን የተለያዩ በራሳቸዉ ምናብ ያለሙትን ትናንሽ አገር የመፍጠር እንደነበር ጠቅላላ የጥፋት ኃይሎች ድምር የተረጋገጠ ነበር ዛሬ ዳግም ዋጋ እያስከፈለ ነዉ ፡፡

አዚህ ላይ የሁላችን ድካም ፍሬ አልባ እንዳይሆን በሚደረግ ብሄራዊ ርብርብ ካለፉት እና በእኛ ዘመን ከሚታዩ ችግሮች መማር ያለብን ይመስላል ፡፡

ለዚህም ቀድሞ የኢትዮጵያ መንግስት (ከኢሀዴግ በፊት) አገር ለመከፋፈል የዛሬዎቹ ከፋፋይ እና ገንጣዮችን  በትክክለኛ ስማቸዉ “ከሃዲዎች እና የናት ጡት ነካሽ”  በማለት ምግባር እና ተግባርን አካታች ወቅታዊ እና ትክክለኛ  መሆኑ የችግሩን ይዘት እና ዉጤት  ሊያስከትል  ከሚችለዉ  ብሄራዊ እና ቀጠናዊ  ቀዉስ ገላጭ ከመሆኑ በተጨማሪ ዕዉነተኛ ስለመሆኑ ለዛሬ ሌላ የመከራ ዉርስ ደርሷል፡፡

ስለዚህም አሁንም ያለፉትን የ8 ወራት ማለባበስ  ይህም ችግሩን የማሳነስ፣ ድንገተኛ የማድረግ፣ ስያሜ፣ የማይገባ ሀተታት( ህፃናት፣ሴት፣ አሩግ……ወዘተ ) ወጥተን  የምንገኘዉ የአገር እና ህልዉና ጉዳይ እንደመሆኑ  ራስን በመከላከል ጦርነት ዕዊነተኛዉን ልክ እና መልክ ማስያዝ ይጠበቃል ፡፡

በህዘብ ፊት አሸባሪ ፣ጠበጫሪ  እና አገር የማፍረስ ተልዕኮ የያዘን እና በህግ በአገር ክህደት እና በጦር ወንጀል ሊፈረጅ የሚገባን አካል በተለያዩ መገናኛ(የአገር ዉስጥ) ይጨምራል በሁለት አቻ ህጋዊ አካላት አድርጎ የማቅረብ አዝማሚያ በራሱ የህዝቡን የህልዉና ትግል ግለት የሚያመክን ነዉና መንግስት እና ህዝብ በመሃል ሰፋሪ አድር ባይ ቀለማጆች ላይ ቁርጠኛ እርምጃ ሊወስዱ ይገባል፡፡

በግንባር ከሚደረግ ትግል በላቀ ህዝባዊ ትግሉን የሚጎደዉ የትግሉን ስያሜ ፣ አካሄድ እና ዓለማ  ለማሳት በሚቀዣብሩት መሆኑን ልብ ሊባል ይገባል ፡፡ ለምሳሌ በህግ አሻባሪ ከተባለ ….የአሸባሪ መሪ፣ አባል…. ከማለት ፋንታ ጉራማይሌ ቧልት / ፕሮፖጋንዳ የሚያራምዱ አካላት ዐቋማቸዉን በግልፅ ሊያሳቁ ይገባል፡፡

ይህ ሲሆን ሁሉም የችግሩን ምንነት በመረዳት ለጋራ ችግር የጋራ መፍትሄ ለማስገኘት ያስችላል ፡፡

በአገር ላይ የጥፋት እና የመለያየት ሴራ ይዞ ከጠላት ጋር በማበር ለሚኳትኑት የክህደት እና የሞት አረም ለማስወገድ በሚደረገዉ የመመንጠር ስራ ፍሬዉን  ከገለባ ለመለየት ዕንክርዳዱን ካሜከላዉ ሳይለይ ለዘላቂ ዕድገት እና አንድነት መሰረት ነዉ ፡፡

ገለባ ከምርት ለመለየት በሚደረግ  ህዝባዊ ትግል  የአሸባሪ እና የክህደት ደቀመዝሙር ብቻ ሳይሆን ተባባሪ እና መሰሪ ተልዕኮ ይዞ በመንታ ባላ የሚረግጠዉንም ፋንታ አለመስጠት የሀገሪቷን እና ህዝቦች መከራ ዘመን ለማሳጠር የሚያስችል  ይሆናል ፡፡

በጦርነቱ ሚዛናዊነት ስለመሆን የአዞ ዕንባ የሚያነቡ  የዉስጥ ምንደኞችን በቃ ማለት ያስፈልጋል ፡፡

“ፍትህ ከክርስቶስ እንጅ  ከዓለም እና ጦርነት ፍትህ የለም ፡፡” ስለ ጠላት አሰላለፍ  አቅም ፣ ሠባዊነት …ማለት ጊዜ ማጥፋት ነዉ ወዶ እና ለምዶ የገባን ጠላት ማሳነስ እና ማለባበስ መቆም አለበት ፡፡

በችግር ጊዜ ወዳጅ ይሸሻል ፤ በድል ጊዜ ዓለም  ከጀግኖች ጋር ይሆናል ፡፡

አንድነት ኃይል ነዉ

ማላጂ

 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.