የመከላከያ ሠራዊት፣ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ እና የአማራ ሕዝባዊ ሠራዊት በአውደ ዉጊያ ዉሎው ጠላትን እያንበረከከ ወደፊት እየገሰገሰ ነው

መሆኑን የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት አስታወቀ

222973190 359926442310998 307957990353304141 nባሕር ዳር፡ ሐምሌ 19/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ግዛቸው ሙሉነህ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት፣ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ እና የአማራ ሕዝባዊ ሠራዊት በአውደ ዉጊያ ዉሎው ጠላትን እያንበረከከ ወደፊት እየገሰገሰ መሆኑን አስታወቁ።

ዋና ዳይሬክተሩ በቅጥረኛ የትህነግ ተቀጣሪ አክቲቪስቶች በሀሰት እንደሚነዛው መረጃ ሳይሆን በማይጠብሪ፣ በዋግ በአበርገሌ አከባቢ፣ በራያ በአላማጣ አከባቢ እየተደረገ ባለው አሸባሪውን የማፅዳት ዘመቻ ደማቅ ታሪካዊ ድል እየተገኘ ነው ብለዋል። በትህነግ አስገዳጅነት ሳያምንበት ሊወጋን የመጣው የትህነግ ኃይል ለመቁጠር በሚያስቸግር ሁኔት እንዳልነበር ሆኖ ተደምስሷል ነው ያሉት።
አቶ ግዛቸው እንዳሉት የቀረው ኃይልም ከያለበት ምሽግ እየተደመሰሰ ይገኛል፤ ዉጊያ የተደረገባቸው አከባቢዎችም በቁጥጥር ሥራ እየሆኑ ተቆርጠው የቀሩ አካላት ከያሉበት እየተለቀሙ የማፅዳት ሥራ በከፍተኛ የሕዝብ ሞራል ታግዞ እየተከናወነ ይገኛል ነው ያሉት።
የክልሉ መንግሥት ያቀረበው የክተት ጥሪን ተከትሎም በአስገራሚ ሁኔታ አሸባሪውን ትህነግ እስከመጨረሻው ላይመለስ ለመሸኘት ከሁሉም የክልሉ አከባቢና ከክልሉ ውጭም ያሉ አካላዊ ሁኔታቸው ለዉጊያ ብቁ የሆኑ ሁሉ ትግሉን በስፋት እየተቀላቀሉና እየተደራጁ እንደሚገኙም አስታውቀዋል።
ለመላ ኢትዮጵያዊያንና ለክልላችን ካንሰር የሆነውን የትህነግን ቡድን ነቅሎ ለመጣል የሚደረገው ትግልም አሁን ያለውን ሁኔታ ከአሰብነው በአጠረ ጊዜ ግብአተ መሬቱን ለመፈፀም የሚያስችል እንደሆነ የታጋዩና የሕዝባችን እንቅስቃሴ ተጨባጭ ማስረጃዎች ናቸው ብለዋል።
የትህነግ ቡድን በውሸት ፕሮፓጋንዳ ከሀገር ውስጥ እስከ ውጭ ማኅበረሰቡን ለማደናገር ይሄን ቦታ ይዣለሁ እያለ ሊያናግር ቢሞክርም ሕዝቡ ፕሮፓጋንዳው የተነቃበት ያረጄ ያፈጄ መሆኑን በግልጽ ተረድቷል ነው ያሉት፡፡
ትህነግ አከርካሪውን እየተመታ እየሸሸ መሆኑንም አረጋግጠዋል፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.