አሸባሪው ትህነግ ከጥቅምት 24/2013 ዓ/ም ጀምሮ የፈፀማቸው ዋና ዋና ወንጀሎች! – ጌታቸው ሽፈራው

debre1 አሸባሪው ትህነግ ከጥቅምት 24/2013 ዓ/ም ጀምሮ የፈፀማቸው ዋና ዋና ወንጀሎች!   ጌታቸው ሽፈራው

1) ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በሰሜን ዕዝ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሠራዊት ላይ ጥቃት በመክፈት በመከላከያ ሰራዊት ወታደራዊ እና ኢትዮጵያ አሉኝ በምትላቸው የመከላከያ ቁሳቁሶች ላይ ከፍተኛ ውድመት አድርሷል። የሰራዊቱ አባላትን በብሔር ለይቶ ረሽኗል። እጅግ ሰጥቃጭ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ፈፅሟል።
2) ጥቅምት 28 እና 29/2012 ዓ.ም በማይካድራ በመንግስት ሪፖርት መሰረት ከ700 በላይ የሚሆኑ፣ ከአካባቢው በተገኙ ምንጮች ደግሞ ከ1600 የማያንሱ የወልቃይት የአማራ ላይ ማንነትን መሰረት ያደረገ ጭፍጨፋ ፈፅሟል።
3) ህዳር 4/2013 ዓ.ም ወደ ኤርትራ ፣ በተመሳሳይ ህዳር 3/2013 ዓ.ም ወደ አማራ ክልል ባህርዳር እና ጎንደር ሮኬቶችን ተኩሷል፡፡ ሕዝብን አሸብሯል።
4) ግምቱ በዉል ባልታወቀ የኢትዮ ቴሌኮም የንብረት ዝርፊያ፣ የገቢ ኪሳራ እና በስራ ላይ የነበሩ የጥበቃ ሰራተኛ ግድያ እና አፈና ተፈፅሞል፡፡
5) የአክሱም ኤርፖርትን በህዳር 14 ቀን 2013 ዓ.ም ሙሉ ለሙሉ አውድሟል፡፡
6) በህዳር 08/2013ዓ.ም በሁመራ ከተማ የሚኖሩ የወልቃይት ጠገዴ አማራ ተወላጆች ባለሀብቶች የአማራ ማንነት ትደግፋላችሁ በሚል ከሁመራ ከተማ አፍኖ በመዉሰድ እድሪስ በተባለ አካባቢ በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሎ ጫካ ላይ ጥሏቸዋል።
7) በ17/10/201ዓ›ም የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ሀላፊ እምብዛ ታደሰ ከመቀሌ ከተማ አፍኖ በመው ሰድ አይደር በሚባል አካባቢ በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለው አካሉን ቆራርጠው ጥለውታል።
8/ ህዳር 7/2013 ዓ.ም 4 ዋና ድልድዮችን አፍርሷል።
9) ጥር 1/2013 በህፀታ ካምኘ የሚገኙ 300 ስደተኞች ገድሏል።
10) የአለም አቀፉ ቀውስ ኮሚቴ IRC ታህሳስ 2/2013 እንደገለፀው አንድ(1) የቡድኑ አባል መገደሉን፣ ዳንሻ የስደተኞች ምክር ቤት (DRC) ደግሞ ታህሳስ 3/2013 2 አባላቱ መገደላቸውን፣ሰኔ 17 እና 18 አካባቢ 3 MSF ወይም የድንበር ተሻጋሪ ሐኪሞች አባላት መገደላቸው ገልፆአል። የእርዳታ ሰራተኞቹ የተገደሉት በትህነግ ቡድን ነው።
11) የካቲት 10/2013 በታጠቁ የትህነግ አባላት በፈፀሙት ጥቃት አዲ መሲኖ በተባለ አካባቢ በአውቶቡስ የተሳፈሩ መንገደኞች ላይ በተከፈተ ተኩስ 6 ሲሞቱ 10 ቆስለዋል።
12) መሰረታዊ የአገልግሎት አዉታሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እና ዝርፊያ ተካሂዷል።የመብራት አገልግሎት ማቋረጥ፣ የባንክ ዘረፋ ማካሄድ፤ ለተረጅዎች የሚላኩ የሰብዓዊ እርዳታን ዘርፏል።
13) የካቲት 12/2013 የትግራይ ተወላጅ የማነ ንጉሴ በሔዋነ አካባቢ ተገድሏል
14) ትህነግ በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ ጥቃት ከፈፀመ ቀን ጀመሮ ትህነግ በጀመረው ጦርነት ምክንያት በሴቶች እና በልጃገረዶች ላይ የሚፈፀመዉና የሚደርሰዉ ወሲባዊ ጥቃትና የአስገድዶ መድፈር ተፈፅሟል። በርካታ ዜጎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል።
15) በሃይቅ መስሐል 19 ሰዎች አፍኖ በመውሰድ ከሁለት ሳምንት በኋላ ከእያንዳንዳቸው 26 ሺህ ብር ተቀብሎ ለቋቸዋል። ትህነግ መጀመርያ ከየአንዳንዳቸው መቶ ሺህ ብር የተጠየቀ ቢሆንም የለንም ስላሉ ነው በድርድር በነፍስ ወከፍ 26 በር ተቀብሎ ለቋቸዋል።
16) ከአክሱም ትንሽ ወጣ ብላ የምትገኝ ውቅሮ ማራይ በምትባል ከተማ ህዝብ አገልግሎች እንዲያገኝ ተብሎ የተሾሙትን ሁለት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ሹመኞች ገድሏቸዋል።
17) ከመቀሌ 25 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ምትገኘው አጉላዕ ከተማ አስተዳደር አፍኖ ወስዷል።
18/ በመንግስት ሪፖርት መሰረት ከ20 በላይ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አባላትን ገድሏል፣ ከ20 በላይ የሚሆኑ የጊዜያዊ አስተዳደሩ አባላት አግቷል። 4 የአስተዳደሩ አባላት ጉዳት ደርሶባቸዋል።
19) ትህነግ ትግራይ ላይ የፈፀመውን አይነት ጥቃት የቅማንት ኮሚቴ ሽብር ቡድን ጭልጋ ላይ በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ እንዲፈፅም አድርጓል። ይህ አሸባሪ ቡድን ግን ጥቃት እየፈፀመ ያለው በመከላከያና በአማራ ልዩ ሃይል ብቻ ሳይሆን የቅማንት ህዝብም እያሰቃየ ይገኛል። በግዳጅ በወገንህ ላይ ካልዘመትክ እያለ ሰላማዊውን ቅማንት ገበሬ መከላከያና በአማራ ልዩ ሃይል ላይ ጦርነት ክፈቱ እያለ ሲያሰቃይ ከርሟል።
#

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.