የ “ሙሴዎች” ተከታይ ዘልዛላ ምሁራንና የሜክ ዶናልድ ህፃን የንግድ ማስታወቂያ!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

የበፊቱም ሆነ የአሁኑ ይህ አድግ አንዴ “የዓባይ ግድብ” ሌላ ጊዜ “ኢትጵያ ሱሴ”ን ምሁራንን እየሰበኩ እንዳልሰከነች ኮበሌ እንዴት እንደሚያማልሉና እንደሚያሽኮረምሙ ለመረዳት ይኸንን የሜክዶናልድ ንግድ ማስታወቂያ ይመልከቱ፡፡ https://www.youtube.com/watch?v=s8AV4asnO9s በዚህ ማስታወቂያ አንድ ህፃን የሚክዶናልድ አርማ ሲቀርበው ይስቃል፡ ሲርቀው ደሞ ያለቅሳል፡፡ ብዙው የኢትዮጵያ ምሁርም በቀጣፊዎችና አታላዮች ስብከት እንደ ባህር ላይ ኩበት እየተንሳፈፈ በካድሬዎች የጩኸት ነፋስ ሲነዳ ይውላል፡፡ ምሁር እንደ ገለባ ሥርና አቋም አልባ በመሆን እንኳን ተልጅ ተዶሮም አንሶ እንዴት ተሰላሳ ዓመታት በላይ ይታለላል?

ስለመታለል ቅዱሱ መጽሐፍ ሲያስተምር ዘፍ፡፫፡፩ እባብም ከምድር አውሬ ሁሉ ተንኮለኛ ነበረይላል፡፡ ወረድ ብሎም እባብ ሔዋንን አታሎ የተከለከለውን ፍሬ እንዳስበላት፤ አዳምንም እንድታሳስት እንደመከራት ያስተምራል፡፡ ከምድር አውሬዎች ሁሉ እባብ ተንኮለኛ የነበረውን ያህል ለገሰ ዜናዊ በምድር ካሉ ሰዎች ሁሉ ተንኮለኛ ነበረ፡፡ እባብ አዳምና ሔዋንን በበለስ ፍሬ እንዳታለለው ለገሰ አማራ የጭቁን ሕዝቦች ጠላትበሚባል የደደቢት ዕፀ በለስ በአማራ ያቄሙትን ምዕራባውያንንና ትሉል ጭቁን ብሔረሰቦችንአታሎ በአማራ አዘመታቸው፡፡

abiy ugly
abiy ugly

ማታለሉ የተሳካለት ለገሰ ምዕራባውያንን ከጀርባው የጭቁን ብሔረሰቦችወኪሎችከፊት አሰልፎ አማራን ሕገ መንግስት ተመንደፍ፣ ከቤተመንግስት፣ ከወታደራዊና ደህንነት መዋቅር፣ ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴርና ሌሎችም ቁልፍ ቦታዎች አገለለው፡፡ ሐብቱንና ቅርሱን ዘረፈው፡፡ ከአርባ ሶስት ዓመታት በፊት በወልቃይት የጀመረውን የአማራ ፍጅትና ሥቃይ በመላ አገሪቱ አስፋፋው፡፡ አማራ በበደኖ ገደል እንዲወረወር ሁኔታዎችን በማመቻቸት የልጅ አባታቸው ከነነፍሳቸው ገደል ተጥለው፤ ከሃምሳ በላይ ታጣቂዎች በየተራ ደፍረዋቸው የአባለዘር በሽታ መግል እንደ ጅረት ከማህፀናቸው የፈሰሳቸው የአስራ ሶስት ልጆች እናት እንዳይ፤ ሌሎችም ብዙ ገና አደባባይ ያልወጡ ግፎች ሲፈፀሙ እንዲመለከቱ አደረገ፡፡

ገደል ከመወርወርና እንደ ወልቃይት አማሮች ጉድጓድ ውስጥ ከመሰቃዬት የተረፉት በቤታቸው እንዲመክኑ፣ በወህኒ ቤተ እንዲኮላሹ፣ እንዲጠበሱ፣ እንዲቀቀሉና እንጨት እንዲሰደድባቸው ተደረጉ፡፡ የተቀሩትም ሥራና ንብረት የማፍራት ዕድል እንዲነፈጉ፤ ያያቶቸው ደም ከፈሰበት ምድር እንዲፈናቀሉ፤ ባህር አቋርጠው እንዲሰደዱ፤ ሲሰደዱም በማዕበል እንዲሰምጡ፣ በአረምኔዎች እንዲታረዱ፣ ለአረቦች ተሸጠው ባርያ እንዲሆኑ ተደረጉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  በረሃ ላይ ያለው እውነት | መስቀሉ አየለ

በዚህ መልክ አማራን ያሰቃየው የለገሰ ቡድን በ፲፱የ፺ ዓ. ም ከኢትዮጵያ በዘረፉት የባንክ ገነዘብ፣ ጤፍና ቡና ከሻቢያ አምበሎች ተጣልቶ ጦርነት ሲፈጥር ሉአላዊነትየምትባል የዕፀ በለስ ፍሬ ይዞ ብቅ አለ፡፡ በዚች ዕፀ በለስ ምራቃቸው የተዝረበረበ ምሁራንየሰፈር ልጆቹን አሳጪዶ የአገሪቱን የባህር መተንፈሻ አፍንጫ የቆረጠና አማራን ገደል ያስወረወረ ቡድን እንዴት የሉአላዊነት ዕፀ በለስ ይዞ እንደ እባብ ተሳበ?” ብለው አልጠየቁም፡፡ ይልቁንም ጥቂቶቹ በሆዳቸው ብዙዎቹም በየዋህነት እንደ ሔዋን ተታለው የሉአላዊነቷን ዕፀ በለስ እንደ አምባሻ ገመጡና የእነ ለገሰ ካድሬዎች ሆነው ቁጭ አሉ፡፡ በካድሬነታቸውም ጀንዲ በሚያካክል የሉአላዊነት ጥሑፍ ሕዝብን እንደ አዳም አሳስተው ሰባ ሺ ወጣቶች በደኖና ሽራሮ እንደ ሙጃ አስጨረገዱ፡፡ አንድ በሉ፡፡

በበባድሜና ሽራሮ ሰባ ሺ ወጣቶችን እንደ ሙጃ ያስጨረገደው የለገሰ ቡድን ሕዝቡን በሉአላዊነትዕፀ በለስ አታሎ በጤፍና በቡና ዘረፋው ጦርነት ከጎኑ ማሰለፉ የልብ ልብ ሰጠውና በ፲፱የ፺፯ ዓ.. “ነፃ ምርጫየምትል ዕፀ በለስ እንቁልልጪእያለ አሳይቶ ስንቱን ምሁር የቅቤ ሽሮ እንደሸተተው ርሃብተኛ አስጎመጀው፡፡ ስንቱን ፖለቲከኛ በአዲስ ፉንቃ መብላት መጠጣት እንደተሳነው ኮበሌ አነሆለለው፡፡ ይኸንን በነፃ ምርጫዕፀ በለሰ የነሆለለ ፖለቲከኛም ድምፅ የተነፈገው የለገሰ ቡድን በለመደው ጭካኔ ከርቸሌ አጎረው፤ ድምፁ በመቀማቱ የተቆጣውን ሕዝብም አሳጨደው፡፡ መቶ ሺዎችን አሰራቸው፤ ወጣቶችን ካምፕ አጉሮ በደረቅ ምላጪ ላጫቸው፡፡ ይህንን በብራና የተጣፈ ዘግናኝ ታሪክ ከአምስት ዓመታት በኋላ ለገሰ ህዳሴየምትባል የዕፀ በለሰ ፍሬ ምሁራንን እንደ አምባሻ አስገምጦ ከአእምሯቸው አስፋቀና ከጀርባው አሰለፋቸው፡፡ ለገሰና ቡዱኑ ህዳሴ፣ ዓባይ ግድብ፣ ኩልኩልብለው አቀንቅነው አው ኩኩ ኡኡኡኡኡ..” ብለው ሲጮኹ ሕዝብ በነለገሰ ሲጨፈጨፍ ዲዳ የነበሩት ምሁራን ሳይቀር ክንፋቸውን አራግፈው ..ኡው..ኡኡኡሲሉ አስተጋቡ፡፡ ወዲያውም ህዳሴዓባይግድብ ዓባይ .. የሕዝብ ጉዳይ! ያገር ጉዳይእያሉ ተጠቅሎ በማያልቅ ጥሑፍ ስንቱን አታለው ገንዘቡን በቦንድ አስመዘበሩ፡፡ ሁለት በሉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የ ኢትዮጵያ ዋና ዋና ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው-  በ ዘውዱ ገብረ ሕይወት

በቦንድ ገንዘብ የራሱን የንግድ ድርጅት እንደሚያደልብ፣ ልጆቹን ውጪ እንደሚያስተምር፣ ሰርጉን እንደሚደግስ የሚታወቀው ይህ የለገሰ ቡድን ህዳሴው ከተዘመረ ከአምስት ዓመታት በኃላ ግፍ የበዛበት ወጣት የመኖር ዋስትና ሲጠይቀው በጎንደር፣ በጎጃም፣ በሸዋ፣ በወለጋ፣ በአሩሲ፣ በጋምቤላ፣ በኮንሶ፣ በኦጋዴንና ሌሎችም ቦታዎች ረሸነው፤ ወህኒ አጎረው፤ የሜድትራንያንና የቀይ ባህር ቀለብ አደረገው፡፡

የለገሰ የይህ አድግ ቡድን ግፍና መከራ አፍንጫቸው የደረሰና ትዕግስታቸው የተሟጠጠ ወጣቶች አመጡ፡፡ ለመከራ አሳልፈው በሰጧቸው አባቶቻቸው አፍረው የያቶቻቸውን ታሪክ ለመድገም የወሰኑ ቆፍጣና ወጣቶች እንደ አንበሳ አገሱ፡፡ እንደ አያቶቻቸው በውስጥም በውጪም ተከብረው ለመኖር መሰባሰብና መታገል ጀመሩ፡፡ ይህቺን ቁርጠኝነት የተመለከተው የምዕራቡ አለም እሽኮኮ ተሸክሞ ቤተመንግስት የከተተውን የትግሬ ነፃ አውጪ አወረደና ለገሰ በቋንቋ ፖለቲካና በአማራ ጥላቻ እያጠመቀ ያሳደገውን ሌላውን ቡድን የይህ አድግ ማፈያ አምበል አርጎ ሸመው፡፡ አዲሱ የይህ አድግ አምበል የአማራ ምሁራንን እንደ ሜክዶናልዱ ልጅ የሚያማልለውን ስለሚያውቅ “ኢትዮጵያ ሱስ ናት፤ ስንሞት ኢትዮጵያውያን ስንኖርም ኢትዮጵያውያን” እያለ ትምህርት፣ እድሜ፣ ቅስና፣ ጵጵስና ሼህነት ያለበሰለውን ጮርቃና ዘልዛላ ሁሉ ከንፈሩን ጥሎ እንቲያዳምጠውና ጨርቄን ማቄን ሳይል እንዲከተለው አደረገ፡፡ አብዛኛው ምሁር አዲሶቹን የይህ አድግ አምበሎች ተከተሎ ኩኩ አው..ኡ ኡ ወንዝ አሻጋሪው ሙሴ መጣ! ፈንድ! ፈንድ ! ፈንድ እንፈንደድለትሲል ጮኸ፡፡ ሶስት በሉ፡፡

አዲሶቹ የይህ አድግ አምበሎች ተወንበር እንደተዘፈዘፉ በቡራዩ በጋሞች በለገጣፎና በሱሉልታ ደግሞ በአማራዎች ላይ የዘር ማጥዳት ዘመቻ ተኪያሄደ። ትንሽ ቆየት ብሎም በአሩሲ፣ በባሌ፣ በሻሸመኔ፣ በሃረርጌና ሌሎችም ቦታዎች ነፍጠኛ ውጣ እየተባለ በገጀራ ተጨፈጨፈ፡፡ ህልቆ መሳፍርት የሌላቸው አስመሳይ ምሁራን የዘር ፍጅቱን ክደው ዝም አሉ፡፡ ሙሴአቸው የሬሳ ዘር እየቆጠረ አብዛኛው የሞተው አማራ ሳይሆን ሌላው ዘር እንደሆነ አስመስሎ ሲቀጥፍ ተከታዮቹ ምሁራን አሁንም እንዳውራ ዶሮ ክንፋቸውን አራግፈው “ኩኩ አው ኡኡ. ትክክል ነው የዘር ፍጅት ተፈጥሟል ማለት አገር ያፈርሳል” ብለው እየዋሹ በተጨረገዱት አማራዎች ቀለዱ፡፡ አራት በሉ!

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከምክክር ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ

አሁንም ሙሴዎቻቸው “ የኢትዮጵያ ሕዝብ የማስታወስ ችሎታው አጭር ነው” እያሉ በሾርኒ ለምሁራን ተብዮዎች እየተናገሩ በመተከል፣ በወለጋና በሸዋ አማራን በግድየለሽነት አስጨፈጨፉ፡፡ የሙሴዎች ተከታዮች ምሁራን አሁንም የአማራን ዘር ፍጅት በዝምታ አለፉ፡፡ አንዳንድ አረመኔዎች እንዲያውም የአማራ ዘር ፍጅት አልተፈጠመም አያሉ ባለቁት ህፃናትና እናቶች አፅም ተሳለቁ፡፡ ሙሴዎቻቸው አሁንም ጨፍጫፊዎችን አሰርን በሽብርተኝነትም ፈረጅን ምርጫም ልናኪያሂድ ነው ብለው ሲያጃጅሏቸው እንደተለመደው “ኩኩ አው ኡኡ!” ብለው “ሙሴዎቻችን ሺ ዓመት ንገሱልን” ብለው እንደ ቄብ ዶሮ በማከታተል አስካኩ፡፡ አምስት በሉ፡፡

ሞሴዎቻቸው ተድሮ ጌቶቻቸው ጋር በስልጣን ተጣልተው ወታደሩንና ሕዝብን ሲያፋጁ ጦርነቱ የኢትዮጵያን አንድነት ለማስጠበቅ የተደረገ አስመስለውና ተሙሴዎቻቸው ጀርባ ተሰልፈው “ለኢትዮጵያ ትንሳዔ የሚታገል መንግስት ይህ ነው!” አየሉ የስንዴ ዘር ፈጅቶ እንደጠገበ አውራ ዶሮ አንገታቸውን አቅንተው አስካኩ፡፡ ስድስት በሉ፡፡

ሙሴአቸው በምዕራባውያን ቀጪን ትዕዛዝ የጀመረውን ጦርነት እንዲያቆም ሲታዘዝና ለቆ ሲወጣ እነዚህ ዘልዛላ ምሁራን ባቄላ እንዳነቀው ዶሮ ጪጭ አሉ፡፡ ወዲያው ደሞ ማታለል የማይሰለቻቸው ሙሴዎች “ዓባይን እየሞላን ነው” ብለው የክድረምት ጎርፍ ወይም ድቡቅ ሲያሳዪአቸው “ዓባይ ዓባይ ያገር ሲሳይ” እያሉ በአጭር “ሚሞሪ” አስካኩ፡፡ ሰባት በሉ፡፡

ባህር ያሻግራሉ የተባሉት ሙሴዎች ጅረት እንኳን ሳያሻግሩ ራያንና ኮረምን ጥለው እንደ ሚዳቋ ዘለሉ፡፡ እነዚህ እንደ ሚዳቋ የዘለሉ ነገ ደግሞ የድምፅ ማጉያቸውን ይዘው “ስንኖር ኢትዮጵያ ስንሞትም ኢትዮጵያ፣ የዓባይ ግድብ፣ ኢትዮጵያችን” እያሉ ቢመጡ እነዚሁ ምሁራን “ኩኩ አው ኡኡ!” ብለው “ሙሴዎቻችን” ማለቱን ይቀጥላሉ፡፡

ቀጣፊ ሙሴዎች ዓባይ ግድብንና ኢትዮያ ሱሴን እየወሸከቱና በሩቁ እያሳዩ፤ ዘልዛላና አድር ባይ ምሁራንም እንደ ሜክዶናልዱ ህፃን አንዴ እንደ ድብ ዝም ሲሉ ሌላ ጊዜ እንደ ዶሮ ሲያስካኩ ድራማው እንደቀጠለ ነው፡፡ የሙሴዎች የማጭበርበር የንግድ ማስታወቂያና የሙሴዎችን የማታለያ ማስታወቂያ እየሰሙ የሚያስካኩት ዘልዛላና አድር ባይ ምሁራን ትያትር የሚቋጨው መቼ ነው? እግዚኦ እንኳንም ሞት አለ!

መጀመርያ ነሐሴ ሁለት ሺ ዘጠኝ ዓ.. እንደገና ሐምሌ ሁለት ሺ አስራ ሶስት ዓ..

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.