/

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መግለጫ

203123828 5985022758204582 1355415271320847765 n
203123828 5985022758204582 1355415271320847765 n

ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ከ 2 ጣቢያዎች ውጪ በአብዛኛው በሰላማዊ ሁኔታ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገልጿል።

በሲዳማና በጋምቤላ ክልሎች የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ እንደቀጠለና ተጠናቅቆ ወደ ድምፅ ቆጠራ እንደሚገባ ተገለጿል።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ 2 የምርጫ ጣቢያዎች የኮድ ስዕተቶች በማጋጠሙ የቦርዱን ውሳኔ ስለሚፈልግ ለውሳኔ ተለይቶ ተቀምጧል።
በደቡብ ክልልም በአብዛኛው የድምፅ አሰጣጡ ሂደት ተጠናቅቆ ወደ ድምፅ ቆጠራ ተገብቷል።
የድምፅ ቆጠራ በተደረገባቸው ጣቢያዎች ጊዜያዊ ውጤት ይፋ እየተደረገ መሆኑን እና የማዳመሩ ስራ በየምርጫ ክልሉ ከተጠናቀቀ በኋላ ለማረጋገጥ ወደ ቦርዱ ገቢ ይደረጋል ሲሉ የ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ኮሚውኒኬሽን ጉዳዩች አማካሪ ሶሊያና ሽመልስ ገለፀዋል።
የምርጫ ውጤቱን በተመለከተ ከቦርዱ ውጪ ማንም አካል የመጨረሻውን ውጤት የማሳወቅ ፍቃድ ስለሌለው በተለያዩ መንገድ እከሌ አሽንፏል እያሉ ያልተረጋገጠ መረጃ ማሰራጨት በቦርዱ ተቀባይነት እንደሌለው ተነግሯል።
በምርጫ ጣቢያ በ 200 ሜትር ክልል ውስጥ አጋጥሞ የነበረ የፀጥታ ችግር ካለ በሚል ለቀረበው ጥያቄ ፡ ምንም አይነት የፀጥታ ችግር አለማጋጠሙን ወ/ት ሶሊያና ሺመልስ ገልፀዋል ።
በተጨማሪም አንድ የካርተር ማዕከል አባል በሆቴል ክፍላቸው ውስጥ ሕይወታቸው ማለፉን ተከትሎ ከምርጫው ጋር ይገናኝ እንደሆነ በሚል ለቀረበው ጥያቄ ፡ ግለሰቡ በጤና ችግር ሕይወታቸው ማለፉን ከፖሊስ የተገኘ መረጃ ያስረዳል ብለዋል።
የምርጫ አሰፈጻሚዎችን በተመለከተ ሁሉም በትምህርትና በልምድ ጥሩ የሚባሉና ከወገንተኝነት የፀዱ መሆናቸው ተገልጿል።
በየምርጫ ጣቢያዎች ይፋ በተደረገው ጊዜያዊ ውጤት ላይ ምንም አይነት ቅሬታ ለቦርዱ አለመቅረቡ ተገልጿል።
ድምፃቸውን ለመስጠት በሰልፍ ላይ የነበሩ መራጮች ለቦርዱ በደረሰው ጥቆማ መሰረት በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ አሰጣት ሂደቱ እስከ ምሽት ሦስት ሰዓት እንዲቀጥል መደረጉንና እስከ ሌሊቱ ሰባት ሰዓት ድረስ የድምፅ መስጠት ሂደት ሲካሄድ መቆየቱን ተገጿል።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.