ይድረስ ለትውልደ ኢትዮጵያ ምሁራንና አገር ወዳዶች በሙሉ – የአገርህንና ቀጠናህን አድን ጥሪ – ክፍል ፯ (ከአባዊርቱ)

ethiopiansመንደርደርያ!
እድሜ መስተዋት ናትና ብዙ አሳልፈን እነሆ ለታሪካዊዉ የምርጫ ዋዜማ ደርሰናል። ይህም ዘመን የእውነተኛው የኢትዮጵያችን ህዳሴ ማሳለጫ መባቻ መሆኑ እሙን ነው። የዛሬው አርስት ምርጫዬ ከድህረ ምርጫ በሁዋላ አገራችን ሰለሚገጥሙዋት ተግዳሮቶች እንደምን አገራችንን ብሎም ቀጠናችንን እንደምንታደግ ጥቂት ለማለት ስለሆነ የአገሬ ምሁራንና አገር ወዳዶች ከምርጫውም በሁዋላ ዳግም ስህተት እንዳንሰራ ለማሳሰብም ያህል ነው።
ውድ ወገኖች!
ዛሬን ላይ ቆሞ መቼስ የዶር አቢይን በእሳት ተፈትኖ ኢትዮጵያችንን በነፍስ ከውጭና ውስጥ የፅልመት ውላጆች እየተዋጋ እዚህ አድርሶልናል። የአውሮፓ ህብረትን የሚያክል ተጠሪ በጠራራ ፀሀይ እንዲህ ዘቅጦ በአደባባይ ሲቀጥፍ፣ የባይደን አስተዳደር በዛች ቀላዋጭ ዙዛን ራይስ አፈቀላጤነት ክህደት ሲፈፅምብን የታዩኝ ነገሮች አወይ የኢትዮጵያዊንትን ስነልቦና አለመገንዘብ አስብሎኛልም። የነሱ ክህደት ለኛ የአንድነታችን ፍቱን መድኃኒት መሆኑን ማን በነገራቸው እንጅ ።እንዴት አድርገን የነሱን ክህደት ለኢትዮጵያችን ትንሳኤ እንደምናውለው ልጠቁም፣
የምእራቡ አለም ክህደትና የኢትዮጵያ ትንሳኤ፣
ባለፉት ሰላሳ አመታት የምእራቡ አለም ኢትዮጵያችንን የሚያውቋት በሱቅ በደረቴ ዲፕሎማቶች፣ ከአገር ፍቅር ይልቅ በንዋይና ፈረንጅ ፍቅር የነደዱ ተምቾች ይርመሰምሱባት የነበረችን ሀገር ፣ የሚታዘዙላቸው ሹማምንት የበዙባት ሀገርን ነበር። ከ ፫ አመታት ወዲህ ግን ወድያ ወዲህ ቢነቀንቁትና ቢፈታተኑት ፍንክች የማይል አቢይ የሚባል የቅድመአያቶቹ ፣ የነ አይበገሬዎቹ የኢትዮጵያ ልጅ ጋሬጣ ሆኖ ከፊታቸው ስለቆመ እጅግ የወረደና ለውሸት እንኩዋ የውሸትን ደረጃ ያልጠበቀ ቅጥፈትን ከ ፊንልንዱ ግልብ ሰውዬ ለመስማት በቅተናል። በአንድ በኩልም ነገርዬው አኩርቶኛል – እመለስበታለሁ።
አሜሪካ ሆነች ምእራብ አውሮፓ ይመስለናል እንጅ ለነሱ ስላጎበደድን አያከብሩንም፣ አይወዱንምም። ምናልባት ያው ዘላለማዊ ጥገኛ ለማድረግ ግን የማይነጥፍ የሚመስል የገንዘብ ድጎማ ከማድረግ ወደሁዋላ እንደማይሉ እሙን ነው። በውርደት ከሚገኝ ድጎማ ይቅርብን የሚል ጉደኛ መንግስት መጣባቸውና አቅጣጫው ጠፋባቸው እንጅ ።
ምእራብያውያን በተመለከተ አዲሱ መንግስት ምን ማድረግ አለበት? የምሁራንስ ሚና ምን መሆን አለበት?
በመጀመርያ እንደምኞቴ ማንም ያሸንፍ ከዚህም ቀደም በዚህ ብዙ ብያለሁ የብልፅግናና ኢዜማ ጥምረትን እመኛለሁ በምርጫ ማግስት ። በምርጫ ማግስት  እነዚህ ሁለቱ ማንዴቱን እንደተጎናፀፉ  እንኩዋንስ ለወደፊቱዋ የኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ምስረታ ይቅርና ለተቃዋሚነት እንኩዋ የማይመጥኑትን በጎሳ ፖለቲካ የተሰገሰጉትን የብልፅግና ይሁን ሌሎችን ልቅም አድርጎ ወደየቤታቸው፣ እርሻቸው ይሁን ንግዳቸው ማሰናበት። እስቲ የኢትዮጵያ አምላክ ያሳያችሁና ዬትኛው የፌዴራል ይሁን ክልል ፓርላማ ነው በብቃትና ዜግነት ላይ በተመሰረቱ ጠበብቶች የተሞላው? ስንቶቻቸውስ ናቸው የፌዴራሉን ይሁን የየክልሉን ንድፈ ሀሳብ ተረድተው ለአገር ይሁን ክልል ፍሬ ያለው ነገር ማስተናገድ የሚችሉ? ወንበሩ ይቁጠራቸው።
ስለሆነም አዲሱ የኢዜማና ብልፅግና ጥምረት ይህን ሁሉ አስተካክለው  በብቃትና ክህሎት ተወዳዳሪን ይመርጣሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። አዲስም ማንዴት ስለሆነ የሚከተሉትን እጠቁማለሁ:
፩) የሁለቱ ጥምረት አዲስ አገር አድን አዋጅ በውጭና  ውስጥ ምሁራን ላይ ስለ ማውጣት
ኢትዮጵያውያንን በተለይም በየፕሮፌሽናቸው በአለም የተበተኑትን እንደ መልካም አዝመራ መሰብሰቢያው አሁን ነው። በዚህ አጋጣሚ ዶር ብርሀኑ ከባድ ሚና ይጫወታል ባይ ነኝ። ሁሉንም ባይሆን አብላጫውን የማወቅ እድሉ በውጭ ቆይታው ገጥሞታል። እኔ በፓርቲ አይን ሳይሆን በኢትዮጵያዊ ፕሮፌሽናል አይን ነው የማየው። ብዙ አሉ ያገሬ ልጆች ብዙ ማድረግ ለአገራቸው የሚችሉ። አብዛኛው ሰው ጩሀት የሚያበዙትን የነ ኤርምያስ ለገሰ አይነቶችን፣ የነ ሀብታሙ አያሌው አይነት ወናፎችን ከቁጥር አስገብቶ ወሬአቸውን (ሀሜታቸውን) ሲሰማ የሚውልን የዘመነ ወያኔ ትውልድን በአጭር ጊዜ ወደ መልካሞቹ ጎራ የሚሰበስቡልን  ሞልተዋል – እነ ዳኛቸው ተሾመ አይነቶችን  በኢትዮጵያ ፍቅር የነደዱ ወጣት ምሁራን መጥቀሱ በቂ ነው። በእድሜ የገፉትም አሉ በናት አገር ፍቅር የነደዱና አጋጣሚውን የሚጠብቁ። በምርጫ ማግስት በአንዲት አዋጅ ምርጥና ቆራጥ በየሙያው አንቱ የተባሉትን ኢትዮጵያውያን/ዊያትን ማሰለፍ ይቻላል። በጃን ሀፕኪንስ ጣቢያ ብቻ ስንት ምሁራን እህቶቻችን ለኢትዮጵያ በየቀኑ የሚደሙ እንዳሉ ስንቶቻችሁ ታውቃላችሁ? የምእራባውያኑ ጥመትና ዛቻ ብቃትና ክህሎት፣ ቆፍጣናነትና አይበገሬነታችንንም ጠንቀቅው ስለሚያውቁም ነው። ከወያኔ ያላቸው የፍቅር ጫወታ እነዛ ከሀዲያን ጅቦች የኢትዮጵያዊነት ጠረን ሲያልፍም እንዳልነካቸው ስለሚያውቁትም ነው – አይምሰላችሁ። ከላይ እንደጠቀስኩት የፊንላንዱ ጠቅላይ የዘቀጠው መግለጫ አይሉት እራሱን የጠለፈበት የክህደት ዜና ከዚሁ ከእውነተኛው የኩሩ ኢትዮጵያዊነት ፍራቻ የተነሳ ነው። እስቲ አቢይ ነው ደመቀ፣ ክብርት ሳህለወርቅ ወይስ ዲና ናቸው ያንን መአት ለህዝባችን የተመኙት? ማፈርያ ሰውዬ!!! እናም ይህ አዲስ አዋጅ ባንዲት ጀምበር ብዙ ምሁራንን አሰልፎ እውነተኛውን የኢትዮጵያ ትንሳኤ የሚያሳልጥ ይሆናል።
፪) የምስራቅና ምእራብ ካምፕ
በኢትዮጵያ ታሪክ  እንደ ጃንሆይ ብልጥ መሪ አልነበረንም ተማሪው ጉዳዩ ሳይገባው ሳንካ ባይሆንባቸው ኖሮ ። ምእራቡንና ምስራቁን በ collective security መርህ ጠፍንገው ሲያበቁ ከሁለቱም በዘዴ በመወዳጀት ኢትዮጵያን ለብዙ አስርተአመታት ክብሯን አስጠብቀው አልፈዋል – እስከ ጉድለታቸው። ከጃንሆይ በሁዋላ ይህ አቢይ እንዲህም ከሁዋላው እርቃኑን ሆኖ ምእራብያውያንን ጢባጢቤ እንደተጫወተባቸው ወገን የሚረዳው ካለፈና በተለይም ከዳግማዊዉ የአባይ ሙሌት በሁዋላ ነው። ይህንን እንኳ በቅጡ ለማድነቅ አልታደልንም። ለምን? ከውስጥ የወገንን የአገር ሸማ ለብሰው እንደኛው በልተውና ጠጥተው ግን የሳጥናኤልን ግሳት የሚያገሱብንን የከሀድያን ልጆች መሀላችን በመሰነጋቸው ነው። ይቅርታ አድርጉልኝና በትግራይ ልጆችማ ተስፋ ቆርጫለሁ። ምናልባት በዶር አረጋዊ እድሜ ከቀሩ ጥቂት ምሁራን በቀር ባለፉት ሰላሳ ምናምን አመታት የትምህርት ተቋሞቻቸው ኢትዮጵይዊነቱ ቀርቶ የፅልመት ውላጆችን እንጅ ሰው እንኳ ያፈሩ እስካይመስል ድረስ ኢትዮጵያን ከውስጥና ውጭ እየወጉ ይገኛሉ። ወያኔ በህይወት እያለች እንደዛ ሲያደርጉ በሀዘን “አይይ ፈርተው እንጅ ወደው አይደለም” ብለን ጀስቲፋይ አደረግንላቸው። ዛሬ እንዲህ ወያኔ መቅም ገብታ ከገባችበት አዘቅጥ ለማውጣት ሲዳክሩ ሳይና ስሰማ ፣ በተለይም አይምሮ አላቸው የምናለቸው የነበሩ ወጣት የ አረና ልጆች ጭምብላቸው ተገልጦ ሳየው፣ በምርጫው ማግስት ያቺን የኢትዮጵያችን አሻራ የሆነችዋን ትግራይን ለማፅዳት ወታደራዊ ቀጠና ስር ማድረግ የግድ ነው። በበኩሌ እድሜውን በማየት የአዲሱ የዶር አብርሃምም ሁኔታ አልጣመኝም። ወጣቱን የትግራይ ትውልድ በመጥፎ መርዝ ስለተመረዘ፣ የፅልመት ሰንኮፍ ተነቅሎ እስኪ ውድቅ ድረስ በወታደራዊ ቀጠና ስር ይሁን። በቃ የሲቭል ጫወታ። ገና ብዙ ይቀረናል። ጌታቸው ረዳ ይሁን ታደሰ ወረደ እንኳ ቢሞቱ ገና ብዙ ውስብስብ ጉዳይ ስለሚኖር በነ ጄኔራል ባጫ ቫይስሮይነት ትመራ ትግራይ ። ቅር የሚለው ካለ የኢትዮጵያን ትንሳኤ የማይመኝ ብቻ ነው። ይህው ነው። ይህን ካደረግን የምእራብያውያን ጉዳይ እልባት ያገኛል። ከቻይናና ሩስያ ያለንን ትስስር እጅግ ላቅ ማድረግ ያስፈልጋል። በመከራው ጊዜ ሁሉ የሚደርሱልን እነሱው ብቻ ሆነው አረፉት። ይረዳኝል ሁሉም የየራሱ አጀንዳ እንዳለው ፣ እኛም የራሳችን በ ኮሌክቲቭ ሴኩሪቲ ያጠነጠነ ቢኖረን ይብልጡኑ ያስከብረን ይሆናል እንጅ አያጎድለንም ለማለት ነው።
፫) የኢትዮጵያና ኤርትራን ወዳጅነት ከፍ ስለ ማድረግ
የኤርትራን ውለታ ይህ ትውልድ ሳይሆን የወደፊቱ ትውልድ ይፋ ያወጣው ይሆናል። የማውቀውና ያደኩበት የኢትዮጵያዊነት እልክና አይበገሬነትን ያየሁባቸው ኤርትራውያን በዚህ ሁለት አመታት አስደምመውኛል። የወያኔ ዝተቶችና እንግዴልጆች ቢጠሏቸውስ ምን ይገርማል? ይህን ወዳጅነት ወደ ኮንፌዴሬሺን በአስቸኳይ ከፍ አድርጎ የወያኔና የአይዟችሁ ባዮች ምእራባውያንን ቡግንጅ ማፈንጅያው ወቅት ከምርጫው በሁዋላ ነው። ታድያ ኤርትራውያንና አገራቸውን በክብር ማስተናገድ የግድ ነው። አንድ ነን ጥሩ ሆኖ አንድ ነን በምግባር እንደ ሀገር ግን ሁለት ነን ቢታከልበት የሚፈልጉትን ክብርና ሞገስ እንደማጎናፀፍ ነው – ይገባቸዋልምና። ይህም አካሄድ የምእራብያውያንንም ይሁን የከጄልቱ ጁንታ ጀሌዎቻቸውን አንደበት እስከወዲያኛው ይዘጋል።
ማጠቃለያ!
ምን እናድርግ ከምርጫው በሁዋላ?
እኔ የአገርና የመጨረሻው ቀጠና አድን ጥሪ የማደርገው
የምርጫውን ውጤት ተቀብሎ በአንድነት በመቆም ጠላትን ማሳፈር ለኢትዮጵያውያን የተስፋና ትንሳኤ መሰረት መሆንን ነው። ይህ ምርጫ እንደተደገሰልን ሳይሆን በፈጣሪ ቸርነት አንድነታችንን የምናጎለብትበትና እምቢኝ ባይነታችንን የምናድስበት የቃል ኪዳን መሰረት ይሆነናል ብዬ እጅግ ከልቤ አምናለሁ። የኢትዮጵያችን አምላክ ይህ ይሆን ዘንድ ይርዳን ።
አሜን።

3 Comments

 1. አባዊርቱ በብሄር የተደራጁትን ባለመደገፎ መልካም ይመስላል ብልጽግና ከብሄር ውጭ ነው ብለው ያስባሉ?
  በውጭ ያሉትን ምሁራን የማፈላለጉን ስራስ ለብርሀኑ እንዴት ሰጡት? ብርሀኑና አንዳርጋቸውን የመሰሉት የሚያመጡት ምን አይነት ዜጋ ይሆናል? ምርጫዎስ እንዴት እነዚህ ሰዎች ሆኑ? በታላቁ የኢትዮጵያ ባንድራ ስር ብዙ ዘመን ኑረው ይህን የኢሉሚናቲ ባንድራ ለምን መረጡት? ከረብሻና እንደመንደር ሴት በብሽሽቅ የተካኑትን ታየ ደንዳንና ድፍን ከተማ ሲቃጠል አርፈህ ተኛ ብሎ ለበታቹ ትእዛዝ የሰጡት እንደ ሽመልስ አብዲሳ ከምርጫው ብሁዋላ ቦታቸው የት ይሆናል?

  እንዲህ እንዲህ ያለውን ስናገጣጥም ጥርጣሪያችን የጎላ ይሆናል ኤርምያስና ሀብታሙ የፋሽስት ትግሬዎችን ለመጣል ባለ ውለታችን ናቸው ከነሱ በከፋ ስዩም መስፍን ከሞተ በሁዋላ አቅሉን እንደ መንሳት ያደረገው ቴዎድሮስ ጸጋዬ ነበረሉት። ለኢትዮጵያ መልካም አሳቢ ከሆነ ብዙ ሊሉት የሚችሉት ነበሮት የስበት ማእከሎ ካልጎተቶት በስተቀር። አምላክ አገራችንን ይታደግ ነገር ሁሉ ተበላሽታል ወታደር ለመግደል እስከ መሳሪያ በረሀ ገብቶ ሳይደመሰስ የተያዘውን ዘፋኝ አንድ ቀን ሳይታሰር መልቀቅ ምን የሚሉት ነው? ስብሀት ነጋም ይለቀቅ የታሰሩት ይለቀቁ። መሳፍንት ጥጋቡ መግደል አለመግደሉ ሳይረጋገጥ ትግሬን ማስተንፈሻ እንዲገደል ውሳኔ ሲሰጥ መከላከያውን ያረዱት ይሽሞነሞናሉ ይህ ነው ኦሮሙማ የኢትዮጵያ አምላክ ይፍረድ።

 2. መልካም ዕድል ለሁሉም ተፎካካሪዎች፤
  በየትኛውም ወገን እንሁን ሁላችንም የአንድ እናት ልጆች ነን፤ እናታችን ታሸንፍ፤
  ሃገሬ ኢትዮጵያ፤ ሰላምሽ ይብዛ!

 3. አባ ዊርቱ፣
  ደግ ደጉን ለ አገራችን ኢትዮጵያ መመኘትዎ ታላቅ ስብዕናዎን አጉልቶ ያሳያል። እግዚአብሔር ይባርክዎ።
  ከ ጽሁፍዎ ውስጥ በጣም የ አሳሰበኝ የ ትግራይ ጉዳይ ነው። አንድ መላ ከ አልተደረገለት ለ ኢትዮጵያ አለመረጋጋት ምክንያት ይሆናል ብዬ እሠጋለሁ። የ ኢትዮጵያ ሠራዊት ትግራይ ውስጥ የማያባራ ጦርነት ውስጥ መዘፈቅ የለበትም። ደርግ የወደቀው እንደዚያ በ ማድረጉ ነው። በ እኔ ግንዛቤ መሆን የ አለበት ሠራዊቱ ትግራይ ድንበር ላይ ሠፍሮ እንደፈለጋቸው እንዲሆኑ መተው ነው። በ አላቸው የ ውጭ ድጋፍ ጦርነቱን ማራዘሙ ብዙ መዘዝ ያመጣልና።

  ሌላው ምልከታዎም ትክክለኛ ና መደረግ የ አለበት ነገር ነው። ምሁራን ሁሉ ተረባርበው አገራችንን በየሙያቸው ከአልረዱ ከ አለችበት ችግር ፈጽሞ ልትወታ አትችልም። ስለዚህ ፕሮፌሽናሎች ተደራጅተው ለ አገራችን ብዙ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ይህ ታላቅ ተግባር ሊተገበር የሚችለው መንግሥት የ ዜጎችን ህልውና ና መብት ከ አስከበረ ብቻ ነው። እነዚህ መብቶች ሳይከበሩ ኢትዮጵያውያንን ለታሰበው አላማ ማሰባሰብ አይቻልም።

  ማንም ይምራ የዜጎችን መብት ማስከበር አለበት። የ አለፉት የ ህልውና ና መብቶች ጥሰቶች ፈጽሞ ሊደገሙ አይገባም። ያ ከሆነ አገር ትፈርሳለች። አልጠራጠርም።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.