የኢትዮጵያ ትንሳዔ  ቢባልስ – ማላጂ

የግዕዝ ቋንቋ በዓለም ከሚገኙ በቁጥር አነስተኛ ነገር  እጅግ ጥንታዊ ሜቲክ ቋንቋ የሆነ ከዕብራይስጥ፣ አረብኛ…… ቋንቋዎች የሚዛመድ መሆኑን የአገራችን  እና የዓለም ሊቃዉንት በተለያየ ጊዜ እና አጋጣሚ ለዓለም ምስክርነት ሰጥተዉበታል፡፡

እንደምንሰማዉም  ምዕረባዉያን  በተለይም ጀርመን በከፍተኛ ትምህርት ተቋም በመደበኛ ትምህርት ጥናት ከጥንት ጊዜ ጀምሮ እንደሚካሄድ እና እንደሚሰጥ ይነገራል/ይሰማል ፡፡

geez

ግዕዝ በባህሪዉ ብዙ የምርምር፣ጥበብ ፣ እና ታሪክ እና ሁለንተናዊ ኢትዮጵያዊነት እና ጥንታዊነት መሰረት እና አብነት ነበር ፤ነዉ ፡፡

ርግጥ ነዉ አፄ ቴወድሮስ በዘመናዊት እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ግንባታ ዘመን የግዕዝ እና አማርኛ ቋንቋ  አጠቃቀም  እና አገልግሎት መለያየት አስፈላጊ መሆኑን  ንጉስ ቴወድሮስ ቋንቋ ለቤተ ክህነት እንዲሁም አማርኛ ለቤተ መንግስት እንዲያገለግሉ ሆኖ ተወስኗል ፤ በአዋጅ መደንገጉን እኛም ፤ዓለምም  እናዉቃለን፡፡

ሲያሳስበኝ የነበረዉ እና አለመማሬ የሚቆጨኝ የአገራችን የግዕዝ ቋንቋ  የሁለንተናዊ ማንነት መሰረት የሆነ  ሲሆን ለቤተ መንግስት ፣ ለዘመናዊ መንግስት  መመስረት ፤ዕድገት እና ለብሄራዊ ዕድገት እና ብልፅግና ባለዉለታ መሆኑን ከእኔ ይልቅ ለኢትዮጵያዉን እና ለዓለም ህዝብ መተዉ ይቀላል፡፡

ለዛሬዉ የምስራች የተሰማኝ በባህርዳር የክልሉ የትዕይንት ዜና በክልሉ( አካባቢዉ) በሚገኙ የትምህርት ተቋማት በመደበኛነት ሊሰጥ በዝግጅት ላይ መሆኑን ስሰማ በእጅጉ ደስ የሚያሰኝ ብሄራዊ ብስራት ነዉ ፡፡

በተለይም በዉይይት ወቅት የተነሱ  እና ስለ ግዕዝ ቋንቋ  ከዕምነት ጋር የማያየዝ  ልማድ በሚመለከት የተሰጠዉ ማገናዘቢያ በጣም የሚያስመሰግን ነዉ ፡፡

በርግጥ ዕምነት እና ቋንቋን ከአንድ ማህበረሰብ  በዘመናችን አጠራር ብሄር ጋር ማገናኘት የትዉልዱ ፍላጎት እና ዕምነት ሳይሆን ህዝብን ከህዝብ  አማኝ እና መናኝ አድርጎ ለማሳየት ከፋፋይ ሴራ መሆኑን መርሳት የለብንም ፡፡

እንደምናዉቀዉ በዘዉድ ስርዓት ግዕዝ በብሄራዊ (አገር ዘቀፍ) ፈተና ድረስ ይሰጥ እንደነበር እንሰማለን ፤ከታሪክ እንረዳለን ፡፡

ሆኖም ዕምነት እና ኢትዮጵያዊነትን ከቋንቋ እና ከማንነት ጋር  ማያዝ እና መደባለቅ የአገራችን የፖለቲካ ፈሊጥ ሆኖ እንዲነገድበት በመሆኑ ዛሬ ላይ ከረጅም ዘመናት በኋላም ቢሆን እንዲህ መታሰቡ ይበል የሚሰኝ ነዉ ፡፡

ዕዉቀትም እንዲህ ነዉ ከራስ ወደ ዓለም መድረስ፡፡ ዛሬ የዓለማችን  አለኝታ ሊሆን የሚችል የስነፅሁፍ፣ የምርምር(ፍልስፍና/ሳይንስ)፣ የስነ መንግስት፣ የምጣኔ ሀብት እና የመሳሰሉት ግንባር ቀደም አገሮች መሰረት እና ምንጭ ከራስ መነሳት እንደሆነ ዛሬ በገሀዱ ዓለም ያየንዉ እና የምናየዉ ዕዉነት (ተፈጥሯዊ) የሆነ ንቡር ነዉ ፡፡

ክቡር ደ/ር ከበደ ሚካል ….ጃፓን እንዴት ሰለጠነች…….ሲሉን እኛ እንዴት ደነቆርን ብንል ሊሆን የሚችለዉ የሩቅ ናፋቂነት እና ከራስ መጣላት ቁራኛ መሆናችን ነዉ ፡፡

በመጨረሻም ስለ ግዕዝ ቋንቋ በነበረ ዉይይት የቤተ ክህነት ሊቃዉንት ከጠቀሷቸዉ እና ከተማርኩባቸዉ ዉስጥ  ሳልጠቅስ የማላልፈዉ ፡-

“ቋንቋ ኃይማኖት የለዉም ይልቅ ቋንቋ  አገልጋይ መሳሪያ ነዉ(ይሰበካል፣ ይወደሳል፣   ይቀኛል፣ ይጠበባል…..) ሲሉ ሌላኛዉ  ዕለቱን የግዕዝ እና የኢትዮጵያ አገር በቀል ዕዉቀት ትንሳኤ ነዉ” ብለዋል ፡፡ በሚገባ ተገልጧል …..ግን እኔም እዚህ ላይ ማከል ቢፈቀድልኝ  የግዕዝ ትንሳኤ የአገር በቀል ዕዉቀት ትንሳኤ መነስኤ ከመሆኑ በላይ የኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን ትንሳኤ ቢባል ማጋነን አይሆንም ፡፡

በርግጥ የትግራይ ክልል በሁለት ዓመት አስቀድሞ የግዕዝ ትምህርት በመደበኛ ትምህርት ስርዓት  እንዲካተት ማድረጉን ስናስታዉስ በጊዜዉም ሆነ አሁን የሚያስመሰግን እና አርዓያነት ያለዉ በጎ እና ሚያስቀና ተግባር ነበር ፤ነዉ ፡፡

አቢሲንያ…….ኢትዮጵያን  ስታወርሰን  ግዕዝ  አማርኛን፣ ትግርኛን……..አውርሶን ብዙ የጥበብ እና ምርምር ክምችት ሀሳብ ይዞ  በራሱ ምድር እና አገር ተርስቶ እና ተገፍቶ ለዘመናት በግዞት ተወስኖ ኖሯል፡፡

በኢትዮጵያ እና ሴሜቲክ ቋንቐወች ጥናት እና ምርምር እንዲሁም የኢትዮጵያን ጥንታዊ እና መናዊ ምንነት እና ማንነት ለዓለም በመመስከር ከፍተኛ በጎ እና ዘላለማዊ ተጋድሎ ላደረጉት በአገር ዉስጥ እና ዉጭ ላሉት ፣ በህይት ላሉት እና ለሌሉት በጥቂቱ ከምጣቅሳቸዉ  ፕ/ር ኤፍሬም ኢስኃቅ፣ ፕ/ር ጌታቸዉ ኃይሌ፣ አለቃ አያሌዉ ታምሩ፣ ………… እኛ ቀርቶ ዓለም  ለዓለም ለሰጡት አበርክቶ ዝንት ዓለም ያከብራቸዋል፣ይዘክራቸዋል  ፡፡ የምንጊዜም የሰዉ ልጆች መነሻ እና መድረሻ  ማሳያ መስታዉቶች ፡፡

እናም የግዕዝ ትንሳዔ የኢትዮጵያዉያን ትንሳዔ ቢባል ቢያንስ እንጅ አይበዛም፡፡

“የግዕዝ  ቋንቋ ከግዞት (ከተገደበበት) አርነት  መዉጣት የኢትዮጵያዉያን እና ኢትዮጵ  ትንሳኤ እና ነጻነት ነዉ ”!!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.