ጠቅላይ ሚኒስትሩን በመጥላት የብዙ አስረ አመታት የጎሳ ፖለቲካ ያመጣው የኢትዮጵያ ችግር አይፈታም – አልማዝ አሰፋ -ዘረ ሰው

abiyዛሬ ያለውን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድን የሚጠሉ ሰዎች በተለይ ኢትዮጵያዊ ነን እያሉ የሚደልሉ : ለኢትዮጲያ ሰላምና የወደፊት እርምጃ : ለሕዝቦቿ አንድነትና ብልፅግና ከውጭ ጠላት : ከውስጥ ባንዳዎችና በግልፅ በጎሳ ከተደራጁት ድርጅቶችና የጎሳ ፖለቲካ አቀኝቃኞች ግለሰቦች የበለጠ አደገኞች ናቸው ብዬ ፅሁፌን ብጀምር ስህተት እይሆንም::

 

ሁላችንም እንደምንገነዘበው የኢትዮጵያ ችግር ዋናና ብቸኛው መነሻ የጎሳ ፖለቲካ ነው:: የታሪክ መሃይም ብሆንም : የዛሬ ሰባት አስረ አመታት ኤርትራን ከኢትዮጵያ ለመገንጠል የተነሳው የጎሳ ንቅናቄ ዛሬ በአገራችን ውስጥ እንደ አሸን ለፈሉት የጎሳ ፖለቲካ ድርጅቶች ክርስትና አባት ነው:: ጣሊያን ባደረገው ወረራ እንደዛሬ አያድረገውና አያቶቻችን ጎሳ ነገድና ሃይማኖት ሳይቆጥሩ አንድ ሆነው በፍቅር ጦርና ጋሻ የመክላከያ መሳሪያ በማድረግ በጀግንነት ተዋግተው በአውሮፕላንና በመርከብ በመታገዝ በዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጀበውን የሰላቶ ጦር ገርፈውት ከአብዛኛው የኢትዮጵያ ግዛት አባረሩት:: ለዚህም ድል ዋነኛ ጀግናዎቹ በድንበር የሚገናኙት የትግራይና የአማራ ኢትዮጵያውያኖች ናቸው:: ትግራያንና አማራዎች በቀይ ባህርም ሆነ በሱዳን በኩል ለሚነሳው ለአገር ጥቃት የተጋለጡ በመሆናቸው የኢትዮጵያን ህልውናን ለማስጠበቅ ከተቀሩት የኢትዮጵያ ወንድሞቻቸው ጋር ለዘመናት ደማቸውን አፍሰዋል : አጥንታቸውን ከስክሰዋል:: የአገር ስሜት በቋንቋ ወይም በሃይማኖት ወይም በባህል ስለማይመነዘር ኢትዮጵያዊነታቸውን ባንዲራውቸውንና የእገራቸውን ድንበር በማስከበር የአገራቸውን ህልውንና የሕዝባቸውን አንድነት አስከብረው ይገኛሉ:: የአገር ስሜት በደስታ ወይም ባኮረፍን ጊዜ የምናበራውና የምናጠፋው እንደ መብራት ማብሪያና ማጥፊያ አይደለም:: የአገር ስሜት ስልጣን ላይ ስንወጣና ሃብት ስናካብርበት የምናነሳው : ስልጣን ስናጣ የምናስወግደው ሱስ አይደለም:: የአገር ስሜት በእኔ እይታ በሕይወት እስካለን የማይለወጥና የማይሸረሸር ቋሚና ዘላቂ ፍቅር ነው:: ለዚህም ነው የኤርትራ ጎሳ ላይ የተመሰረተ ንቅናቄ የትግራይን ኢትዮጵያውያንን ያላካተተው:: በትግራይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ጥቁር ነጥብ የጣሉትን ከሃዲ ባንዳዎችንና የባንዳ ልጆች ቁጥር ውስጥ ሳንከት : ትግራይ ኢትዮጵያውያን ምን ያህል ጥልቅ የሆነ የአገር ስሜት ፍቅር እንዳላቸው ለመረዳት በ3000 አመት የኢትዮጵያ ህልውና የተጫወቱትን ሚና ማየት እንጂ የዛሬ ሰላሳ አመት በጠመንጃ ሃይል ስልጣን የተጎናፀፈውን ዛሬ ግን ባልታሰበ መቅሰፍት በደረሰበት የለውጥ እሳት ተቃጥሎ አመድ የሆነውን አገር አፍራሽ የወያኔ ጁንታ ሊፅፍ የሞከረውን ተረታዊ ታሪክ አይደለም:: ትግራይ ኢትዮጵያውያን ለእናት አገራቸው ያላቸው ስሜት ለ3000 አመታት ቅድመ ቤተሰቦቻቸው ያቆዩላቸውና ያወረሷቸው የአገር ፍቅር ምንም እንኳ አረመኔው ወያኔ ጁንታ በጉልበት ሊያጠፋባቸው ቢሞክርም በምንም ሁኔታ አይለውጡትም:: የዛሬ 3000 አመታት የትግራይ ሕዝብ ኢትዮጵያዊ ነበር:: ዛሬም ነው:: የዛሬ 3000 አመታትም ኢትዮጵያዊ ይሆናል:: ይህንን ስል የተቅሩትን የኢትዮጵያ ጎሳዎች በማሳነስ አይደለም:: የኢትዮጵያ ችግርና ስቃይ የተፈጠረው በሶስቱ የኢትዮጵያ ሃያላን ጎሳዎች ፉኩክር ስለሆነ ነው:: እነዚህም ኢትዮጵያን የሚያምሱት ጎሳዎች : በመጀመሪያ የኔውኑ አማራ ጎሳ ሲሆን : ሁለቱ የችግር ፈጣሪ ጎሳዎች የትግራይና የኦሮሞ ጎሳዎች አባላት ናቸው::

 

የኤርትራ በወራሪ እጅ መሰንበቷ ምክንያት : በቀይ ባህር ሰፍሮ የነበረውን የጣሊያን ኃይል መቋቋም የሚችል ጦር ኢትዮጵያ በጊዜው ስላልነበራት ነው:: በእንግልዝና በዘመኑ ሃያላን ሃይሎች ሽምግልና ኤርትራ ወደእናት አገሯ ትመለስ ወይስ ነፃ አገር ትሁን የሚል ውሳኔ ማስተላለፍ ያለባቸው የጠቅላይ ግዛቷ ኗውሪዎች ናቸው በማለት ሕዝበ-ውሳኔ (REFERENDUM) እንዲሰጥ ተደርጎ በሕዝብ አንድነት በሚያምኑትና ኢትዮጵያ የምትባለው ምድር የእነሱም መሆኗን የተረዱና ቅድመ ቤተሰቦቻቸው ደም እፍሰው : አጥንት ከስክሰው : ሕይወታቸውን ሰውተው ያቆዪላቸው አገራቸው መሆኗን በሚረዱ ኤርትራ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ድምፅ ኤርትራ ከእናቷ ኢትዮጵያ ጋር ተቀላቀለች:: ይህም ለጠባብ ኤርትራውያን ጎሰኞች የመገንጠል ንቅናቄ ምቹ አጋጣሚ ሆነ:: የእናትና ልጅ አንድነት ያልተዋጠላቸው የጣሊያን አሽከሮችና ለሆዳቸው የኖሩ ባንዳዎች የጎሳ ፖለቲካቸውን እቀጣጠሉ:: ሆኖም የባንዳ ልጆች በወያኔ ጁንታ ስም ተሰባስበው ስልጣን ኮርቻ ላይ ፊንጥጥ እስኪሉ ድረስ የኢትዮጵያና የልጇ ኤርትራ አንድነት ተከብሮ ቆየ:: ባንዳ የወለደው ባንዳ ስለሆነ : ፋሽስቱ ወያኔና(TPLF) ኤርትራ ከተገነጠለች ጀምሮ ራሳቸውን የኢርትራ ፕሬዝዳንት የሾሙት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ የሚመሩት የኤርትራ ሕዝብ ነፃነት ግንባር (EPLF) : በነበራቸው ጀርባዬን እከክ ጀርባህን አካለሁ ስምምነት : ኢትዮጵያን ኤርትራን ከማሳጣት አንስቶ የጎሳዎች ውጊያ ሜዳ አድርገዋታል::

 

ይህንን ያነሳሁበት ዋናው ምክንያት : ያሁኑን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድን የማይወዱ በተለይ ኢትዮጵያዊ ነን እያሉ በአረንጏዴ ብጫና ቀይ ቀለማት የደመቀውን ባንዲራ እየለበሱ : በውስጣቸው ያለውን የራሳቸውን ጠባብ ጎሰኝነት በድብቅ የሚያራምዱ የሚያቀርቡትን የተዛባና ውሃ የማይቋጥር ክሳቸው ለአዳማጭ አሰልቺና ለአገር አንድነትና ደህንነት ጎጂ መሆኑን ለማሳየት ነው:: ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ ከመወለዳቸው በፊት ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ጤና አሳጥቶ የሚያንገላታውን ተላላፊ የጎሳ በሽታ ወረሱት እንጂ አልፈጠሩትም:: ይህንን ጠንቀኛ ወራሪ የጎሳ በሽታ ለማጥፋት በሚያደርጉት ታላቅ ጥረት ላይ ተረባርበን ከማገዝ ይልቅ : ያልሆኑትን ሆኑ : ናቸው እየተባለ በየቀኑ የሚበተነው የሃሰት ወሬ ለአገርና ለሕዝብ ይጠቅማል ብሎ የሚያስብ ካለ በከንቱ ስሜት የተለከፈ ብኩን ሰው ነው:: እኝህ መሪ ሁልጊዜ ትክክል ናቸው ማለት አይቻልም:: ሊሆኑም አይችሉም:: በስራ ሂደት ውስጥ ስህተት ይከሰታል:: የማይሳሳት ሰው : የተኛ ወይም የሞተ ሰው ነው:: ዶ/ር አቢይ አህመድ እንደማንኛውም ሰው ናቸው:: ግን የተሸከሙት ኃላፊነት ከተቀረነው በጣም ይለያቸዋል:: እንዴት 110 ሚሊዮን ሕዝብ ያለባትን አገር ማስተዳደር እንደቢራና ኮፊሾፕ ውይይት ቀላል የሆነው? እንዴት በጎሳ ፖለቲካ የምትታመሰውን አገር ከኪይቦርድ ጀርባ ተቀምጠው እንደሚፅፉት ፍሬፈርሲኪና ከዩቱብ ማይክሮፎን ጀርባ ሆነው እንደሚለፈልፉትና እንደሚያወሩት የቀለለው? በእርግጥ እኝህ መሪ ወደው ለተቀበሉት የአገር ኃላፊነት ሊታዘንላቸው ይገባል:: ለአገርና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላምና ብልፅግና የሚፈልግ የኢትዮጵያ ተወላጅ ቅድሚያው መሆን ያለበት : እንዴት እድርጌ ያለውን ስርአት ከእነጉድለቱ ተቀብዬ ልረዳው እችላላሁ? ብለን መጠየቅ ሲገባን ተጨማሪ የችግር ምንጮች እንሆናለን?

እኝህ መሪ መጠቅ ያለ አስተሳሰብና አመለካከት ያላቸው ብሩህ ሰው መሆናችውን የማይረዳ ሰው ካለ : ሰውን የመመዘን አቅም ወይም ችሎታ የጎደለው ነው:: ለኢትዮጵያና ለሕዝቧ ያላቸው ራዕይ መልካምና ውብ መሆኑን በሶስት አመት አመራራቸው አስመስክረዋል:: አቅደው ያከናወኗቸው ስራዎች ይናገራሉ:: ይህም የማይዋጥላቸው እነሱ ያልመሩትና ያልገዙት አገር እንድትፈርስ ጧትና ማታ የሚሸርቡ እንኩቶዎች ናቸው::

 

አዎን! ስለእሳቸው ብዙ አሉታዎች ይነገራሉ:: ኦሮሞ ያልሆኑ ጠባብ ጎሰኞች ስለኦሮሞነታቸው በማንሳት ለኦሮሞ ያግዛል : ያደላል : ኦሮሞ ይሾማል እያሉ ስም ለማጥፋት የማይሰለቻቸው የሃሜት ስልቻዎችና የማይደርቁ የአሉታ ምንጮች ሞልተዋል:: በተለይ የእኔ ጎሳ : የአማራው አባሎች እንዲህ አይነት ቅሌት ውስጥ ሲወድቁ ማየት ያሳዝነኛል:: በአስተዳደር ስልቶች : በሃሳብ ልዩነቶችና በፖሊሲዎች ላይ ብልህ የሆነ ቅዋሜ ማሰማት ተገቢ ነው:: ግን በጎሳ ላይ የተመሰረተ ቅዋሜ ለአማራው ሕዝብ የሚያመጣው ጥቅም የለም:: እንዲያውም ለዘመናት የአማራ አገዛዝ እያሉ ሸጋውንና ደጉን የእማራ ሕዝብ መቆሚያና መቀመጫ ላሳጡን ጠባብ ጎሰኞች መንገድ በመክፈት : ይኸው ስንለው የነበረው ሆነ:: አማራ ከስልጣን ሲወርድ ኢትዮጵያ ማለቱን ትቶ አማራ እያለ ነው:: ሌላውንም ኢትዮጵያዊ አድርጎ ማየት ትቶ በጎሳ ማየት ጀመረ : ለሚሉት ትረካቸውን ነፍስ ዘርተንበት ቱሉቱላቸውን እንዲቀጥሉ መንገድ መጥረግ ነው:: ለዚህም ነው አማራ ሲገደል : ትግሬ ሲጨፈጨፍ : ኦሮሞው ሲሞት : እውነተኛና ፅኑ ኢትዮጵያውያን ማስተጋባት ያለባቸው ኢትዮጵያዊ ተገደለ : ተጨፈጨፈ : ሞተ ማለት እንጂ : ጎሳን መለያ ማድረግ ልዩነትን በሕዝብ መሃል ከማስፋፋትና ከማራመድ በስተቀር የአገርን ህልውናና የሕዝብን አንድነት አያጠነክርም::

 

ሌላው በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ ላይ የሚቀርብ ክስ : በኢሀደግ ውስጥ ማደጉና መስራቱ ነው:: ይህ በእንድ ስርአት ውስጥ ማደግ : መማር : መስራትና መኖር የሚያስከስስና ኃጢአት ከሆነ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ተከሳሽና ኃጢአተኛ ሊባል ነው? ይህን አይነት አስቂኝ ግምገማ የሚሰጡ በእውነቱ ከመናገራቸውና ከመፃፋቸው በፊት ድጋሚ ሊያስቡ ይገባቸዋል:: እንኳን ከተማረ ሰው አፍ ይቅርና ከመሀይሟ እናቴ ሊወጣ የሚችል ነገር አይደለም:: ሰውን ዝም ብሎ መጥላት ይቻላል:: ግን የማይረባ ምክንያት ማቅረብ ራስን ያስገምታል:: ዋጋ ያሳጣል:: በተበላሸ ስርአት ውስጥ መኖርና መስራት የማህበረሰቡን አባል ሁሉ ጨቋኝና ገዳይ ያደርጋል ብሎ መደምደም አይቻልም:: የዚያን ስርአት ጉድለትንና ጎጅነትን የሚረዱ ሰዎች በውስጡ መካተታቸው አይቀርም:: አመቺውን ጊዜ ጠብቀው ስርአቱን ያስተካከሉ በሌላዎች አገሮች ታይተዋል:: ኢትዮጵያም እድሏ ሆኖ በፋሽስቱ ወያኔ ስርአት ውስጥ አድጎ : ተምሮ : ሰርቶ የኖረው ሰው ከአባሮቹ ጋር ሆኖ ስርአቱን በመለወጥ የተስፋ ጮራ እያበራ ይገኛል:: ወደድንም ጠላንም አገሪቱ የምትደዳረው በጠላነው ስርአት በተነደፈ ሕገ መንግሥት ስለሆነ : ሕዝብ የተሰጠውን መብት ተጠቅሞ በመጪ ምርጫ የሚፈልገውን ወኪሎቹን መርጦ በሚቋቋመው የሕግ ምክር ቤት : አዲስ ሕገ መንግስት አስኪነደፍ : የተወሰኑ ለውጦች ማምጣት አይቻልም:: አንዳንድ ሰዎች ሕገ መንግስቱን መለወጥ አለበት ብለው የሚናገሩ አሉ:: ምንም እንኳ ያለው ሕገ መንግስት ሕዝብ የማይፈልገው ቢሆንም : ሳይመረጥ ስልጣን ላይ ያለ ቡድን : በተለይ ከአሮጌው ስርአት የመጣ : እንደፈለገው ሕገ መንግስት መጣስ የለበትም:: ህገወጥነት የጥሩ ለውጥ ባህሪ ሊሆን አይገባም:: ትግስት የተሞላው ለውጥ ለዲሞክራሲ ጥንካሬ በጣም አስፈላጊ ነው:: በጥቅሉ በእሀደግ ውስጥ መኖርና መስራት የለውጥ ሐዋሪያ አያደርግም ለሚሉት : መሆን ይቻላል እላቸዋለሁ::

 

የስው ልጅ ድክመትን መታዘብ የምንችልበት አንድ መንገድ : እንዴት ነቀፌታን ተቀብሎ ማስተናገድን እንደሚችል ስንገመግም ነው:: አብዛኛው የሰው ልጅ ሂስንና ተቃውሞን በጥሞና አይቀበልም:: ራስን ትክክልኛና እውነተኛ አድርጎ ማቅረብና መውሰድ ሚዛናዊ መሆን ይኖርበታል:: ማንኛችንም ፍፁምና ሁልጊዜ ንፁህ አለመሆናችንን ተገንዝበን : ሌላው ሁልጊዜ እኛ የምንፈልገውንና የምንመኘውን : እኛን የሚያስደስተንና የሚስማማንን እንዲያደርግ መጠበቅ ተገቢ አይደለም:: ምክንያቱም እኛ ሁልጊዜ ሁሉንም አናስደስትም:: ማለትም ድርጊታችን : ሃሳባችን : እቅዳችን : ፅሁፋችን ሁልጊዜ ለሌላው ተስማሚ ነው ማለት አይቻልም:: በዚች ፅሁፌ የሚደሰቱ አሉ:: በተቃራኒ ቢያገኙኝ ጉሮሮዬን የሚያንቁ እንዳሉ አረዳለሁ:: ማንም ፍፁምና መቶ በመቶ እውነተኛ ሰው በዚህ አለም አይገኝም:: እኔ የማቀርበው ፅሁፍ : አንባቢ አንብቦ ከሚያስበው ሃሳብ ጋር ሊጣጣም ይችላል በሚል ግምት እንጂ : የእኔ እውነት ከአንባቢ እውነት ጋር መቶ በመቶ ይዛመዳል ብዬ ልምል አልችልም:: ለዚህም ነው ሌላ ሰው የሚያደርገው ድርጊት : የሚያራምደው እቅድና የሚሰጠው ሃሳብ : ከሌሎች ጋር ሁልጊዜ ይስማማል ብለን መናገር የማንችለው:: ስለዚህ ሌላውን ሰው መተቸት የምንችለው : የሚፈፅመው ድርጊትና የሚያከናውነው ስራ ታዛቢዎቹ ከምንጠብቀው ጋር ይስማማል ወይስ አይስማማም : ለሰፊው ማህበረሰብ ይጠቅማል ወይስ አይጠቅምም ብለን ስንፈርጅ ነው:: ለዚህም በጎሳ ላይ የተመሰረተ ፖለቲካዊ አካሄድ እንኳን ለተጠሉት ጎሳዎች ይቅርና ለራሱ ለጠሊ ጎሳ እንደማይጠቅም : የጎሳ ፖለቲካ አቀንቃኞችና አረማጆች መረዳት ያለባቸው::

 

አስቂኝና ገራሚ የሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ ላይ የሚቀርብ ክስ : እውነት አይናገርም ነው:: እውነት በማይከበርባት አለም ውስጥ የተወለደ ሰው : እውነትን ካልተናገርክ መባል ተገቢ አይመስለኝም:: ሁላችንም እየዋሸን :ይህንን መሪ አትዋሽ ለማለት የስነ ምግባር ስልጣንም የለንም:: ይህንን ስል እውነትን ቦታ ለማሳጣት ሳይሆን : ሌላው እውነተኛ እንዲሆን ስንፈልግ : እኛ እውነትን እያቀነቀንን ነው ወይ? ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል:: እውነት በአንድና በጥቂቶች እኝታ የሚወሰን ሳይሆን : እውነት ያልነው ነገር ለብዙሃኑ ጠቀሜታ የሚውል ከሆነ ነው:: አረመኔው ወያኔ ጁንታ : ለሃያ ሰባት አመታት ሲነፋብን የነበረው ዲስኩርና ፕሮፓጋንዳ እውነት እየተባለ ነበር:: ለደጋፊዎቹና ለጥቅማችው ሲሉ ጫማውን ሲስሙት ለነበሩት አጎብጃጅ ኦሮሞች : አማራዎች : ወላይታዎች ሱማሌዎችና ወዘተ ውሸቱ አውነት ተብሎ ሲሸጥላቸው እያወቁ ተቀብለው ኖረዋል:: እነዚህ የስልጣን ጥማቸውን ለማርካትና በዚያ ተንተርሰው በሙስናና በያዙት ሹመት ከሕዝብ ጉሮሮ እየሰረቁ ሃብት ሲያካብቱና : የሀገርን ልማት እየጎተቱ ሀገሪቱን ለማኝ ሲያደርጉ የነበሩ ስለእውነት ለመናገርና ሌላውን ውሸታም ለመለት የሞራል ስልጣንም የላቸውም:: ፖለቲካ ማለት ውሸትንም እውነት አድርጎ ማቅረብ እንደሆነ መገንዘብ ተገቢ ነው:: በግል ሕይወትም ሆነ በኩባንያዎች : በድርጅቶችና በመንግስት አስተዳደር ውስጥ ሆነ በማህበረሰብ ግኑኝነት ለጥሩ አላማና ግብ ውሸት ተነግሮ ውጤታማ የሚሆንበት ጊዜ አለ:: ስንዋሽ ዋና ጥንቃቄ ማድረግ ያለብን ውሸታችን ከሚሰጠው ጥቅም ጉዳቱ ያመዝናል ወይ? በሚል ጥያቄ ራሳችንን መገምገም ይኖርብናል:: “ሰው ዋሽቶ ሰው ያስታርቃል” የሚለው ተረት በጥልቀት ከመረመርነው እኔ በውሸት ላይ ምን እንደማለት እንደሞከርኩ ሊገልፅ ይችላል:: በውሸታችን እንኳን ሕዝብንና ሀገር ይቅርና የአንድን ሰው ሕይወት የሚያጠፋ ሁኔታ ከፈጠርን : በእርግጥም ዋሽተናል ይባላል:: የሕዝብን ሁከታ ለማቀዝቀዝና ሰላም ለማምጣት የሚነገር ውሸት ለምንድነው? የሚሰጠው ጥቅም ምን ያህል ነው? ብለን በመጠየቅ የተነገረበትን አላማ ልንመረምር እንችላለን:: አባይን እየሞሉ ሁልተኛውን ዙር የአባይ ሙሌት አልሞላንም ብለው ጠ/ሚሩ በይፋ ለአለም ቢናገሩ ውሸት እንደሆነ እናውቃለን:: ግን የዋሹቡት አላማ እየሞላን ነው ቢሉ : ግብፅና ሱዳን ምንም ማድረግ ባይችሉም : የሚፈጠረውን የሶስት አገሮች የፖለቲካ ውጥረት ለመቀነስ ነው:: በትግራይ ክልል ከሃያ አመታት በላይ ክልሉንና የአገር ድንበር እየጠበቀ : ከክልሉ ሕዝብ ጎን ቆሞ ገበሬዎችን ሲረዳ : ትምህርት ቤት ሲገነባ : መንገድ ሲሰራ : ምግብ ሲያድል የነበረውን የፌደራል ጦር አገር ሰላም ነው ብሎ በተኛበት ሰአት አረመኔው ወያኔ ጁንታ ሲያጠቃ : ኢትዮጵያና ኤርትራ የሰላም ስምምነት ባይኖራቸው : ባለፈው ህዳር በኢትዮጵያ ጦር ላይ የደረሰው ጥቃት ኢትዮጵያን ትልቅ ችግር ላይ ይጥላት ነበር:: በዶ/ር አቢይ ብልህነትና ነገሮችን አርቆ በማሰብ ችሎታው : በፖሪቲዎች ተመርጦ ስልጣን እንደያዘ ከጎረቤት አገሮች ጋር ጥሩ ግኑኝነት መፍጠር ለኢትዮጵያ ህልውና እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ተረድቶ በመጀመሪያ ከኤርትራ ጋር እርቅ አወረደ:: በህዳር ወር በትግራይ ክልል በወንበዴው ወያኔ የተለኮሰው እሳት እራሱን ወያኔን እንዲያጠፋ ይህ ወዳጅነት ዋጋውን አሳይቷል:: የኤርትራ ጦር ከኢትዮጵያ ጦር ጋር ተቆራኝቶ የኢትዮጵያን ድንበር ጠብቋል:: ጦራችን በአራቱም አቅጣጫ በተወጠረበት ሰአት : የኤርትራ ጦር የተወሰነ የእገራችን ክልል ውስጥ ገብቶ ለአገራችን የሚጠቅም ስራ ሰርቷል:: በዚያን ሰአት የኤርትራ ጦር ከትግራይ ይውጣ እየተባለ በእለም አቀፍ ደረጃ ዶ/ር አቢይ ሲጠየቁ : የለም ብለው ዋሽተዋል ተብሎ ያደኖቀረን ሃሜታ ከአገራችን ህልውና ጋር ሲታይ እምንት ቦታም አይሰጠውም:: ሀገር ወዳድ የሆነ መሪ የመጀመሪያ ተልእኮው የሀገርን እንድንትና ልዑላዊነት በማንኛውም መንገድ ማስጠበቅ ነው:: ለዚህ ስኬት ማሟያ ማንኛውንም ጠቃሚ ኃይል ከጎኑ ማሰለፍ ግዴታው ነው:: ለአንድ መልካም መሪ ከአገርና ከሕዝብ ደህንነት የሚበልጥበት ነገር ስለሌለ መዋሸት ካለበት እንክት አድርጎ መዋሸት ይጠበቅበታል::

 

አገር ለመገነጣጠል : ትልቋን ኢትዮጵያ ትናናሽ ኦሮሚቻ : አማሪቻ : ትግርቻ : ወላይትቻ : ወዘተ ለማድረግ ሲጥሩ የነበሩ ቅሌታሞች : ዶ/ር አቢይ አህመድ ወደ ስልጣን ሲመጡ : ለጥቅማቸው ሲሉ የበፊት ሀገር አፍራሺነት ስራቸው የተረሳ መስሏቸው አይናቸውን በጨው አጥበው በአማካሪነት ደረጃ ቤተመንግስት የገቡ ሌንጬዎች ምን ያህል ፖለቲካ የሚያራምዱ ሰዎች የፖለቲካ ዝሙተኞችና እንደ እስስት ቶዳ የሚለዋወጡ ውሸታሞች እንደሆኑ ነው:: ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት መንግስታት አሉ በማለት አንዱ የአቢይ ሲሆን : ሁለተኛው እኔ የምመራው የቄሮ መንግስት ነው : ብሎ ጉራውን ሲቸርችርብንና በአልነኬነት ሲመፃደቅብን የከረመውና ሕዝብን በጎሳ ፖለቲካ ሲያጋድል የነበረውና አሁን በእስር ላይ የሚገኘውን ጀዋር መሃመድን ስንመለከት : ምን ያህል ፖለቲከኞች ውሸታምና የግል ጥቅም አስጠባቂዎች መሆናቸውን መገንዘብ አይሳነንም:: ለመገንጠል አላማ የቆመ ፖለቲከኛ እውነተኛ ከሆነ እስከመጨረሻው መታገልና መሞት ያለበት ያንን አላማ ለማሳካት ነው:: ግን የጎሰኞች ፖለቲካ ዋና አላማ በጎሳዎች መሃል ቅራኔ ፈጥረው ሕዝብን በማጋጨት ሀገርን ሰላም ነስተው እነሱ ሀብት የሚያከማቹበትን መንገድ ማጠናከር ነው:: ኢትዮጵያ ውስጥ በጠባብ ጎሳኛነት የተደራጀ ድርጅት ግድያና ዘረፋ ከማድረግ በቀር “ነፃ አወጣሃለሁ” ለሚለው ደሃ ሕዝብ ጠቃሚ ነገር ሲያደርግ አይታይም:: ትምህርት ቤት : ቤተክርስቲያን : መስጊድ : ክሊንክ ማቃጠል እንጂ : ሲገነባ : ውሃ ጉርጏድ ውስጥ ሰው መክተት እንጂ : ሲቆፍር : ሌላ ቋንቋ አትማር አትናገር እንጂ : ሌላ ቋንቋ ሲያስተምር: አይታይም:: “ነፃ አወጣሃለሁ” የሚለውን ሕዝብ መሃይምና ደንቆሮ ያደርጋል እንጂ : ጥሩ ጥሩ ነገር አያስተምረውም: ሰባዊነት የተሳነው ጎሰኛ : ሰውን እንደሰው ማየት የማይፈልግ : ሰዎችን በጎሳ ከፍሎ ሰውነታቸውን ከድቶ : ይህንን ጎሳ አታጊቢ እያለ ጣልቃ በመግባት ሰዎች እንዳይፋቀሩ እንቅፋት ይሆናል:: ይህንን ኢሰብዓዊ ድርጊትና አመለካከትን ለመቀየር የሚታገለውን መሪ ሲከሱት : አንዱ ጎሰኛ ነው:: ሌላው ደግሞ ሙሉ በሙሉ የእኛ ጎሳ አባል አይደለም:: ሶስተኛው ቡድን ደግሞ በእምነቱ በኩል በመምጣት : ፕሮቴስታንት እምነት ያላችውን ብቻ : ስልጣንና ሹመት ይሰጣል ይላል:: እንዲህ አይነት እርካሽ ምክንያት የጎሳ ቅራኔ አልሰራላቸው ሲል በእምነት ልዩነት በኩል አሹልክልከው ሕዝብን ለማጋጨት ካልሆነ ለአገር ልዑላዊነትና ለሕዝብ አንድነት የሚያመጣው ጥቅም እንደሌለ ተናጋሪውም : እሳት ጫሪውም ያውቀዋል:: ጀዋር መሃመድ የሚባለው የየመን ዲቃላ : ኦሮሞና እስላም ነኝ ብሎ : የኦሮሞ ጎሳና የእስልምና ሃይማኖትን እወክላለሁ : ለኦሮሞ ሕዝብ መብት እከራከራለሁ : ክዚህ በፊት በኦሮሞ ሕዝብ ስም ትግል ሲያካሄዱ የነበሩት : ችሎታ የሌላቸው ናቸውና : እኔ ወጣቱ የ34 አመቱ የስታንፎርድና የኮለሚቢያ ዩኒቬርስቲዎች ምሩቅ ስለሆንኩ አዋቂ ነኝና ቄሮን እመራለሁ : ያለ ቄሮ ፍላጎት አዲስ አበባ ላይ በስልጣን ደረጃ ማንም ሊቀመጥ አይችልም እያለ ሲፎክር የነበረው የተማረ ጠባብ ጎሰኛና መሃይም የአቢይን ብልህነት አንድ ሶስተኛ ቢኖረው ዛሬ የከርቸሌን አስከፊነት ባልኖራት ነበር:: ማንኛውም ጎሰኛ የተማረ ክፍልና ጀሌዎቹ የሚረሱት : የኢትዮጵያ ሕዝብን ከማንኛውም የኢትዮጵያ ጎሳ ብንወስደው : የዘመኑ ትምህርት ላይኖረው ይችላል:: ግን አገር ቤት ካለፉት ትውልዶች ጀምሮ እስከአሁኑ ትውልድ ከቤተሰቦቹ ኢትዮጵያዊነትን ወርሶ በኢትዮጵያዊነት ያደገውን ትውልደ ኢትዮጵያዊ : የማንም ተምሬአለሁ የሚል ዶማ ሊያጭበረብረው አይችልም:: ኦሮሞ ወይስ አማራ ወይስ ትግሬ ወይስ ጋምቤላ ጎሳ ይሁን ለዘመናት የውጭውን ጠላት ተባብረውና ተረዳድተው ወግተው እንዳሸነፉት የዛሬውም ትውልድ ጎሳና ሃይማኖትን የልዩነት ምልክት ሳያደርግ ኢትዮጵያን አስከብሮ ለሚቀጥለው ትውልድ እንደሚያስተላልፍ ተስፋ አደርጋለሁ::

 

በመጨረሻ ለጠባብ ጎሰኞች : በተለይ ለእኔ ጎሳ : ለአማራ ጎሳ እባሎች : የማስተላልፈው : አማራ ያልሆነ ጎሳ ተወላጅ : እናንተን ለማበሳጨትና ለማናደድ አማራዎች እንዲህ ናችው የሚል ክስ ሲመጣ ከመጨነቅ ይልቅ: ፊትለፊት እውነትን መጋፈጥ የመሻሻል ትልቁ ችሎታ ነው:: አማራ ተመችቶት ሌላው ኢትዮጵያዊ እየተራበና እየተጮከነ ያሳለፈበት ሕይወት የለውም:: ኦሮሞ ሲቸገር : አማራ ደልቶት : ትግራይ ሲራብ አማራ የጠገበበት ጊዜ አለ የሚል ካለ ውሸት ብቻ ሳይሆን ለኦሮሞና ለትግራይ ኢትዮጵያዊያን ያለአፍረት የሚዋሽ የግል ጥቅሙን በኦሮሞና በትግራይ ሕዝብ ጫንቃ የሚውጣጣ ጥገኛ እንሰሳ (PARASITE) ነው:: ለዚህም ነው : እኔ የምመኘውና የእኔ ጎሳ ስልጣን ላይ ካልወጣ የሚመጣው ለውጥ አጥጋቢ አይደለም የምንል ከሆነ : እምዬ ኢትዮጵያን እንድትበታተን ጮቤ ከመርገጥ በስተቀር አንድና የማይበገረው ልዕልናዋ በትውልዶቿና በዜጋዎቿ እንዲጠበቅ የምናደርገው ጥረት አጥጋቢ እንዳልሆነ መረዳች እንችላለን::

 

ስለዚህ የአገር መሪ ካልጣመን : ዲሞክራሳዊ በሆነ መንገድ : ለመላው እገር የሚጠቅወዉን አመራር : ስራ ላይ እንዲውል ክመጦቆም ይልቅ ጎሳና ሃይማኖት የመሪ መለኪያ በማድረግ ኢትዮጵያን ለማመፅ የምትፈልጉ የኦሮሞ ሆነ የአማራና የትግራይ ጠባብ ጎሰኞች እርስ በርስ ትገዳደላችሁ እንጂ ኢትዮጵያን አታፈርሷትም:: ይህን ሃቅ ለልጆቻችሁ ማስተላለፍ ትችላላችሁ:: ባይሆን ቅድመ ቤተሰቦቻችሁ በደማቸው ለ3000 አመታት ያቆዯትን የጠበቋትንና ያኖሩላችሁን ታሪከኛ አገር ክብሯንና ሞገሷን ጠብቃችሁ ለሚከተላችሁ ትውልድ የሰላምና የፍቅር ቀጣይ አገር በማድረግ አሻራችሁን ጥላችሁ ብታልፉ የመንፈስ እረፍት ይሆንላችሗል:: በጎሳ በሃይማኖት በቁሻሻ ስርአት ውስጥ የሰራ ነው እያልን አፍራሽና እንቅፋት ከመሆን ያለው መሪ ግዴታውን እንዲወጣ ገንቢ ሂስ እያቀረብን የጎደለውን እየጦቀምን : ከትውልድ ወደትውልድ ጠግቦ ይማይበላውን ሕዝብ ከድህንነት መዴብ በጋራ ፈልቅቀን ማውጣት የሁላችንንም ትብብር ይፈልጋል::

 

ኦሮሞ አማራን ይጠላል : አማራ ኦሮሞን ይጠላል : ትግሬ ኦሮሞና አማራን ይጠላል የሚባለው ሕዝብን አጋጭተው የግል ጥቅማቸውን የሚያራምዱ የጥቂት አረመኔ የፖለሊቲካ ዝሙተኞች እንጂ : ኦሮሞ : አማራ : ትግራይ : ወዘተ ኢትዮጵያውያን በጎሳና በሃይማኖት ተጋጭተውም አያውቁም:: ይህ የዛሬ ሰባት አስረ አመታት በኤርትራ ባንዳዎችና የጣሊያን አሽከሮች በኤርትራ ጠቅላይ ግዛት ውስጥ የተጀመረ የአስተሳሰብ በሽታ ነው:: እስኪ መጀመሪያ ሕዝብ ለመኖር የሚያስፈልገውን መሰረታዊ ፍላጎቱን ያሟላ:: ከዚያ የሚቀጥለው ትውልድ ከዛሬ ትውልድ የተሻለ ትምህርትና ብልፅግና አግኝቶ በግሉ የማሰብና ዲሞክራሲን ጠንቀቅ ብሎ ይረዳ:: በቂ እውቀት ካገኘና በኢኮኖሚው አድጎ የሰለጠኑ አገሮች የደረሱበት ደረጃ ሲደርስ ለመለያየት በዲሞክራሳዊ መንገድ ተወያይቶ በምርጫ ያፅድቀው:: ዛሬ ቁርስ በልቶ ምሳ ለመብላት አስተማማኝ ያልሆነ ኑሮ ውስጥ ያለውን: ልጆቹን ማስተማር ያልቻለውን : በማገዶ በጭቃና በጭድ የቆመ አፈር ቤት ውስጥ የሚኖርን ደሃ ሕዝብ በጎሳ ክሌላው ወንድሙ ጋር ማባላት ፈጣሪም አይወደውም:: በእርግጥ ይህንን ቆሻሻ ጎሰኝነት የሚያራምዱ ፈጣሪያቸውንም የሚያውቁ አይመስለኝም:: ሰው እንዴት ሆን ብሎ ሰውን ያገዳድላል? ማረነ ክርስቶስ ብዬ ማለፍ ይሻለኛል::

 

ኢትዮጵያ አገራችንን ላለፉት ሰባት አስረ አመታት የበከላትን የጎሰኝነት በሽታ በአርባዎቹ እድሜ ውስጥ ያለ መሪ አመጣ ማለት ሽምጥ ውሸት ነው:: ይህንን መሪ ስለጠላነው ይህ ስር ሰደድ ጎሰኝነት በሽታ ከኢትዮጲያ ለቆ አይሄድም:: ይህ በሽታ የሚወገደው በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተውን ጎሰኝነት እያንዳንዳችን ከአእምሮአችን ገፈን በማውጣት የአገራችንን ልዑላዊነትና የሕዝባችንን አንድነት በጋራ ስናስብ ነው::

ይህም የተሻለ እስኪተካ ካለው መንግስትና መሪ ጋር ለአገር ደህንነትና ለሕዝብ ሰላም እጅና ጏንት ሆነን ማሻሻያ እያቀረብን መስራት አስፈላጊ ነው::

 

ኢትዮጵያ ለዘለአለም ትኖራለች::

 

 

15 Comments

 1. የሃበሻ ምድር የፓለቲካ እብዶች ስብስብ ነው ስል በመላ ሳይሆን ሲዳሰስ ሊገኝ ከሚችል እውነት በመነሳት ነው። የዘር ፓለቲካ ሃገራችንን ዛሬ ላለችበት የአፓርታይድ የክልል ፓለቲካ ዳርጓታል። የዚህ አስተሳሰብ መስራችና አራማጅ ሻቢያና ከሻቢያ በፊት በረሃ ላይ የነበሩ ነፍጥ አንጋቾች ናቸው። ይህ እውን አይደለም ዝም በል የምትሉ በረሃ የነበሩና ከሞት የተረፉ አሁን በእድሜ የገፉ የኤርትራ ታጋዮችን ጠይቆ መረዳት ይቻላል። ሲጀመር አማራ ጠላትህ ነው ብሎ ያስተማረው ሻቢያ ነው። ይህን ስንኩል ሃሳብ ከሻቢያ ተቀብሎ በቁሙ የተጋተውና እልፍ ግፍ የፈጸመው ደግሞ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ነው። ፓለቲካ እልፈት የለሽ ፍትጊያ ነው። 70 ዓመት ሙሉ የሰው ህይወት የተገበረለት የሶሻሊዝም የፓለቲካ እይታ ፍርክርኩ ሲወጣ የነበረው እንዳልነበረ እንደሆነ በራሽያ፤ በዪጎዝላቪያና በሌሎቹ የዚህ አስተሳሰብ ተለጣፊ ሃገሮች አይተናል። እኛን ስሙ የሚሉት የምዕራቡ ጉረኞች ደግሞ ለከት የለሽ ስመ ዲሞክራሲያቸው ሃገርን ከሃገር እያላተመና እያፈረሰ ይኽው ይነጉዳል። የራሳቸውም ሃገር በተለያዪ የሶሻልና የፓለቲካ እንዲሁም ፍትህ እጦት ይናጣል። እብድ ሂዶ እብድ ይተካል።
  ታዲያ ይህ ሁሉ ነገር ከአልማዝ አሰፋ ሃሳብ ጋር ምን አገናኘው ለምትሉ ሰከን በሉ አስረዳለሁ። ክርችም ብሎ ነው የሚገጣጠመው። በመግቢያው ላይ ዘረ ሰው ያስቀመጠችው ዓረፍተ ነገር ለእኔ ይስማማኛል። በመሰረቱ እኔ ፓለቲካ አልወድም። ፓለቲከኛም ሁኜ አላውቅም። ለነፍሳቸው ከሚያድሩትም አልመደብም። አንድ ነገር ግን ቋሚ መመሪያዬ ነው። እውነትን እውነት ነው ማለት። በዘርና በቋንቋ ወይም ክልልን አልፎ ተርፎም ሃይማኖትን ባልተቆናጠጠ አስተሳሰብ ሰውን በሰውነቱ ማየት። ገልቱ ፓለቲከኞች ዛሬም የሚያቅራሩት በዘራቸው ዙሪያ በመሆኑ ከመንደራቸው አልፈው የሌላውን ህብረተሰብ መበደል የሚያይ ዓይን የላቸውም።
  አሁን እንሆ ዶ/ር አብይን በዚህም በዚያም ጭቃ የሚቀቡት የኢትዮጵያ ወዳጆችና ለሃገሪቱ የሚያስቡ ናቸው ብለው የሚያምኑ ሁሉ ልበ ቢሶች ናቸው። በቅድሚያ ማንም መንግስት በዚህች ምድር ላይ ሙሉዕ የሆነ የለም። ሁሉም ጉድለት አለበት። የጠ/ሚሩ መንግስት ምጡቅ ነው ስህተት የለበትም እያልኩ አይደለም። ግን ሚዛናዊ የሆነ እይታ ላለው ሰው በሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ የተሰሩ የላእላይና የታህታይ የሃገሪቱ መዋቅሮችን መዝኖ ለጠ/ሚሩ ይበርቱ ማለት ይችላል። ዝርፊያው፤ ግድያው፤ ማፈናቀሉ፤ በዘር፤ በክልል ወዘተ ሰውን እንደ እሳር ማጨድ የውጭና የውስጥ ጠላቶቻችን ሴራ እንጂ አንዳንዶች እንደሚሉት ዶ/ር አብይ አማራን ግደሉ፤ የትግራይ ልጆችን አጥፋ ብሎ መመሪያ በመስጠቱ አይደለም። የህዝባችን ቀንደኛ ጠላቶች በብሄራቸው የሚነግድ የሙታን ፓለቲከኞች ናቸው። ዛሬ የትግራይ ህዝብ ለገባበት መከራ ተጠያቂው ከበረሃ እስከ ሃገረ መንግስትነት የበቃው የወያኔ ማፊያ ስብስብ ቡድን ነው። የኤርትራ ወታደር ጠላትህ ነው፤ የአማራ ልዪ ሃይል ይህን ያን አረገ፤ የመከላከያ ሰራዊት ይህን ፈጸመ የሚሉት ሁሉ ሙሉ በሙሉ የሚታመን አይደለም። ይሁን እንጂ የጦርነት ቀዳሚ ሟች እውነት በመሆኗ ጠበንጃ አንጋች ሆኖ ሰው ሁሉ ግፍ አይሰራም ማለት አንችልም። ያኔም ተሰርቷል፤ አሁንም ይፈጸማል፤ ወደፊቱም ይሆናል። የሰው ልጅ የእንስሳ ባህሪው የሚታየው የባሩድ ሽታ ሲሸተው ነውና መሳሪያ በእጅ ሲገባ ነው።
  እኔ ዶ/ር አብይን አላውቀውም። ሌሎችንም የፓለቲካ የዘርና የክልል ሾተላዎች አላውቃቸውም። ዶ/ር አብይ ለኢትዮጵያ ፓለቲካ “A Breath of fresh air” ቃሉን ሳይሆን የተገበረውን መመልከት ነው። የምእራባዊያን አካኪ ዘራፍ ማለት አልበገርም እናንተን አልሰማም በማለቱ እንጂ ለትግራይ ህዝብ አስበው አይደለም። ያ ቢሆን ኑሮ ወያኔ የሰሜንን እዝ ለማጥቃት ሲዘጋጅ ነገሩን ደርሰውበት ስለነበር ማክሸፍ ይችሉ ነበር። ዝም ነው ያሉት። አሁን የአዞ እንባ የሚያነቡት ከልብ ሳይሆን ከአንገት በላይ ነው። የሃገር ቤቱቹና በውጭ የሚንጫጩት የእድሜ ልክ ፓለቲከኞች የተሻለ ሃሳብ በማቅረብ ሃሳብን በሃሳብ እንደ መሞገት ሁሌ መግደልን፤ ጦርነትን እልቂትን እንደ መኖሪያ ብልሃት በመቁጠር ነጻ እናወጣሃለን በሚሉት ወገን ስም ሲነግድ እንደኖሩና አሁንም እንዳሉ ዓይናችን ያያል። ለዚያ ነው የእነርሱ አስተሳሰብና የጠ/ሚሩ እይታ አብሮ የማሄደው። በግድ እኛን ምሰሉ የፓለቲካ አባዜ ከምድራችን ተነቅሎ መጥፋት አለበት። ስለሆነም በፈጠራ ወሬ ጠ/ሚሩን ለማጠልሽት መከጀሉ ያለ የሚኖር የፓለቲከኞች ባህሪ ነው። ግን ዛሬ ኢትዮጵያ ላለችበት ምስቅልቅል ከጠ/ሚ አብይ የተሻለ ሰው አለ ብዬ አላምንም። ገጣሚዋ እንዳለችው ነው።
  ቢቸግር ነው እንጂ ቢጠፋብን ውሉ
  ምጥማጥና ደሮ መች አብረው ያድራሉ።
  ይብቃኝ። የሚሆነውን ቆይተን እንይ!

  • ተስፋ:-

   ችግሮችን መጠቆም መፍትሔ የሚመስላቸው : ግን ለችግሮቹ መፍትሔ መስጠት የKILIMANJARO ተራራ የሆነባቸው እንደተልባ በአንድ ሙቀጫ መንጫጫት ነው ስራቸው:: በመሳደብና በእርግማኔ አገር አይገነባም : የሕዝብ አንድነትና ደህንነት አይጠበቅም:: ችግራችን የድንቁርናችን ውጤት ነው:: የተማረ ያስባል ሲባል : እውነትንና ሃቅን ማቀፍ ባልቻለ ወንፊት ጭንቅላት ውስጥ የገባ እውቀት ከእንዲህ አይነት ተምሮ መሃይም ምሁር እባካችሁን አድኑኝ በማለት በወንፊቱ ቀዳዳ እየሾለከ የተቀባይ ያለህ እያለ ጩኸቱን እያሰማን ነው:: ፈጣሪ ልቦና ይስጣቸው ብለን እንደምንፀልይላቸው እናሳያቸው::

 2. I wish the prime minister could be a politician you try to defend and praise ! Sadly enough, the very hard reality that reflects itself in the ground for the past three years and continued without any end sight or hope does not support your generous defense and praise at all! It is both politically and morally disgraceful to deny what happened and is happening in the very watch of Anyi Ahmemed including politically motivated genocide and untold politically motivated crime against humanity ! It is a very brutal stupidity to defend and praise a politician of EPRDF who is at the very top responsibility of genocide or ethnic cleansing ! It is not a matter of like or dislike Abyi as a person ! It is a matter of rejecting his evil – guided political behavior and of course action . Believe or not. he is the guy who must face justice both at home and internationally ! It is. mater of being Oromo or any other ….! It is matter of holding him responsible and accountable as a very badly crooked and painfully dishonest political leader of the country !
  Defending and praising those who have caused and keep causing untold sufferings to innocent people of Ethiopia must end by telling the truth and challenging what is dangerous !!!!

  • TG: Believe me or not, I feel sorry for you being stuck on hate groove as a needle of a record player stuck on a tune that irritates the listener. You can call the PM ABIY whatever name satisfies your quench of throwing insult to him but it doesn’t flinch him an inch from whatever he is set to do to save ETHIOPIA & its people from never ending conflict & poverty. I wish that you can tell the readers what your solutions are for the TRIBAL ANIMOSITY which lingers in our country & the tribal conflicts which has left millions of ETHIOPIANS in TIGRAY due to the bantustan strategy of FASCISTIC WOYANE JUNTA. In my previous & this commentaries, you never presented any tangible solutions except throwing blames, cursing, insulting & condemning PM ABIY. You seem to be intelligent but the proof is in the pudding. Let me leave you with the following quote from Jocko Willink: “Just as discipline and freedom are opposing forces that must be balanced, leadership requires finding the equilibrium in the dichotomy of many seemingly contradictory qualities between one extreme and another.” That is what PM is doing to deal the multifaceted tiring problems facing our nation. So, please learn to see the light in the tunnel of his dealings of the Tragedy manifested in our nation. I say to you again that I never tried to make PM ABIY a perfect person or leader but a better one than anyone who occupied the helm of ETHIOPIAN GOVERNMENT. Is there anyone better in the pipeline of leadership in ETHIOPIA? May be. I don’t have the magic Wanda to wave to pick one. My ability is to gauge what qualities PM ABIY posses as a leader, and his intentions for the nation. Am I 100% right? Except in certain examinations when I was in school, I have never scored 100% in my judgment in my life & I will never. But I learned from early age to hold back in my negative judgements & give the opportunity to people to prove me wrong. Three years is a small fraction of time to mend the seven decades of ugly TRIBAL animosity & conflict, and that is why I stand by this young PM ABIY which ETHIOPIA has been blessed with. I am entitled to support him & you are entitled to blindly hate him.

 3. በመጀመሪያ አልማዝ አሰፋ ቀደም ሲል”ፍጹም ሰዎች በሌሉበት ምድር መሪ ፍጹም ይሁን ማለት ተገቢ አይደለም” በሚል ርዕስ የጻፍሺውን አነበብኩ። አሁን ደግሞ ልዩ የሆነ ሀቅ እና እውነተኛ ጽሁፍ አንገትም ዘወር ብሎ እንዲአስብ የሚያደርግ ጽሁፍ በመሆኑ ምስጋና ይድረስ። የሥነጽሁፍ ሰው ባለመሆኔ በአንቺ ጽሁፍ ቁስሌ አገገመ ማለትም አስችሎኛል። በጣም ጥሩ ጽሁፍ ነውና በርቺ።በዚሁ አጋጣሚ ተስፋ ለሰጠኸው አስተያየት ምስጋናው ይድረስ።

  • አምባው:-

   ለመልካም ቃሎችህ እጅግ አመሰግናለሁ:: ረጅም እድሜ የሕይወትና የመኖር መለኪያ ነው:: ከዚያም አልፎ ትልቅ አስተማሪ ነው:: በዚህ የሕይወት ሂደት ጥሩና መጥፎ ሰርተናል: አይተናል:: ከሰራናቸውና ካየናቸው ድርጊቶችና ሁኔታዎች ማንነታችን እንቀርፃለን:: የማንንታችን መመዘኛ የትምህርት መጠንና ሀብት ሳይሆን : ምንም ሕመም ቢፈጥሩብን እውነትንና ሃቅን የሕይወታችን ምሰሶ በማድረግ የማንነታችን መመዘኛና መገለጫ ይሆናሉ:: ደጋግሜ እንደጠቀስኩት የኔ እውነትና ሃቅ የሁሉም ነው ብዬ አልወስድም:: ግን እኔ ያመንኩበትን እውነትንና ሃቅ ከመግለፅ አላፍርም:: ስህተቴንም ከነማስረጃው ከካቀረቡልኝ : ትክክል ናችሁ :: ተሳስቼአለሁ ከማለት አልቆጠብም:: የውይይትና የመድረክ ሃሳብ መለዋወጡ ለመግባባት እንጂ : እኔ ትክክል ነኝ : ሌላው ተሳስቷል ለማለትና : እንደአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች እንኪያሰላምታና የስድብ ችሎታ ማሳያ አይደለም:: የሰው ልጅ ማደግ ይኖርበታል ብዬ አምናለሁ:: ስድብና ጥላቻ ቅዋሜ ለእኛም ለአገራችንም አይበጅም::

   በረከቱ አይለይህ!!

 4. በመመሰጋገን ብዛት ጊዜው እንዳይባክን ብርሀኑ ነጋን በቃህ የሚለው ሰው እንዴት ይጥፋ እንዴት 5 መንግስት እንደተምቦጃቦጀ ይቀጥላል በሀሳብ ነጥፏል ፕሮፌሰር የሚለው ቅጥያ ከአካዳሚክሱ አለም ሲፋታ አቶ ይሆናል። ዛሬ ላይ ብርሀኑ የሚናገረው አንዱም ረብ የለውም እኛ ግን ሊናገር ያሰበው እንዲህ ሊሆን ይችላል እያልን የምናዳምጠው እራሳችንን ነው። ብርሀኑና አንዳርጋቸው የምትባሉ ይቅርባችሁ ይህን ወጣትና አዲሲቱ ኢትዮጵያን የሚመጥም ሀሳብ የላችሁም።

 5. እህቴ አልማዝ ድንቅ ትንታኔ ነው:: የተወሰነውን ሃሳብሺን በመውሰድ በአጭር በአጭሩ አድርጌ እንድጠቀምበት እባክሺ ፍቀጅልኝ::

  • ውድ ያገሬ ልጅ ያሬድ:-
   ምን ችግር አለ! ሃሳብ መጋራትና ማስፋፋት የውይይት አላማ መሆን ይገባዋል::

   በረከቱ አይለይህ::

 6. ለነፍሰ ገዳይ ሰላይ የልብ ወዳጅ ሆኖ በካድሬነት ቂጥ እስቲያልብ ማረጥረጥም የአገራችንን ችግር አይፈታም ወይዘሮ ዮዲት ጉዲት!

 7. It is funny to see Abiy Ahmed cadres, paid or volunteer, praising each other. You guys do not have shame and common sense.

  • Dear, I doubt if you really grasp the essence of common sense. It needs a deep & thorough understanding of its meaning. Just don’t throw it out there but try to study its qualitative properties as a phrase. The only argumentative capacity you have is to label your counterparts with nonsensical adjectives. Show your maturity by presenting your points as TEGENAW GOSHU because I can learn something.

   • Mrs. Sell out,

    You are the one with the least common sense, trying to throw your garbage at us and make us worship your little man. Time will tell how long you will continue doing this. Once up on a time, millions of Ethiopians, including me, were in your position. However, we left that camp when white lies and machiavelli politics became routines of the little, showy guy.

 8. Dear Almaz Asefa,
  1) As I always believe, whenever we engage in a conversation and/or exchange of ideas and views on any subject matter should not be based on whether right or wrong. It rather should be a matter of trying to express our ideas and views, if possible, to find a common ground, if not agree to disagree without unnecessary attack against each other. I want to believe that the conversation between you and me is in line with this type of healthy or normal approach. I do not know your intent. But to me there is nothing that makes us enemies at all. We have a common enemy; and that is the very deadly or criminal political system of EPRDF/Prosperity.
  2) We must be mindful of the difference between attacking someone personally or his/her personal behavior and private way of life on the one hand, and her/his political and moral behavior and action which causes a profoundly serious not just problem but dangerous to the very interest of the people. If it is the later, it is necessary to call a spade a spade and fight back accordingly.

  3) I do not think any Ethiopian with his/her right and rational mind hates Abyi Ahmend based on his personal behavior and private way of life. Absolutely not! What is to be hated is his political behavior and action that is characterized by the continuation of very cynical, dishonest, hypocritical, conspiratorial, and of course deadly political system he grew up in and served as one of the most notorious cadres. So, if you are saying that telling this very fact is an insult or a terrible disrespect, so be it! Because it is his very ugly and dangerous political behavior and action and/or inaction that has caused a very devastating consequences during his regime of three years which of course continued with no meaningful end sight or hope.
  4) Is it not very painful for you to worry about the prime minister’s “great performance” but not first and foremost be worried about those innocent citizens who not only killed but also mutilated and denied places of burial simply because of who they were and what faith they worship? Was it not an open secret that the prime minister was either on foreign trip or busy with his park beautifying, busy with giving empty and highly misleading rhetoric via any means of communication, etc. whereas so many innocent citizens had to face untold sufferings?
  4) Can you tell us why the prime minister did not have a real sense of at least moral obligation to express his condolences and words of genuine concern when so many citizens perished within hours in a very inhuman way? Can you tell us why he could not declare a one-day national mourning for those innocent Ethiopians who have been victims of a deadly political system of ethno-centrism which of course he belongs to as a leader?
  5) Can’t you hear the very horrifying voices of those mothers whose wombs were cut off and their dead bodies were forced to “hug” their murdered babies? What did the prime minister do either to protect them or to take swift action against those who committed genocide including people in his own ruling party and government?
  6) Do you really think and believe that these and so many horrible inactions of the prime minister were and are simply matters of being wrong as human being? What does a common mistake as human being mean?
  7) Are you trying to say that the politics of ethno-centrism came to existence before Abyi Ahmed was born is a good or convincing excuse for what he did under TPLF to which he served as a very important cadre and what is happening in this very moment of his administration?
  8) Do you really believe that those Ethiopians who vehemently stand against all these and other countless politically motivated heinous crimes including genocide are people of beer and coffee shop? Don’t you feel self-disgusting when you go this much downward? I am not saying you as person are bad. Bu,t I hate say but I have to have say that your political thinking and position towards the prime minister and his genocidal ruling circle is painfully idiotic! You may claim again that this is an insult. Let me reiterate that if it is about your political thinking and position, not your personal identifies and behavior, so be it!
  9) You talk about the performance of the prime minister. Yes, he did some positive things when we see things as they are. But the positive things he did are not comparable with the very general and devastating situation for the past three years.
  10) This horribly cancerous or incurably toxic system of the former EPRDF, now Prosperity cannot be a leading asset toward a democratic system at all! Do you really believe that Shemeles Abdesa, Taye Denda, Agegnehu Teshager, Demeke mekonnen, Gedu Andargachew, etc. are good assets for the realization of a true democratic system? Who is the leading figure of all these and so many other ruthlessly idiotic cadres of EPRDF/Prosperity? Is it not the prime minister?
  11) The solution? a) common understanding about the question of how to get out of this horrible mess or crisis b) the need to rally behind those truly patriotic children of Ethiopia such as Eskindir Nega and his amazingly strong , firmly purposeful , unwaveringly determined , truly visionary, etc. colleagues and so many supporters who are sick and tired of the political system that has continued simply by renaming itself as Prosperity c) Insist on the very idea that the very objective of the movement is not to continue EPRDF’s political system in the name of fake reform but to bring about fundamental democratic change through inclusive national dialogue and reconciliation platform d) fight back those who may want to continue with their evil agenda and practice e) make a clear and straightforward call to the prime minister to be part of making a truly democratic Ethiopia once and for all by patriotically rejecting those forces of destruction and obstruction if he is really and truly patriotic Ethiopian . I wish I could go on and on! But I think these are some of the things to be done if we want to make our dream for a true democratic system a reality.
  It must be noted that this political system of EPRDF/Prosperity which continued its history of being badly stained with the very blood of countless innocent Ethiopians will never be an asset of true democracy if it is allowed to go ahead as a leading force!!! The prime minister must clearly and loudly be told that it is time for him to make history and save the country from falling apart and of course his own soul too!

  • TG: If you want my honest opinion on politics & politicians, I equate POLITICS to streetwalker & POLITICIANS to its enablers. But the world cannot live without the seducer & the seduced. That is the dilemma. I cannot say that I fully disagree with your arguments & assessments on PM ABIY’S silence on expressing his sympathy on the unjustified murders of innocent citizens of the country he governs. I wish he could have said something. God & he know why he kept quiet. The first duty of a reasonable, fair & just government must have been to protect the sovereignty of the nation, security & safety of its people. We have now the election. I expect him to bring acceptable & equitable change which satisfies all the citizens of the nation without any tribal favor one way or the other. The current Constitution needs to be scraped & rewritten to the satisfaction of all citizens of our nation. Till now he didn’t have the necessary mandate to effectively implement ኢትዮጵያዊነት without tribal colorings. That is why I have stood by him. My attitude is let’s give him opportunity to show us & the world that he isn’t propagating ኦሮሙማ but ኢትዮጵያዊነት.

   By the way, I respect you & your opinion. My differences are with opinions forwarded but not with the persons behind the opinions.
   Thank you for challenging me.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.